ሰበር ዜና – የእንደራሴ ምደባ አጀንዳ የመንግሥት ታዛቢ ባለበት እንዲታይ ተወሰነ፤ ፓትርያርኩ በተቃውሟቸው እንደቀጠሉ ናቸው
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ የሚጥሱና የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና የሚያስደፍሩ የፓትርያርኩ እንቅስቃሴዎች መበራከታቸው፤ ሙስናንና የፍትሕ ዕጦትን በማስወገድ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በየጊዜው ከሚያደርጓቸው ንግግሮች በተፃራሪ ችግሩ እየተባባሰ መምጣቱ፤ ከዚኽም አልፎ ራሳቸው ፓትርያርኩ በአማሳኞቹና ችግሩን እንደ ከለላ(safe heaven) ተጠቅመው ኅቡእ ዓላማቸውን በሚያራምዱ የተሐድሶ ኑፋቄ ወኪሎች ተጽዕኖ ሥር መውደቃቸው፤ ይህም በሒደት የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ለከፋ አደጋ ማጋለጡ የእንደራሴ ምደባውን አስፈላጊ እንዳደረገው በምልዓተ ጉባኤው እንደታመነበት ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

ዛሬ ከቀትር በኋላ አልያም ነገ ታዛቢ ባለበት ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ተደርሷል በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ ለተከታታይ ሦስተኛ ቀን ውይይቱን የቀጠለው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ በፓትርያርኩ ተቃውሞ ምክንያት…