የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ በDropbox እና ሶሻል ሚድያዎች ተሰራጨ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።


በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ሰኞ እንደሚካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ሲሆን ሆኖም ግን ፈተናው ተሰርቆ ቀድሞ በኢንተርኔት መሰራጨቱ ታወቀ:: በDropbox አማካኝነት እንዲሁም በፌስቡክ እና በሌሎች ሶሻል ሚድያዎች ፈተናው ተሰራጭቶ የሚገኝ ሲሆን መንግስት ግን ምንም ዓይነት ፈተና አልተሰረቀም ሲል በሚያዛቸው ሚዲያዎቹ አውጇል::


