ሃይለማርያም ደሳለኝ ውበታቸውን ለማስተካከል የፊት ቀዶ ሕክምና በጀርመን ሊያደርጉ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሃይለማርያም ደሳለኝ ውበታቸውን ለማስተካከል የፊት ቀዶ ሕክምና በጀርመን ሊያደርጉ ነው:: #Ethiopia ……

ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሕወሓት ጠ/ሚኒስትሩ ከቀናት በፊት የግል አውሮፕላን ተከራይተው ባደን ባደን በተባለ የጀርመን ከተማ የገቡ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው በስፍራው ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል። አቶ ሃይለማርያም በጀርመን የእረፍት ጊዚያቸውን የሚያሳልፉበት ለእረፍት በሚል በገዙት ቤት ሳይሆን እንደማይቀር የገለጹት ምንጮች፣ በቆይታቸውም ለአይናቸው የውበት ቀዶ ጥገና ወይም ኮስሞቲክስ ሰርጀሪ ሳያደርጉ እንደማይቀር ምንጮች ገልጸዋል።

20 ሚሊዮን ህዝብ በተራበበት እና ከፍተኛ አለማቀፍ እርዳታ እየተለመነ ባለበት በዚህ ወቅት፣ አቶ ሃይለማርያም ለእረፍት እና ለውበታቸው በመጨነቅ የግል አውሮፕላን ተከራይተው መምጣታቸው በአገሪቱ ያሉ መሪዎችን ባህሪ እንደሚያሳይ ምንጮች አስተያየታቸውን ገልጸዋል።ባደን ባደን የጀርመን ሃብታሞችና ታዋቂ ሰዎች ከሚኖሩባቸው ከተሞች መካከል አንዷ ናት።