በአዲስ ከተማ አንድ ጎልማሳ ራሱን አቃጥሎ ገደለ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 2፣ ልዩ ቦታው ጭላሎ ሆቴል ገባ ብሎ እድሜው  55 ዓመት ገደማ
ይሆናል የተባለ ጎልማሳ ራሱን አቃጥሎ ገደለ፡፡ ይሄይስ ደምሴ የተባለው ይኸው ጐልማሳ፣ ሐሙስ ጠዋት 12 ሰዓት አካባቢ በመኖሪያ ቤቱ በረንዳ ላይ ሰውነቱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ እሳት በመለኮስ፣ ራሱን አቃጥሎ እንደገደለ የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ሟች ራሱን ሲያቃጥል የተመለከተች የግቢው ተከራይ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት ተጐጂውን ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ቢሞከርም ህክምና ቦታ ሳይደርስ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል፡፡
ግለሰቡ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ሰላማዊ የወዳጅነት ግንኙነት ያለውና ከሁሉም ጋር ተግባቢ እንደነበር የጠቀሱት የቅርብ ወዳጆቹ፤ እነሱ እስከሚያውቁት ድረስ ምንም ዓይነት ለዚህ አሰቃቂ ድርጊት የሚያደርስ እክል እንዳልነበረበት ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ በዚህ መንገድ ህይወቱ ማለፉ የአካባቢውን ህብረተሰብ ማስደንገጡንም ምንጮቻችን አክለዋል፡፡ ሟች ይሄይስ ደምሴ የመኖሪያ ቤት ክፍሎችን እያከራየ በሚያገኘው ገቢ ይተዳደር የነበረ ሲሆን ትዳርም እንዳልመሰረተ የአካባቢው ምንጮቻችን ጠቅሰው፤ ለረጅም አመታት በብቸኝነት ይኖር እንደነበር አስረድተዋል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በዚያው ዕለት 9 ሰዓት ላይ በአማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡