ሐጎስ ገብረህይወት – “ኢዶ”


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Tigrigna singer Hagos Gebrehiwot

ሐጎስ ገ/ሂወት ታዋቂ የትግርኛ ዘፋኝ ነው። ብዙዎች የሚያውቁት የኢትዮጵያን ባንዲራ ግንባሩ ላይ ጠምጥሞ ሲያዜም ነው። 4 ወንድሞቹ ለህወሓት ሲታገሉ ሞተዋል። በ1990 ዓ.ም ሻዕቢያ ጦርነት ሲከፍት ወደ ግንባር ከዘመቱት ጥላሁን ገሰሰ፣ መሀሙድ፣ ታምራትና ሌሎች ታዋቂ ዘፋኞች ጋር አብሮ የተጓዘው ሀጎስ ዝግጁት ሲያልቅ አዛውንት አባቱ ወደሚኖሩበት ቦሎሞኮዳ ወረዳ “ይፈልጉሀል” ተብሎ አመራ። አባቱ በተደራራቢ ሀዘን ህይወታቸው አልፎ ደረሰ።

በ1996 ዓ.ም “የህመንሎ” በሚል ርእስ የተለየ አልበም ይዞ ወጣ። “ኢዶ” የምትለው የሀጎስ ዜማ “መሬታችን ተቆርሶ- ተሸራርፎ፣ ውሃችን (ወደብ) ተወስዶ፣ ሁሉም ጀርባ ተሰጣጥቶ፣ ሀብትና ንብረት የሚዘርፉት ህዝብ አጣልተው እንዳይሸሹ በትርህን ይዘህ ጠብቃቸው” ይላል። በትግራይ የገጠር መንደር ድረስ ሰፊ አድማጭና ተቀባይነት ያገኘው ይህ የሐጎስ አልበም በገዥው ሰፈር ቁጣን በመቀስቀሱ፣ የወቅቱ የማ/ሚ/ር በረከት ስሞኦን ለኢቲቪና ራዲዮ ባስተላለፉት ቀጭን ትእዛዝ የሐጎስ ማናቸውም ዘፈኖች በመንግስት ሚዲያ እንዳይተላለፍ አደረጉ። ወሎ ሰፈር በሚገኘው ቤቱ ደጃፍ ድብደባ ተፈፀመበት። ጭራሽ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ። የምሽት መዝናኛ ሲሰራ “ኢዶ የምትለዋን ትዘፍንና” እየተባለ በደህንነቶች ተዋከበ። ሰርግና መሰል ዝግጅት እንዳይሰራ ሰፊ ዘመቻ ተካሄደበት። የገዥው ልሳናት “ወይን” እና “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ጋዜጦች “ይህ ባንዳ፣ ያመኛል አለ? ይህ በሽተኛ ደርግ” እያሉ ያለማቋረጥ ስድብና ዘለፋቸውን አዘነቡበት። በደርግ ዘመን ለምስራቅ እዝ ኪነት ሲያዜም የነበረውን ፎቶ እያያዙ ተሳደቡ። ጦር ሀይሎች ሆ/ል ሰው ለመጠየቅ ሲሄድ በአጋጣሚ ያገኛት የመለስ ዜናዊ ታናሽ እህት “ሐጎስ እንዴት ትሰደብናለህ? ማነው ሌባ” ስትል ልታሸማቅቀው ሞከረች። ደህንነቶች እየተከታተሉ “ከዚህ በኋላ ትዘፍንና እናጠፋሀለን” እያሉ አዋከቡት።

ወዲ ህዝቢ ማለትም የህዝብ ልጅ በሚል ቅፅል ስም የሚጠራው ሐጎስ ገ/ሂወት በዜማው ላይ “እኔ በሙያዬ የእናት አገሬ አደራ አለብኝ! ብዙ እንደሚሉኝ ባውቅም አልንበረከክም! ሌሎች አንቀላፉና እኔ እንዴት ብዬ ልተኛ አገሬ ኢትዮጵያ” ብሏል። በሙያው መስዋእትነት የከፈለው ድምፃዊ ሀጎስ ከህዝብ የሚገባውን ድጋፍ አለማግኘቱና አስታዋሽ ማጣቱ አሳዛኝ ነው! ይህቺ ናት ኢትዮጵያ!

ዘፈኑን ያዳምጡ↓