በደሴ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግል ጥሪ ወረቀቶች ተበተኑ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወጣቶች ትናንት ምሽት በተለያዩ የደሴ ከተማ አካባቢዎች የበተኑት ወረቀት የከተማው ህዝብ ትኩረት መሳቡን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወጣቶች ተናግረዋል፡፡ የትግል ጥሪ ወረቀቶች፣ ህዝቡ ለመብቱ እንዲነሳ፣ በወልቃይት ጥያቄ ዙሪያ የደሴ ህዝብ ጥያቄውን ከሚያቀርቡ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ጋር በጋራ እንዲቆም የሚያሳስቡ ናቸው፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ህዝብ በብዛት ይገኝባቸዋል በተባሉ ቦታዎች፣ በአራዳ፣ መናፈሻ፣ መላ፣ መናሃሪያ እና በዋና ዋና መንገዶች ወረቀቶች መበተናቸውንና ግድግዳዎች ላይ መለጠፋቸውን የሚናገሩት ወጣቶች፣ ጠዋት ላይ ፖሊሶች ወረቀቶችን ለማንሳት ሲረባረቡ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ወረቀቶቹ በበቂ ሁኔታ ለህዝብ ተዳርሰዋል ብለው እንደሚያምኑ የተናገሩት ወጣቶች፣ ዛሬ ድርጊቱን ሊፈ‹ሙ ይችላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች እየተያዙ በመታሰር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡የጸጥታ ቁጥጥሩም ከወትሮው በተለዬ ሁኔታ በመካሄድ ላይ መሆኑን አክለዋል