ኢሕኣዴግ የተረጋጋ መንግስት እየመራ አለመሆኑን የድርጅቱ ሰዎች እየተናገሩ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ እገኛለሁ:: በአዲስ አበባ ቆይታዬ ከሄድኩበት ጉዳይ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ሚና ከሚጫወቱ የማህበራዊ ድህረገጽ ጓደኞቼ ጋር ተገናኝቶ በሰፊው የመወያየቱ እድል ገጥሞኛል::ከነዚህ ወዳጆቼ ውስጥ የተወሰኑት በወያኔ አገዛዝ ውስጥ በስልጣን ላይ ተቀምጠው ወያኔን የሚያጋልጡ የውስጥ አርበኞች የማግኘቱ እድል የገጠመኝ ሲሆን ኢሕኣዴግ ውስጡ ያልተረጋጋ መንግስቱ የደፈረሰ መሆኑን በእርጋታ የውስጥ ፖለቲካቸውን እያጣቀሱ በስፋት አጫውተውኛል::

የጥቂት ግለሰቦች ትእዛዝ የሚፈጽሙ ቡድኖች በራሳቸው የሚመሩ እና ማስተዋል ያልፈጠረባቸው የክልል ባለስልጣናት ክትትል እና ቁጥጥር የሌለበት የሃገሪቱ አስተዳደር ዘርፍ ማእከላዊ አመራሩ ላይጠራ የደፈረሰበት እና በጥቅም የተሳሰሩ ባለስልጣናት የሚፈነጩበት ድርቅ እና ረሃቡን በተመለከተ የድርጅቱን አመራሮች አቋም በአባላቱ ዘንድ ኩርፊያ መፍጠሩ የመከላከያ እና ደህንነትን ጉዳይ በተመለከተ እንዲሁም የውጪ ፖሊሲን በተመለከተ ከሕወሓት ባለስልጣናት ውጪ ሌሎች ምንም መረጃ እንደማይሰጣቸው እና እንዳሌላቸው በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ዘመን ብኣዴን ይሁን ኦሕዴድ በሁሉም ተቃማት እስጥ የማገልገል እድሉ እና አቅሙ ሲኖር አሁን ግን አቅሙ አያለ ደህንነት ውጪ ጉዳይ እና መከላከያ ውስጥ በማንናውም የስልጣን እርከት እንዳይኖሩ መደረግ ያሉትንም በማውረድ እና በማግለል ከስተዳደር ስራ ጋር ማቀናጀት እየተለመደ ነው::

ሕዝቡ በኑሮ ውድነት እያማረረ ስለፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ስኬቶች ማውራት በራሱ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን ችግር ለሌላው ያሳያል ስብሰባ የሚባለው ሁሉ ለፕሮፓጋንዳ እንጂ ከአዳራሻ ውጪ ትርጉም የሌለበት ባለስልጣናት ለሕግ እና ለመመሪያ ለሕዝብ ጉዳዮች ለውሳኔ እና ለደንብ ሳይሆን ለጥቂት ግለሰቦች ታዛዥ መሆናቸው ተወሰነ ይባል እንጂ ማንም ጠያቂ የሌለበት በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል መተማመኑ የሰፋ ሲሆን ሕወሓት ከደቡብ ግንባር ውጪ ከብኣዴን ይሁን ከኦሕዴዽ ሰዎች ጋር በፍጹም አለመተማመን ውስጥ ሲሆኑ በየቀኑ የሕወሓት በቀል እና ጥቃት በድርጅቶቹ አባላት ላይ እያረፈ እንደሚገኝ ሕወሓት በአምሳሉ የፈጠረው የሃይለማርያም ደሳለኝ የደቡብ ሕዝቦች ግንባር የሚባለው የሕወሓት ዋና አለቅላቂ እና አሽከሮች ስብስብ ሲሆን ከብኣዴን እና ኦሕዴድ አባላት ጋር በፍጹም እንደማይስማሙ ታውቋል::በነዚህ እና ወደፊት በዝርዝር በምናያቸው ጉዳዮች ወያኔ የተረጋጋ መንግስት እየመራ እንዳልሆነ አስረድተዋል::

በሃገሪቱ ጠንካራ የሚባል የለውጥ ሃይል ስብስብ የሆነ ፓርቲ አለመኖር እና የተቃዋሚዎች የእርስ በእርስ መናቆር የወያኔን አለመረጋጋት ሽፍኖታል የሚሉት የውስጥ አርበኞቹ ከኢሕኣዴግ ፓርቲ ውስጥ ከባድ የሱናሚ አብዮት እንደሚነሳ ጠቁመዋል::ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በግለሰብ ደረጃ የለውጥ ሚና የሚጫወቱ ጠንካራ ዜጎች ቢኖሩም በድርጅት ደረጃ ግን ሁሉም መልፈስፈሳቸውን እንዲሁም ከትጉህ እና ታጋይ አባላት ይልቅ ሰርጎገብ ቅጥረኞች በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ ክብር እና ቦታ ማግኘታቸው የወያኔን ገበና እንደሸፈነለት ገልጸዋል::(ይቀጥላል) ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.