ትልቁ እውነት!!! ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ባንድ ጎን – ጨቋኝ አገዛዞች በሌላ ጎን – በፍጹም አይገናኙም:: Ethiopianism


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ትልቁ እውነት!!! ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ባንድ ጎን – ጨቋኝ አገዛዞች በሌላ ጎን – በፍጹም አይገናኙም:: Minilik Salsawi
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiopianism‬ ‪#‎Ethiopian‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎MyIdentity‬

Minilik Salsawi መጀመሪያ ራሳችን እንመርምር:: ዘመኑ ስልጡን መሆኑን እናገናዝብ::ከሆያሆየ ወጥተን ሰከን እንበል::ሃገር ማለት ምን ማለት ነው? ጨቋኙስ ማነው የሚለውን እንለይ::በጭፍን ተንደርድረን ጨቋኝ አገዛዞች በሃገር እና በሕዝብ ላይ ተንሰራፍተው የሚሰሩትን ወንጀል ይዘን አንድ ግኡዝ አካል (ሓገር) ማጣጣል እና ማንቋሸሸ ከሞራል አኳያ ባዶነትን ያሳያል::በሃገርችን ለረዥም ዘመናት የነበሩ ጦረኞች በጋራ ተነስተው ጠላትን ሲዋጉ ድል ሲያደርጉ የነበሩት ሃገር ስለተነካ እንጂ የጨቋኞች ወንበር ስለተደፈረ አልነበረም::በቅርብ ጊዜ እንኳን በምስራቁ ጦርነት እና በሰሜኑ የባድመ ጦርነት ቀፎው እንደተነካ ንብ ሆ ብሎ የወጣው እና ያለቀው ወጣት ለእናት ሃገሩ ያለው ፍቅር እንጂ የወንድማማጮቹን የደርግን እና ወያኔን ስልጣን ለመጠበቅ አልነበረም::

Minilik Salsawi's photo.

በኢትዮጵያ ውስጥ ለሕዝብ የሚበጅ አንድም መሪ እስከዛሬ አልተፈጠረም::የአፄዎቹም ስርዓት ይሁን ደርግወወያኔ በሕዝብ ላይ እንዳሾፉ አልፈዋል;እያሾፉም ይገኛሉ::ኢትዮጵያ ግን እንደ ሃገር ልጆቿን ሰብስባ እስካሁን በመደጋገፍ በስሯ አድርጋ ይዛለች::ሁሉም ስለ ኢትዮጵያ ስለ ሃገር አንድ ሆኖ ቢከፋም ቢለማም እየጮኸ ይገኛል::ኢትዮጵያ ገዳይ አይደለችም ኢትዮጵያ አሳሪ አይደለችም ኢትዮጵያ ገራፊ ዘራፊ አይደለችም ወ.ዘ.ተ. ገራፊው ገዳዩ ዘራፊው አሳዳጁ በየስርዓቱ ራሳቸው እያፈራረቁ ሕዝብ በመንከስ ላይ የሚገኙት የገዢ መደቦች ናቸው::ሃገር እንደ ሃገር ሕዝብ እንደ ሕዝብ በልጥላው ላይ የፈጠረው አሊያም የደረተው አደጋ የለም::የሁሉ ችግሮች መነሻ እና መድረሻ ጬቋኝ እና አምባገነን አረመኔ አገዛዞች እና መሪዎቹ ናቸው::

አሁንም ከቻልን ረጋ እንበል::እውነታውን ትተን ከእውነታው ወጥተን ኢትዮጵያን ብናዋርድ ብናቋሽሽ ምም የሚገኝ ትርፍ የለም::አምባግነን ታግለን ጨቋኝ መደቦችን ደምሥእን በሃገሪቱ ላይ ለሕዝብ የሚበጅ አገዛዝ ብንመሰርት ግን ትልቅ ድል መሆኑ ልንገነዘብ ይገባል::ካልሆነ አያት ቅድመአያት ሞቶ እና ቆስሎ ያቆያትን አገር እንደወንጀለኛ አየሳልን የምንጓዝ ከሆነ መንገዳችን ሁሉ እንደተጣመመ ሰሚ ጆሮ እንደተደፈን እየለፈለፍን እንሄዳለን::የሕዝብን ፍላጎት እና ትኩሳት እንለካ ::በደፈናው በጭፍን ጨቋኞችን መቃወም ሲገባን ሃገርን የምናጣጥል ከሆነ የጨቋኞችን እድሜ ከማስረዘም ውጪ ምንም አናመጣም ይህን እውነት ልንውጥ ግድ ይለናል::ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ባንድ ጎን – ጨቋኝ የገዢ መደቦች በሌላ ጎን – በፍጹም አይገናኙም::ኢትዮጲያዊነት ሲበርድህ የምትደርበው፣ ሲሞቅህ ደሞ የምታወልቀው ጃኬት አይደለም!