ውይይት ከሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ ጋር
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ውይይት ከሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ ጋር

ሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ Major Dawit WeldeGiorgis Interview
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ መከሰቱ፣ በዚህም ሚክንያት አያሌ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለራብ መጋለጣቸው፣ ሕይወታቸውን ያጡም እንዳሉ፣ ድርቁም አስጊና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የዓደባባይ ምስጢር ነው።
የዛሬው ወጋችን ግን በሕይወት ታሪካቸው ማለትም ስለ አስተዳደጋቸው ወይም ስለ ትምህርት ቤት ሕይወታቸው ሳይሆን፣ (ያ ለሌላ ጊዜ ይቆየንና) ዛሬ የምናተኩረው ይበልጥ በሚታወቁበት በእርዳታ ማሰባበሪያና ማቋቋሚያ ኰሚሽን አገልግሎታቸው ዙሪያ ይሆናል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ መከሰቱ፣ በዚህም ሚክንያት አያሌ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለራብ መጋለጣቸው፣ ሕይወታቸውን ያጡም እንዳሉ፣ ድርቁም አስጊና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የዓደባባይ ምስጢር ነው።
በመሆኑም በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ፣ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ እንግዶችን፣ ባለሙያዎችን እየጋበዝን አወያይተናል። ሻለቃ ዳዊትም ለዚህ ዓይነቱ ርዕስ ተገቢ እንደሚሆኑ በማመን፣ ከእርሳቸው ጋር ካደረግንው ሰፊ ውይይት፣ ለዛሬ በወቅታዊው ድርቅና ረሀብ፣ እንዲሁም በመፍትሔ ሃሳቡ ላይ ብቻ እናተኩራለን። ያወያያቸው አዲሱ አበበ ነው።
“በአሁኑ ወቅት የት ነው እንዴ ያሉት? ምንስ እየሠሩ ነው?” ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት መልስ እንነሳለን። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።