የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዘላለም ወርቃአገኘሁ ላይ አምስት አመት ከአራት ወር የእስር ቅጣት በየነ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዘላለም ወርቃአገኘሁ ላይ አምስት አመት ከአራት ወር የእስር ቅጣት በየነ። ዘላለም እና ጓደኞቹ ከሀገር ውጪ የሚሰጥ የኢንተርኔት ደህንነት ስልጠና ለመውሰድ ማመልከታቸውን ተከትሎ “ለሽብር ተግባር ተሰናድተዋል” ተብለው ከሁለት አመት በፊት ለእስር ተዳርገዋል።
ወጣቶቹ የተከሰሱበት ስልጠና ፈፅሞ ያልተካሄደ ሲሆን አላማውም ከየትኛውም የፖለቲካ ቡድን ጋር የተያያዘ አልነበረም። ዘላለም ለደ ብርሀን ድረ ገፅ ተባባሪ ጦማሪ ሲሆን ከመታሰሩ አስቀድሞ በትምህርት ላይ ነበር። ሌሎቹ ታሳሪዎች ከሳምንታት በፊት ከእስር በነፃ ተሰናብተዋል።
Wazema Radio ዋዜማ ሬዲዮ