ከመስመጥ የተርፉት ኢትዮጵያውያን 11 ብቻ ናቸው፤ ሦስቱን አነጋግረናቸዋል – VOA
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሚስትና ልጁን ያጣ፣ እናትና ወንድሞቹን ውሃ የበላበት፣ እህቱን እና 28 ጓደኞቹን ያጣ ናቸው። ስላሳለፉት ጉዞ አስቸጋሪነትና ለመሄድ ስለተዘጋጁ ስደተኖች የሚነግረን ወጣትም ከግብጽ አነጋግረናል።
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ 500 ስደተኞች ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ እማኞችን አነጋግሮ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።
ከዚህ አደጋ የተረፉት 41 ስደተኞች በጣሊያን የባህር ሃይል ተርፈው ወደ ግሪክ ተሻግረው ነበር። የአውሮፓ ህብረትና የግሪክ መንግስት በአሁኑ ሰዓት ስደተኞችና ፍልሰተኞች በመበራከታቸው፤ ወደየሃገራቸው እንዲመለሱ ማዘዣ እየሰጡ ነው።
ሶሪያዊያንም ወደ ቱርክ ወደሚገኝ የስደተኞች ጣቢያሲመለሱ ቆይተዋል። ጽዮን ግርማ ከጀልባ አደጋ በህይወት ተርፈው ግሪክ ከገቡ መካከል ጥቂዎቹን አነጋግራለች። ያዳምጡ → listen