ቀነኒሳ በቀለ ከብራዚል ኦሎምፒክ ውጪ ሆነ!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ቀነኒሳ በቀለ ከብራዚል ኦሎምፒክ ውጪ ሆነ!
ዘገባ – በናታ
በላቲን አሜሪካዋ ብራዚል የሚካሄደው 31ኛው የሪዮ ዴጄኔሮ ኦሎምፒክ ላይ የሶስት ጊዜያት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ቀነኒሳ በቀለና በተጨማሪም በካናዳ ኦቶዋ የማራቶን ባለ ክብረ ወሰን የማነ ፀጋዬም ከሪዮ ኦሊምፒክ ውጪ መሆናቸውን ተሳታፊ እንደማይሆን አትሌቲክስ ኮሚቴው አስታወቀ።
ዛሬ ይፋ በተደረገ መግለጫ የማነ 5ኛ ደረጃ አግኝቶ ተጠባባቂ ሲሆን፥ ቀነኒሳ ግን መመዘኛውን ባለማሟላቱ ነው ከምርጫው ውጪ የሆነው።
በወንዶች ለሚ ብርሀኑ፣ ተስፋዬ አበራ፣ ፈይሳ ሌሊሳና ለሊሳ ዲሳሳ፤ በሴቶች ደግሞ ትዕግስት ቱፋ፣ ማሬ ዲባባ፣ ትርፌ ጸጋዬና አበሩ ከበደ ሲመረጡ አማኔ ጎበና ተጠባባቂ ሆናለች። በዚህ ምርጫ 12 አትሌቶች ቅሬታ ማቅረባቸውም ታውቋል።
ለዚህ ምርጫ ቴክኒክ ኮሚቴ አራት ጊዜ ስራ አስፈጻሚውና የፅህፈት ቤት ሃላፊው ሶስት ሶስት ጊዜ መመዘኛውንና ምርጫውን መመልከታቸውም ተገልጿል።