በምስራቅ እዝ የሕወሓት ሰራዊት የጦር መሪዎች እና በበታች መኮንኖች መካከል ንትርኩ ከሯል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በምስራቅ እዝ የሕወሓት ሰራዊት የጦር መሪዎች እና በበታች መኮንኖች መካከል ንትርኩ ከሯል::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎EthiopianArmy‬ ‪#‎Ogaden‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬ ‪#‎Change‬

ተቃዋሚዎች ወደሰራዊቱ ዘልቀውለመግባት አለመቻላቸውናፍላጎት አለማሳየታቸው አንዱችግር ነው
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በጎዴ በሚገኘው የሕወሓት ምስራቅ እዝ ክፍለጦር የጦር መሪዎች እና በበታች መኮንኖች መካከል በስብሰባ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ አለመግባባቶች ተከስተው እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወታደራዊ የደህነት አባላት ለምንሊክ ሳልሳዊ አስታውቀዋል::ሃሙስ እና አርብ እለት እስከ ለሊት ግማሽ ድረስ በተደረገ ስብሰባ የበታች መኮንኖች የሕወሓት የጦር መሪዎችን ሲወነጅሉ እንደነበር ተጠቁሞ በከፍተኛ ደረጃ በሕገወጥ ግድያ እና የኮንትሮባንድ ስራ ላይ ተሰማርታችሁ ሰራዊቱን በስለላ በመጠርነፍ ከመረጃ በማራቅ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦና ችግር በመፍጠር ስለሃገሩ ደንታቢስ አንዲሆን በዘር እንዲቧደን በማድረግ ሰራዊቱን አደጋ ውስጥ ከመጣላችሁም በላይ ከመረጃ ይልቅ አሉባልታ በመንዛት እርስ በርሱና ከራሱም ጋር ወታደሩ እንዲወዛገብ አድርጋችሁታል በማለት ፈቃድ እና ስልጠና የሚሰጠው በዝምድና እና በቋንቋ መግባባት ላይ ነው::በማለት የበታች መኮንኖች ስለ ሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው መስተካከል ያለበት ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲስተካከን እና ከሰራዊቱ ለመሰናበት የሚፈልጉ እድሉ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል::

Minilik Salsawi's photo.

በደቡብ ምስራቅ እዝ ተብሎ የሚጠራው እና በሜ/ጄ አብርሃ(ከተር)የሚመራውሰራዊት የሕወሓት ሰዎች የሆኑ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች በጋራ እየተቀናጁ በከፍተኛ የኮንትሮባንድ ስራ ላይ መሰማራታቸው ከዚህ ቀደም የተጋለጠ ሲሆን በመርካቶ አከባቢ በኮንትሮባድ እቃዎች አዘዋዋሪነት እንዲሁም የሚያዘዋውሯቸውን እቃዎች መልሰው የፌዴራል ፖሊስ በመላክ የሚያዘርፉ እነዚሁ መሰሪ የሕወሓት የጦር መኮንኖችና ግብረ አበሮቻቸው መሆናቸውን ወታደራዊ ደህንነቶቹ ከዚህ ቀደም በሱማሊያ በኩል የገቡ እና መርካቶ የደረሱ ሞባይሎችን የተዘዋዋሪ ዝርፊያ አስታውሰው አስረግጠው ተናግረዋል::

በእዙ ውስጥ የሕወሓት ሰዎች ካልሆኑ በቀር ስልተናም ይሁን ፍቃድ በፍጹም ለማንም እንደማይሰጥ እንዲሁም ማንኛውም የሃገር ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ በተመለከተ መረጃ ማግነት የታገደ መሆኑን የጠቆሙት ወታደራዊ ደህነቶቹ በከፍተኛ ደረጃ በተሳሰረ ኔትወርክ አጅግ ከባድ ስለላ በወታደሮች ላይ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል::የሰራዊቱ የበታች መኮንኖች እና ባለዝቅተኛ ማእረግ ወታደሮች ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የመረጡት የአጠያየቅ ስልት ለየት ያለ እንደነበር እና በረጋና በሰከነ መንፈስ ቢሆንም ቁጣ እና አጉል የበላይነት የተተናወታቸው የሕወሓት የጦር መሪዎች ጉዳዩን ወደ ግጭት መሳባቸው ታውቋል::ተቃዋሚዎች ሰራዊቱ ውስጥ ዘልቀው ለመግባት አለመቻላቸው እና ፍላጎት አለማሳየታቸው አንዱ ችግር ነው::ያሉት መረጃ አቀባዮቹ በሃገሪቱ ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልግ አካል ሁሉ በተለያየ የትግል ስልት ወደ ሰራዊቱ እና ደህነቱ ዘልቀው መግባት እንዳለባቸው ተቁመው ከሕወሓት አባላት ውስጥ ሳይቀር የሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ የሚያሳስባቸው ቅን መኮንኖች መኖራቸውን ሳይጠቅሱ አላለፉም:: ስለመረጃው የመከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ደህነቶችን አመሰግናለሁ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬