ከታገቱ የኢትዮጵያ ህጻናት 32 ተለቀቁ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከታገቱ የኢትዮጵያ ህጻናት 32 ተለቀቁ

ከታገቱ የኢትዮጵያ ህጻናት 32 ተለቀቁ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ሰርገው በገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከታገቱ 125 ህጻናት መካከል 32 መለቀቃቸውን የደቡብ ሱዳን መንግሥት ባለሥልጣናት አስታወቁ።

በደቡብ ሱዳን የቦማ ግዛት ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ኦጋቶ ቻን ከሊኳንጎሌ ሦስት መንደሮች የአካባቢው ባለሥልጣናት ጥቃት ፈጻሚዎቹ ጥለዋቸው የሄዱ ያሏቸውን ህጻናትን መሰብሰባቸውን ዛሬ ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ቀደም ሲል አጋቾቹ ላይ ከበባ አድርጌያለሁ ሲል ገልጦ ነበር።:-/

ህጻናቱ ወደ ቦማ ግዛት ዋና ከተማ ፒቦር፤ ከዚያም ወደ ጁባ ከተወሰዱ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ የቦማ ግዛት ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ተናግረዋል። ቀሪዎቹ ህጻናትም እየተፈለጉ መሆኑን ጊዜያዊ አስተዳዳሪው ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከደቡብ ሱዳን ድንበር ያቋረጡ ታጣቂዎች በጋምቤላ በፈጸሙት ጥቃት በርካቶችን ገድለው 208 ሴቶች እና ህጻናትን አግተው መውሰዳቸውን አስታውቆ ነበር::

DW Amharic