“የሰሜን ሱዳን ወታደሮች በተራቸው ኢትዮጵያን ጥሰው ገብተው እያፈኑ መውሰድ ጀምረዋል” ቪኦኤ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“የሰሜን ሱዳን ወታደሮች በተራቸው ኢትዮጵያን ጥሰው ገብተው እያፈኑ መውሰድ ጀምረዋል” ቪኦኤ
++++++++++++++++
ከጥቂት ወራት በፊት : የ ኤርትራ ወታደሮች ወርቅ ለማውጣት ይቆፍሩ የነበሩ በርካታ ወጣቶችን ታፍነው መወሰዳቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ገልጾ ነበር:: ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ ዩኒፎርም የለበሱ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን ገድለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕጻናትን አፍሰው መውሰዳቸውን አሁንም የኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል:: አሁን ደግሞ የሰሜን ሱዳን ወታደሮች ቤንሻንጉል ድረስ ገብተው በርካታ ኢትዮጵያውያንን አፍነው ወስደው ሱዳን እንዳሰሯቸው እና ሌሎቹም የት እንደገቡ እንደማይታወቅ ባለሀብቶች እየገለጹ ነው::
ቀጥሎስ ተረኛው ማን ይሆን? የጅቡቲ ወይስ የኬንያ ወታደሮች?

አልኑር በሽር ሲባል በቆየ በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል በጉባ ወረዳ በኦሜድላ ቀበሌ ባለ እርሻ ልማት ላይ የሚሠሩ 22 ሠራተኞች በሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሰዳቸውን የእርሻ ልማቱ ባለቤት ነኝ ያሉት አቶ ይርሳው የሺወንድም ተናግረዋል።