ይህ ትወልድ የግንቦት 20 ሰለባ ነው ሲሉ የራያ ቆቦ ወጣቶች ገለፁ፡፡
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ይህ ትወልድ የግንቦት 20 ሰለባ ነው ሲሉ በዲግሪ ተመርቀው ከ2-5 ዓመት ስራ በማጣት የተቀመጡ የራያ ቆቦ ወጣቶች ገለፁ፡፡
ያሬድ አማረ
*******************************************************
በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ነዋሪ የሆኑ ከ200 በላይ ወጣቶች ከተለያዩ ዪኒቨርስቲዎች በዲግሪ መርሀ ግብር ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ተመርቀው ስራ ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ገለፁ ፡፡ እንደ ወጣቶቹ ገለፃ ከተመረቁ ግዜ ጀምሮ ስራ ለማግኘት ጥረት ቢያደርጉም እስካሁን እንዳልተሳካ እና የተለያዩ የመንግስት ሀላፊዎችን ለማነጋገር ጥረት ቢደረግም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ክፍት የስራ ቦታ የለንም በማለታቸው ምክንያት ከተመረቁ ከ2-5ዓመት ያለስራ ለመቀመጥ መገደዳቸውን ገልፀዋል፡፡አያይዘውም አብዛኛው ተመራቂ ተስፋ በመቁረጡ እና ትምህርት ጨርሶ የቤተሰብ ተጧሪ ለመሆን በመገደዱ ምክንያት አማራጩን በባህር ወደ አረብ አገራት እያደረገ መሆኑንና ይህም በስርአቱ የተሳሳተ የትምህርት ፖሊሲም ቢሆን ታልፎ እና ትመህርቱን ጨርሶ ለሚወጣው ተመራቂ አማራጭ የስራ እድል የሚያገኝበት ተቋማት ባለመገንባታቸውና ባለመዘጋጀታቸው ምክንያት ይህ ትውልድ አማራጭ እንዲያጣና ተስፋ እንዲቆርጥ የተፈረደበት የግንቦት 20 ሰለባ ነው ብለዋል፡፡