የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ሃላፊ አቶ ኢሳይያስ ወልደ ጊዮርጊስ ከስልጣናቸው ተባረሩ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ሃላፊ አቶ ኢሳይያስ ወልደ ጊዮርጊስ ከስልጣናቸው ተባረሩ። ባሌቤታቸውም ከስራቸው የተነሱ ሲሆን፡ ሁለቱም በጸጥታ ሃይሎች ክትትል ውስጥ ይገኛሉ።በአቶ ኢሳይያስ ምትክ በደርግ ዘመን የደርግ ደህንነት የነበሩት ሃደራ አበራ ተክተዋቸዋል።ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቅርብ የነበሩት አቶ ኢሳይያስ ወልደጊዮርጊስ መባረራቸውን ተከትሎ በሌሎች ሃላፊዎችም ሆነ ሰራተኞች ላይ ስለተወሰደ ርምጃ የታወቀ ነገር የለም። ወ/ሮ አዜብ መስፍን ግን የአቶ ኢሳይያስን ስንብት ተከትሎ ባለፈው ቅዳሜ አሜሪካ ገብተዋል፡ ዋሺንግተን ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ካሜራ ዕይታ ውስጥ የገቡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአንድ ልጃቸው ጋር ሰለመጡብት ምክንያት በውል የታወቀ ነገር የለም።
Source ESAT TV