ሰበር ዜና:- አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ዲሲ ፍርድ ቤት ዉሉ። የወያኔ ተወካይ ባለስጣን ዓይነት ተቃውሞ አጋጠማቸው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሰበር ዜና:- አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ዲሲ ፍርድ ቤት ዉሉ።   

ሚያዚያ ት 4 ቀን 2008 ዓ.ም.  (April 12, 2016)

አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) በዛሬው ዕለት ዋሽንግተን ዲሲ  Office of Capital Reporting Services, 1250 I Street NW, Suite 350, Washington DC 20005 ከቀኑ 1:00PM ጀምረው የእምነት/ክህደት ቃላቸውን ሲሰጡ ዋሉ።

ምንም ኢንኳን የእምነት/ክህደት ቃላቸውን ለመልከት ባይችልም አባ መላኩ ወደ ቦታ ሲደርሱ የገጠማቸውን በአጭሩ የሚገልፅ ቪድዮ ይዘን ቀርበናል። አባ መላኩ ወደ ቦታው ሲመጡ 1 ሰው ብቻ የተከተላቸው ሲሆን እሳቸውን የሚቃወሙ በአካባቢው በመገኘት ያደረጉትን በቪድዮው ይመልከቱ።  አባ መላኩ ፍርድ ቤቱ ፊትለፊት ሲደርሱ የገጠማቸው ቪድዮ።

123

አባ መላኩ እንዳይታወቅባቸው የሚወዱትን የጳጳስ (አንዳንዴም የፓትሪያርክ ) ልብስ ለብሰው አልመጡም። ላለማስነቃት ሲሉ ቀለል ያለ የመለኩሴ ልብስ ለብሰው ነው የመጡት። ለማጣራት ባደረግነው ሙከራ ተቃዋሚዎቻቸውን ለመሸውድ መኪናቸውን ሌላ ቦታ አድርገው ሲመጡ ያገኗቸው ተቃዋሚዎች ድምፅ በመደናገጥ መንገድ ተሻግረው ሊሄዱ ሲሉ ከተቃዋሚዎች አንዱ አረ ወደዚህ ነው ብሎ ነገራቸው።

ሰሞኑን የአባ ፋኑኤል ደጋፊዎች ሊሆን አይችልም ዉሸት ነው ሲሉ ቆይተዋል። ደጋፊዎቻቸውም እንሰልፍላቸዋለን ሲሉ ተደምጠዋል። ነገር ግን ምንም አልታዩም። ምናልባት አባ መላኩ ተደብቀው ለማድረግና እንዲህ አይነት የፍርድቤት ጉዳይም እንዳልነበረ ልቅዱ ይችላሉ የሚል ግምትም ነበር። በርግጥ አድራጎታቸው ሲታይ ሞክረዋል። ይህ የመጀመሪያው የምርመራ (discovery stage) ስለሆነ አባ መላኩ ሌላ ሰው እንዲያቸው ስላልፈለጉ የተወሰኑ ሰዎች ገብተው ካዩአቸው በኋላ ኢንዲወጡላቸው በመጠየቃቸው ተቃዋሚ ሰዎች ትተዋቸው ወጥተዋል። ነገር ግን የአባ ፋኑኤል ፊታቸው እንዴት እንደደነገጡ ታይተዋል። አባ መላኩ ፍርድ ቤቱ ፊትለፊት ሲደርሱ የገጠማቸው ቪድዮ።