በወያኔ እስር ቤት ሲሰቃዩ የነበሩት ሁለት ፖለቲከኞች ከእስር መፈታታቸው ተሰማ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በወያኔ እስር ቤት ሲሰቃዩ የነበሩት ሁለት ፖለቲከኞች ከእስር መፈታታቸው ተሰማ::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎HumanRights‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Freedom‬

Minilik Salsawi's photo.

Minilik Salsawi – Ethiopian DJ የወያኔው አገዛዝ በሃሰት ክስ መስርቶ ሽብርተኛ ብሎ ሲያንገላታቸው የነበሩ ሁለት ፖለቲከኞች የእስር ጊዜያቸውን አጠናቀው ከእስር መፈታታቸው ሲታወቅ አብሯቸው የታሰረው አብርሃ ደስታ አለመፈታቱ ታውቋል::

በማእከላዊ ማሰቃያ ጣቢያ በወያኔው እስር ቤት ከፍተኛ በደር ቶርች እና ስቃይ ያሳለፉት የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ዳንኤል ሺበሺ እና የሰማያዊ ፓርቲው የሺዋስ አሰፋ ከታሰሩበት ክስ በተጨማሪ ፍርድ ቤት ደፍራቹሃል በሚል በወያኔው የካንጋሮ ችሎች እስር ተፈርዶባቸው ነበር:: በአላማቸው ጽናት እና በፖለቲካ አቋማቸው ሽብርተኛ ተብለው ተፈርጀው በሃሰት ክስ የተንገላቱት ወገኖቻችን በአለም አቀፉ ሕብረተሰብ እና በኢትዮጵያውያን ጫና ከወያኔ እስር ቤት ተፈተው ወደ ሰፊው ሕዝብ እስር ቤት ተቀላቅለዋል::

ከዚህ ቀደም እንዲሁ ሲንገ ላታ የነበረው ሃብታሙ አያሌው መፈታቱ ይታወሳል::ይህ የወያኔ ስርኣት ካልተገረሰሰ በቀር የዜጎች ስቃይ የሚቀጥል ሲሆን አገዛዙን ለመደምሰሰስ ሁላችንም በጋራ ልንቆም ይገባል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬