የአሜሪካ ሴናተሮች “ኢትዮጵያ ውስጥ አለ” ያሉትን አፈና አወገዙ – VOA
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል።
የውሣኔ ሃሣቡን የያዘው ሰነድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን መግደላቸው በተገለፀበት በአሁኑ ሁኔታ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሃገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የገባውን የደኅንነት ውል መልሶ እንዲፈትሽ ይጠይቃል።
የሴናተሮቹ የውሣኔ ሃሣብ መግለጫ ሰነድ ረቂቅ (pdf) አክሎም የኢትዮጵያ መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉ የኃይል እርምጃዎችን እንዲያቆምና አጥፊዎች እንዲጠየቁ ያሳስባል። ያዳምጡ → listen