ውጤት አልባው ኢሕኣዴግ የውጪና የደህንነት ፖሊሲውን እንዲፈትሽ የቀረበለትን ሃሳብ እየመረመረው ነው:: ‪


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የደህንነት ተቋሙን ምስጢር ለውጪ ሃይል አሳልፈው ሰጥተዋል የተባሉ የደህንነት ሃይሎች አስሯል::በተባለበት በዚህ ሳምንት ውስጥ ኢሕኣዴግ መራሹ መንግስት የውጪ ፖሊሲውን እንዲፈትሽ የቀረበለትን ሃሳብ እየመረመረው መሆኑን ለኢሕኣዴግ አገዛዝ የደህንነት እና የዲፕሎማሲ አማካሪዎች ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል:: በአራት ዘርፍ ተከፍሎ በግለሰቦች አምባገነናዊ አመራር ስር የወደቀው የደህንነት እና የዲፕሎማሲው ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ በሃገር እና በዜጎች ላይ አደጋ መደቀኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረው ኢሕኣዴግ የውጪ ፖሊሲው ከዜጎች ይልቅ ዜጋ ላልሆኑት ቅድሚያ መስጠቱ እንዲሁም የደህንነት ተቋማቱ ዜጎችን ለማጥፋት ሌት ተቀን እየሰሩ መሆናቸውን በግልጽ ያስቀመጠ ሲሆን እየተከተለ ያለው ፖሊሲ አደጋው ለሃገሪቱ ካሁኑ በባሰ መልኩ ብሄራዊ ውርደትን ያከናንባል በተያዘው ቸልተኝነት እና ነገርን በንግግር ብቻ አንጠልሎ መተው አደጋው የከፋ መሆኑ ተገልጿል::

ለሃገር ቅድሚያ ሰጥቶ ዜጎችን ማክበር ማስከበር ያልቻለ መንግስት የውጪን ወረራ መመከት ያስቸግረዋል የሚሉት አማካሪዎቹ ከውጪ ሃይሎች ለሚደረግ ማንኛውም የግልጽ እና የእጅ አዙር ወረራ ሕዝብ ፊቱን ካዞረ መመከት ስለማይቻል ወቅታዊ ሁኔታዎች ስጋታቸው መስፋቱን ጠቁመዋል::ሕዝቦች በመንግስት ላይ እምነት የሚኖራቸው ብሄራዊ የዜግነት ማንነታቸውን የሚያከብር አገዛዝ ሲኖር መሆኑን መዘንጋት የለብንም የሚሉት አማካሪዎቹ ለዜጎች የምንተገብረውን እና የምንጠቀምበትን ቋንቋ ልንለይ እና ልናውቅ ይገባል ሲሉ ከሽብር ጋር በተያያዘ በዜጎች ላይ የሚጻፈው ስም አሳሳቢና ብዙም የማያስጉዝ በሕዝቡ ብቻ ሳይሆን በአባላቱ ጭምር ተቃውሞ ያለበት የሕግ ሂደት መሆኑን አስምረውበት ዜጎችን በሃገሪቱ ወንጀለጫ መቅኛ ሕግ መክሰስ እየተቻለ በሽብር ሕግ ማንገላታቱ አደጋው የከፋ መሆኑን አስቀምጠዋል::የሕወሓት ባለስልጣናት ይህን ሃሳብ ቢያስከፋቸውም ራሳቸው በጠየቁት መሰረት ተጠንቶ የቀረበላቸው መሆኑ ታውቋል::

60 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የአለም ክፍሎች ተከራካሪ መንግስት አጥተው በየእስር ቤቱ እየማቀቁ ይገኛሉ:: እንዲሁም በተለያዩ የደህንነት የጨለማ ድብቅ እስር ቤቶች በርካታ ዜጎች ካለፍርድ ታስረው ይገኛሉ::የደህንነት አባላቱ በቡድን በመደራጀት ዘረፋ እና ግድያ ይፈጽማሉ:: በተጨማሪም ሽብርተኛ የሚለውን የማያሟሉ ዜጎች በየእስር ቤቱ በሽብር ስም ተከሰው መገኘታቸው ትልቅ ስጋት መሆኑ ተጠቁሟል::ይህ በደመነብስ አገር የሚመራው ሕወሓት መራሹ ጁንታ የመጨረሻው ሰአት ላይ መድረሱ ሲታወቅ በከፍተኛ ደረጃ የውጪ ሃይሎችን ይፈራል የመከላከያ ሰራዊቱ እንደማይዋጋለት ስለሚያውቅ ወደ ጦር ሜዳ አይልክም ሲሉ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን ሕወሓት ራሱ ያደራጃቸው የወሮበላ ሰራዊቶች የመከላከያ ልብስ በማልበስ ሕዝቡን እያስፈጀ መሆኑን ጠቅሰዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.