የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች የክለቡ ቦርድ ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች የክለቡ ቦርድ ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ::
በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ስታዲይም የቡና ክለብ ደጋፊዎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ተቃውሞ ሲገልጹ አምሽተዋል::በቦታው የነበረ የቡና ክለብ ደጋፊ እንዲህ በጽሁፍ አስፍሮታል::
እግር ኳሳችን ባያድግም እንደ ኢትዮጵያ ቡና የመሰለ ደጋፊ ባለቤት መሆናችን ልንኮራ ይገባናል።
ኢትዮጵያ ቡና ከአደማ የነበረው የጥሎማለፍ ጨዋታ የኢትየጵያ ቡና ደጋፊዋች እጅግ ዲስፕሊን በሆነ መንገድ የቦርድ ኣመራር ከስራቸው እንዲለቁ ከዳር እስከ ዳር በህብረት ተቋውሞ ሲያሰሙ አምሽተዋል።
የኢትየጵያ ቡና ክለብ ሁኔታን ስመለከተው ከቦርድ ጅርባ የሆነ ኢትዮጵያ ቡና የሚባል ክለብ እንዳይኖር የሚፈልግ ኃይል ያለ ይመስለኛል። እውነት ለመናገር ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዋች ማለት የፅናት ተምሳሌት ናቸው።
በሀገራችን እግር ኳስ አለ ብለን በድፍረት እንድንናገር የምያነሳሳን አንዱ ይህ ውድ ዳር ተስፋ የማይቋርጥ የፅናት ተምሳሌት የኢትዮጵያ ቡና ድጋፊዋች ብየ አምናለው።
ስሙ ቄስ አይጥራው እና ዛሬ ከዳር እስከ ዳር እንዲሁም በየ 20 ደቂቃ ስሙ እየተጠራ ልቀቅልን እየተባለ የነበረ ግለ ስው እኔም መልቀቅ አለበት ባይ ነኝ።
ክብር ለኢትዮጥያ ቡና ደጋፊ!!!

Kinfegebriel Gyohaness