ትንሽ ስለ አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) አዋናባጅነት ከዜና ማህደራችን
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ናሽቪል፣ ቴኔሲ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከሰው ፍርድ ቤት እንደቀረቡ ባለፈው ሳምንት የዜና ሽፋን እንደሰጠነው ይታወቃል። አቡነ ፋኑኤል “ወያኔ ይገድለናል” ብለው ከአሜሪካ መንግሥት የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው የተፈቀደላቸው ቢሆንም፣ ከወያኔ ሹመትን ተቀብለው ወደ አሜሪካን ተመልሰው በመምጣት ወያኔን እያገለገሉ ይገኛሉ። አቡነ ፋኑኤል የጵጵስና ማዕረግ የሰጧቸውን የቀድሞውን አቡነ ጳውሎስን እንደሚቃወሙ ለሕዝብ አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ቃላቸውን አጥፈው እንደገና ተገልብጠው የአቡነ ጳውሎስ አገልጋይ በመሆን ወያኔንን እያገለገሉ ይገናሉ። አሁንም የአቡነ ማቲያስ በሰሜን አሜሪካ ተወካይ በመሆን አገልግሎታቸውን ቀጥለውበታል። እኝህ እንኳንስ ለጵጵስና የሚያበቃቸው ሥነ ምግባርና ባሕርይ ሊኖራቸው ይቅርና ተራ ምዕመን እንኳን ቢፈጽመው የሚያስነውረውን ክህደትንና ቀጣፊነትን የተላበሱ ለሃይማኖታቸው ሳይሆን ለስጋቸው ያደሩ የተከማ ጩሉሌ ናቸው። እኝህ ሰው 20 ዓመታት በላይ ሲያወናብዱና ሲያምታቱ መኖራቸውን በተለያየ ጊዜ በማስረጃ በማስደገፍ መዘገባችን ይታወሳል። እሳቸውን አስመልክቶ ከድምፅና ከጽሁፍ ማህደራችን ካጠናቀነው መረጃ መካከል ለማስታወስ ያህል በድጋሚ አቅርበንላችኋል።
http://www.mereja.com/amharic/46801
http://www.mereja.com/amharic/289096