ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች በተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለዋል; 100 ያህል ሰዎችን ለሞት ተዳርገዋል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች በተፈጥሮ አደጋ ተፈናቅለዋል ተባለ

አደጋዎቹ 100 ያህል ሰዎችን ለሞት ዳርገዋል
ጎርፉ ተጨማሪ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊያፈናቅል ይችላል

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ከ20 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቤታቸው እንደተፈናቀሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስታወቁንና መንግስትም 100 ያህል ዜጎች በአደጋዎቹ ለሞት ተዳርገዋል ማለቱን አልጀዚራ ዘገበ፡፡
በአገሪቱ በመከሰት ላይ ያሉት የጎርፍ አደጋዎች ዜጎችን ከማፈናቀል ባለፈ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች እርዳታን በማከፋፈል እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን የጠቆመው ዘገባው፤ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ትብብር የኢትዮጵያ ተወካይ ፖል ሀንድሊም የተፈጥሮ አደጋዎቹ በቀጣይ ሰብሎችንና እንስሳትን ከማውደም ባለፈ ዜጎችን ለከፋ ችግር ሊያጋልጡ ይችላሉ ማለታቸውን ገልጧል፡፡
የእርዳታ ድርጅቶችም የጎርፍ አደጋዎቹ ቀጣይ እንደሚሆኑና ሌሎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊያፈናቅል እንደሚችል ግምታቸውን መስጠታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የተፈጥሮ አደጋዎቹ የተከሰቱባቸው አንዳንዶቹ አካባቢዎች የድርቅ ተጎጂ መሆናቸውንና ዜጎችን ለተጨማሪ ችግር መዳረጋቸውን አስረድቷል፡፡

Source addis admass