የኦሕዴድ 26ኛ አመት በኦሮሞ ሕዝብ ሰማእታት ላይ መሳለቅ ቀጥሏል:: ትግሉ ወደ ዝምታ ተቃውሞ ተቀየረ እንጂ አልቆመም::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : በሕወሓት ሚዲያዎች የኦሕዴዽ 26ኛ አመትን አስመልክቶ የምንሰማው ዘገባ ሁሉ የሕወሓት አገዛዝን ድድብና እና የአላዋቂ ሳሚነት እየገለጸለን ነው:;ትላንትና ለነጻነትና ለመብት በሕወሓት ጥይት የተገደሉ የኦሮሞ ልጆች ደም ሳይደርቅ አገዛዙ የመቀባጠሪያ ሚዲያዎቹ የሚለፈልፈው ዲስኩር መበስበሱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል::ትግሉ ወደ ዝምታ ተቃውሞ ተቀየረ እንጂ አልቆመም::በሕወሓት የሚመራው መንግስት እፍረተ ቢስ ነው አሁንም አይኑን በጨው አጥቦ የኦሮሞን ሕዝብ ለማሞኘት ደፋ ቀና ይላል:: የኦሮሞ ሕዝብ ዝም ሲል ሞኝ የሆነ መስሎት ከሆነ ሕወሓት አሁንም የቀድሞ ስህተቱን እየደጋገመ ወደ ገደል እየተመመ መሆኑን አይዘንጋ::የራሴን ሪፑብሊክ አቋቁማለውሁ ቀሪውን የኢትዮጵያ ክፍል መሳሪያ እያስታጠኩ አፋጃለሁ የሚለው አስተሳሰብ አይሰራም ሕዝቡ ነቅቷል:: ከኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት የሆነው ምሶሶስው ግንዱ የኦሮሞ ሕዝብ መሆኑ መዘንጋት የለበትም::ወያኔ የፈጠረውን የጎሳ ፖለቲካ ለአንድነት እና ለማቻቻል ፖሊሲ አጠጋግቶ ዘረኝነትን በብልህ የፖለቲካ ሲስተም ልክ ማስገባት እንደሚቻል በተግባር እየታየ ነው::

Minilik Salsawi's photo.

የኦሕዴድ 26ኛ አመት በኦሮሞ ሕዝብ ሰማእታት ላይ መሳለቅ ቀጥሏል:: የኦሕዴድን 26ኛ አመት አስመልክቶ የኦሮሞን ሕዝብ ለፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም በየትቋማቱ የሚደረገው ሩጫ መጃጃል ካልሆነ በስተቀር በፍጹም እውነታን አያንጸባርቅም::ወጣቱን ከትግል ያዘናጉ መስሎ ከታያቸው ተሳስተዋል:: ሕዝቡ ለውጥ ይፈልጋል ሕዝቡ ባለው አገዛዝ ላይ ጥርሱን ነክሷል::በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች የጥይት ሰለባ አድርጎ ቀብራቸው እንኳን በደንቡ እንዳይፈጸም አጉላልቶ በሺዎች የሚቆጠሩትን አካለ ስንኩል አድርጎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን የኦሮሞ ልጆች በእስር እያማቀቁ ሕጻን አዛውንት እርጉዝ ሳይቀር ገሎ አስሮ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ተጠያቂው አገዛዙ መሆኑን አምኖ ደግሞ በፖለቲካ አክሮባት ተቃዋሚ ሃይሎች ለመጠቋቆም ማቆብቆብ እብደት ነው::ትላንት ሕዝቡ ያሰማው ተቃውሞ ልክ ነው ሲባል ከርሞ ዛሬ የሕዝቡን ተቃውሞ የጸረ ሰላም ሃይሎች ረብሻ ብሎ መፈረጅ የምን ድድብና እንደሆነ አይገባንም::

የሚሰራውን የማያቀው እና እርስ በርሱ የማይነባበበው እያል የምንሸወድለት የሕወሓት መራሹ መንግስት አንድም ሕዝብን ለማደናበር ሲልም አዘናግቶ ተቃውሞን አፍኖ ለማስቀረት የሚጠቀምበት ስልት መሆኑን ልናውቅ ይገባል::ትላንት ጥሚው እንዲህ ብሎ ዛሬ ሚኒስትሩ እንዲህ አለ ከዛም ሃላፊዎች እንዲህ ይላልሉ እያልን የምንለው ነገር ራሳችንን ከማደናበር እና ከማሞኘት ውጪ ከሕወሓት መንደር የሚፈለሰፉ የማዘናጊያ እና የማስቀየሻ ሲልም አዙሮ ድባቅ መምቻ የፖለቲካ እሽክርክሪቶች እንደሆኑ ልናውቅ ይገባል::ሕወሓትን ማመን ቀብሮ ነው::ትግሉ ወደ ዝምታ ተቃውሞ ተቀየረ እንጂ አልቆመም:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬