ሞረሽ ወገኔ በዐማራው ላይ ስለደረሰው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል ያወጣው ዘገባ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወያኔ በባዕዳን እርዳታና መሪነት የሥልጣን ማማ ላይ ከተቆነናጠጠበት ጊዜ አስንቶ በአማራው ማሕበረሰብ ላይ እጅግ በጣም ብዙ ለቁጥርና ለግምት አዳጋች የሆኑ የዘር ጭፍጨፋዎችን፣ ከኖረበት ቀዬ ማፈናቀል፣ በእስር ቤቶች ማሰቃየት፣ ዘግናኝ አካላዊና ህሊናዊ ሰቆቃዎችንና ሌሎችንም መከራዎች እያወረደበት ይገኛል። በዐማራው ላይ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋ በሌሎች የአገሪቱ ማሕበረሰቦች ላይ እየደረሰ ካለው የሚለይበት አቢይ ምክንያት ወያኔ ደንቆሮ ዋሻ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ አማራውን ማጥፋቱን በፖሊሲና በዕቅድ አስቀምጦ የሰው ኃይል መድቦ እየተንቀሳቀሰበት ያለ መሆኑና ለዚህም የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሆኑትን የጎረቤትና የአካባቢ መንግሥታት እንዲሁም ጥልቅ የታሪክ ጠባሳ ያለባቸውን የምዕራባዊያንንም እርጥባን በማግኝቱ ነው።  ወያኔ 25 ዓመታት ሥልጣን ላይ ቆይቶ ያፈሰሰው የአማራ ደም ስላልበቃው በተለያየ ጊዜ እያገረሸበት የንጹሃንን ደም እያፈሰሰ ይገኛል። ይህንን አስመልክቶ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያወጣውን ዘገባ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያወጣው ዘገባ