ስንቶች ተወጉ!? – አርአያ ተስፋማሪያም
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ረቡዕ ሀምሌ 2 ቀን 2000 ዓ.ም ልጄን ለከፍተኛ ህክምና ለማሳከም አገራችንን ለቀን ልንወጣ ተዘጋጅተናል። ኢየሩስ ዳግም እንድትወለድ ያደረጓትና ለህክምና የሚያስፈልገውን ከፍተኛ ገንዘብ ከጀርመን ግብረሰናይ ድርጅቶች ተሯሩጠው ያስገኙላት ክቡር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለመሰናበት ቤታቸው አመራን። ተንበርክኬ ጉልበታቸውን ተጠምጥሜ (ይህን ስፅፍ እንባዬ በጉንጩ ይወርዳል) አመስግኜና ጤናና ሰላም ተመኝተን ተለየናቸው። በመጨረሻ ቤቴን ለቅቄ ስወጣ ጓደኞቼ ሞልሽ፣ ጆኒና እናቴ እንዲሁም ኮሜዲያን አብርሀም አስመላሽ ነበሩ። አብርሽ በጉንጮቹ እንባው ይፈሳል። ጠጋ አለኝና መስቀል ያለው ማዕተብ ካስጨበጠኝ በኋላ <<በህይወት አታገኘኝም። ይህችን ከአንገትህ አትለያት! ሁሌም እንድታስታውሰኝ!>> አለና ማንባቱን ቀጠለ። ከእናቴም ጋር ተቃቅፈን ስንላቀስ <<ልጄ ተሰናበተኝ ...በህይወት አታገኘኝም>> አለችኝ። የሁለቱንም መርዶ በስደት ሰማሁ። ለሀዘኔ ቃላት የለኝም! የአብርሽ ማስታወሻ ዛሬም አንገቴ ላይ አለች። ልጄም አስቸጋሪና ከፍተኛ የቀዶ ህክምና በጨቅላ እድሜዋ 3 ጊዜ አደረገች። 3ኛው ቺካጎ ነበር የተከናወነው። አይሲስ ከፊት ያርድሀል። አንዳንድ የሀበሻ ዋልጌ ከጀርባህ ይወገሀል። ስንቶች ከጀርባ እንደተወጋችሁ ተረዳሁ። በበኩሌ በርካታ መልካም ሀበሾች በመኖራቸው ተፅናናሁ! ምትኩ፣ ዳዊት፣ አሌክስ፣ ዳኒ፣ የትነበርክ፣ ተስፉ፣ ኑራ፣ ቢኒ… ሁላችሁንም በአክብሮት አመሰግናለሁ! ትሰማለህ አንገቴ ላይ ያጠለቅኩት ጌጥ አይደለም! ክርስቲያን ነኝ!