የወያኔ አገዛዝ ከፖለቲካ ኪሳራ በተጨማሪ የማትሪክ ፈተና በመሰረቁ 215 ሚልዮን ብር ኪሳራ ደርሶበታል:: ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የወያኔ አገዛዝ ከፖለቲካ ኪሳራ በተጨማሪ የማትሪክ ፈተና በመሰረቁ 215 ሚልዮን ብር ኪሳራ ደርሶበታል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎ESLCE‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎EPRDF‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በቀጣይነት የሚወሰዱ ሕዝባዊ እርምጃዎች እንደተጠበቁ ወደ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋም የሚያስገባው የአስራ ሁለተኛ ክፍል (ማትሪክ)ፈተና መሰረቁ ተንጋዶ በቆመው በወያኔው አገዛዝ ላይ ከፖለቲካ ኪሳራ በተጨማሪ የ215 ሚሊዮን ብር ኪሳራ መድረሱ ተጠቆመ::ለፈናው ወጪ የተደረጉ ለኅትመት 120 ሚሊዮን ብር ፣ ለፈተና አስተዳደር 95 ሚሊዮን ብር በአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በኩል ውጪ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ካለተመላሽ በባዶ ወያኔ አጨብጭቦ መቀመጡን ምንጮች ገልጸዋል::በሕወሓት ጥቁር ጥላ ያጠላበት የኢትዮጵያ ትምህርት እየተሽመደመደ ይገኛል::

የሕዝብን መብት እና ነጻነት ለመቀበል አሻፈረኝ ያለ ወያኔ በሚመራው አምባገነን ጁንታ ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎች እየጠነከሩ በመሄድ ላይ ሲሆን በተለይ በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ኔትወርክ ተግባራዊ ስራዎችን በተከታታይ በመስራት ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛል::አሁንም ቀጣይ እርምጃዎች በአክቲቭስቶች እንደሚወሰዱ ይታወቃል::የኦሮሚያ ተማሪዎች ከአስተማሪ ጋር ሲማሩ ከመዋል ይልቅ በክልሉ ሰርገው ከገቡ የአምባገነኑ ወታደሮች ጋር ስለነጻነታቸው ሲፋለሙ የትምህርት ጊዜው ቢቃጠልም አምባገእኦች ያልተማሩ ተማሪዎችን ለፈተና ለማስቀምጥ ያቀዱት እቅድ ሳይሳካ ቀርቶ ተኮላሽቶባቸው ለኪሳራ እና ለድንጋጤ ተዳርገዋል::ሞት ለአምባገነኖች ይህ የሕዝብ ድምጽ ነው::ትግሉ ቀጥሏል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.