የዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ 171 ገጾች ያካተተ የሚያሳፍር ‘የአዛውንት ምስክርነት’ ይፋ ሆነ!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ዶ/ር አክሊሉ እርስ በርሱ የሚጋጭ ምስክርነት ዲሲ ር/አ/ደ/ሰ/ቅ/ ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

Dr. Aklilu

የዲሲ ር/አ/ደ/ሰ/ቅ/ ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከመስከረም ጀምሮ ቤተክርስቲያኗ በዶ/ርና ሌሎች የተለያየ አጀንዳ የያዙ ቡድኖች ጋር በመተባበር በአባሎች ተመርጦ የነበረውን የባለአደራዎች ቦርድ በኃይል መፈንቅለ ቦርድ ማድረጋቸውን ከአሁን በፊት ዘግበናል።  

ይህንን ተከትሎ ቤተክርስቲያኗ በሯ ተሰብሮ በጉልበት በነ ቄስ ተስፋዬ መቆያና ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ ቡድን ቁጥጥር ስር ከማድረጋቸው በፊት የመፈንቅለ ቦርድ የታቀደ እንደነበር የሚያረጋግጥ ከዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ ምስክርነት ተገኝቷል።

ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የተለያዩ ሰዎችን በማነጋገር ባደርገውነው ማጣራት፤ ዶ/ር አክሊሉ ሃብቴ የርእሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የባለ አደራዎች ቦርድ አባል በመሆን ከ18 ዓመታት በላይ ሲያገለግሉ ቆይተው በራሳቸው ጥያቄ ከቦርድ አባልነት ተሰናበቱ። ብዙ ሳይቆዩ  በሕዝብ ፊት ቆሞ ማስጨብጨብ ስለጎደለባቸው ይመሰላል ፤ የለቀቁትን ስልጣን ቀጥታ  ባያገኙም እንደገና በጎ ፈቃደኛ በመሆን በህንፃ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢነት ማገልገል ጀመሩ። የቤተክርስቲያኑን ባኣደራዎች ቦርድ እንደፈለጉት ማድረግ እንደማይችሉ ሲያውቁ መጋጨት ጀመሩ። ይህ ግጭት እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ በየሳምንቱ ከህዝብ ፊት እየቀረቡ ውዳሴ ሲቀርብላቸው፣ ሲጨበጨብላቸው የማቱሳላ እድሜ ሲለመንላቸው እንደነበር ምዕመናን ይናገራሉ።

በአንድ ወቅት፣ ባልታወቀ ምክንያት ራሱን ተቆርቋሪ ብሎ ከሚጠራ ቡድን ጋር ሆነው እንደ ሁልጊዜው ሁሉ፤ በማንኛውም ስብሰባ መሪ የመሆን የሁሌ ባህሬአቸው  የገነቡትን ማፍረስም ጀመሩ። ይህንን ተከትሎ የተጀመረው የፍርድ ቤት ጉዳይ የሰጡት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሰነድ ይፋ ሆነ።

በዚሁ 171 ገጾች በያዘው የምስክርነት ሰነድ ውስጥ ብዙ ኢንኳን ‘ከአዛውንት’ና ከሌላም ሰው አንደበት ይውታል ተብሎ የማይገመት የክህደት ቃሎች መካከል ተናገሩ። አንድ ሁለቱን ለምጥቀስ ያህል:

  1.  በራሳቸው በዶ/ር አክሊሉ የቦርድ ሊቀ መንበር ሰብሳቢነት  በነበሩበት ወቅት ለጥምቀት አገልግሎት ተመድበው በአድማ በመቅረታቸው በቤተክርስቲያኗ ደንብ መሰረት ከስራ ያገዷቸውን ካህናት፣ እገዳው ትክክል አይደለም በተለይም በእኛ እምነት ምእመን ካህናትን ማገድ አይችሉም በማለት የራሳቸውን ውሳኔ የሚቃረን የሐሰት ምስክርነት ሰጥተዋል።
  2. የቤተ ክ/ኗ ህግ ማሻሻያ በአግባቡ አልጸደቀም የአባላት 2/3 ምልአተ ጉባዔ ያላጸደቁት ህግ እንደ ህግ ሊቆጠር አይችልም ሲሉ እርሳቸው ሰብሳቢ ሆነው በ2003 ያሳለፉትን 2/3 አባላት ያልተገኙበትን ማሻሻያ ግን ለቤ/ክርስትያኗ እድገት በማሰብ የተደረገ እንደ ሆነ ሊያስረዱ ሞክረዋል።
  3. የጊዜያዊ ኮሚቴውን የመረጠው አካል በቤ/ክኗ ህግ መሰረት ያልተቋቋመ መሆኑን አምነው ይህም የሆነው ለቤተክርስትያኗ እድገት እንደሆነ ያስረዳሉ።

በአጠቃላይ እርሳቸው የሰሩትን ስራ መለኮታዊ የሌሎችን ግን ሰውሰራሽ በማስመሰል ያቀረቡትን የሐሰት ምስክርነትና ሌሎችንም ከአንድ ‘አዛውንት’ የማይጠበቅ ዝርዝር ቃል ለማንበብ የሚቀጥለውን ሰንሰለት ይጫኑ።  የዶ/ር አክሊሉ ሀብተ የምስክርነት ቃል ሙሉውዝርዝር:  http://www.dskmariam.org/images/Board-News/Habte-Aklilu_full.pdf

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከቤተክርስቲያን ዉጭ ያሉት የቤተክርስቲያን አባላአት ሲያከብሩ የሚይሳይ አጭር ቪድዮ ይመልከቱ።

የተገፉት የቤተክርስቲያኑ አባል ህዝበ ክርስቲያፋሲካን ሲያከብሩ።