ክፉ ወሬ : ሌሊት 6፡30 እና 9፡30 አካባቢ ከማርስ የሚመጣው ጨረር ምድራችንን ይመታል:: ስልካችሁን አጥፍታችሁ ተኙ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


‹‹ዛሬ ሌሊት ምድራችን ከማርስ በመጣ ጨረር የምትመታ በመሆኑ ስልካችሁን አጥፍታችሁ ተኙ››
=================== Dawit Solomon
ዛሬ በተለያዩ መንገዶች ሰዎች ሌሊቱን ምድራችን ከማርስ በመጣ ጨረር የምትመታ በመሆኑ ከመተኛታችን በፊት ስልካችንን ማጥፋት እንደሚገባን የሚመክሩና የሚያስጠነቅቁ መልእክቶች መተላለፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

A glimpse of tonight's 'Blood Moon' amid cloudy skies as seen from Montalban, Rizal. Image was taken a few minutes after totality.

ሌሊት 6፡30 እና 9፡30 አካባቢ ከማርስ የሚመጣው ጨረር ምድራችንን ይመታል በማለት ስልካችንን እንድናጠፋ ወይም ከአቅራቢያችን እንድናርቅ የሚመክሩን ሰዎች የመረጃውን ትክክለኝነት በተመለከተም ናሳ ለቢቢሲ የሰጠውን ማስረጃ እንድንመለከት ይወተውታሉ፡፡
ነገር ግን ወደ ቢቢሲ ፔጅ በማምራት መረጃ ስንጠይቀው በጉዳዩ የተሰላቸ የሚመስለው ቢቢሲ እንዲህ አይነት ክፉ ወሬ ከ2008(በፈረንጆቹ)ጀምሮ ሲናፈስ መቆየቱን ይነግረናል፡፡
ቢቢሲ መረጃው ከውሸት የማይዘል መሆኑን ለመጥቀስም የተለያዩ ሳይንሳዊ ምክንያቶችን ዘርዝሯል፡፡
1)ማርስ ጎጂ የሆነ ጨረር ማመንጨት አትችልም ምክንያቱም ኮከብ አይደለችም፡፡እንዲህ አይነት ጨረሮች ሊፈጠሩ የሚችሉት በኮኮቦች ብቻ ነው፡፡
2) እንዲህ አይነት ጨረር እንኳን ወደ መሬት የሚመጣበት ሁኔታ ቢፈጠር የመሬት ከባባዊ አየር በራሱ በቁጥጥር ስር የሚያውላቸው በመሆኑ ሊያስጨንቁን አይገባም፡፡የመሬት የስበት ኃይል እንዲህ አይነት ጎጂ ጨረሮችን በመዋጥ ይከላከለናል፡፡
በተረፈ ዝርዝር ሁኔታውን ለመመልከት ከታች ያስቀመጥኩልዎን ሊንክ ይመልከቱ፡፡ https://journeytothestars.wordpress.com/