ነጻነታችንን ለማስመለስ በመጀመሪያ ኢትዮጵያ ሁለት ዓይነት በሽታዎች እንደያዟት መቀበል አለብን
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ከአብይ ኢትዮጵያዊ
ነጻነታችንን ለማስመለስ በመጀመሪያ ኢትዮጵያ ሁለት ዓይነት በሽታዎች እንደያዟት መቀበል አለብን
በቃ! ለሥጋ ደዌ ሲሆን፤ ንቁ! ደግሞ በርኩስ-መንፈስ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።
ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫፥ ቁጥር ፯
“ቡዳና ከሃዲ ካልተተፋባቸው:-
ድፍን አገር ያውቃል አይረክስም ጅኒያቸው::”
ይህን የደዌ በሽታ ግኝትን ርዕስ ለምን መረጥኩት?ለምንስ ኢትዮጵያችንን ከደዌ በሽታ ምርምር ጋር አያያዝኳት?ምክንያቱም የበሽታዋ ግኝቶች በመርምር እና ጥናት ላይ ስለተመሰረቱ።ሥራዎቹ ከጥፋት ይልቅ ለልማት፤ከክፋት በተሻለ ደግሞ ለበጎ ተግባር እንደሚውሉ በደምብ አድርጌ ስለማውቅ ነው።በመንፈሳዊ ጉዳዮችም ያሉትን ስናይ:-በየቤተክርስቲያን እና በየመስጊዶቹም ሆኑ በዕምነት ተቋማት የምናያቸው ፈተናዎች ድብቅ አይደሉም።
ኢትዮጵያ አገራችን ለዘመናት በመታመሟ እና ሐኪሞቿ(በጎ አሳቢ ምሁራን ዜጎቿ) ለማከም ቢጥሩም (በክፉ አሳቢ ምሁራን ደግሞ) እንዳትታከም በመደረጓ እነዚያ (በሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ የተፈጠሩት የሰባ አመታት ችግሮቿ እየተባባሱ)የያዟት በሽታዎቿ ዛሬ ነቀርሳ እና ደዌ ስለሆኑባት ነው።አንዳንድ የሥጋ ትል የሆኑባት ኢትዮጵያውያንም ቢሆኑ “ማነው ኢትዮጵያ ታማለች የሚለው?”በማለት ሽንጣቸውን ገትረው አይናቸውን በጨው አጥበው እንደትል በቃላት ክርክር ይቦረቡሯታል። ከዚሁ ጋር ሁለት ዓይነት ዜጎች ያሏት ኢትዮጵያ አገራችን ከጣሊያን ሽንፈት በኋላ እሷን ለመጥቀም ወይም ለመጉዳትየተሰለፉ መኖራቸውን ማጤን ይገባናል።እነሱም “በግልፅ በሽታዋ ይነገር፤ ይታወቅ፤” የሚሉ እና “በፍፁም አይነገርም፤ አልታመመችም፤” የሚሉ ናቸው።እርስዎ በየትኛው በኩል ነው የቆሙት?።የሚያሳዝነው እንደጀርሞቹ ሁሉ፣ በዲባቶዎች (ዶክተሮች)ውስጥ፣በተቃርኖ ስላሉ፣ ገዳይ ዲባቶዎች መኖራቸውና ለጥቅማቸው ሲሉ ያዩትን እንዳላዩ ሆነው፤”ኢትዮጵያ በሽታ አልያዛትም” ማለታቸው ነው። ብታምኑም ባታምኑም በኢትዮጵያ ነፃነት የደዌ በሽታዋ የትግራይ ጉጅሌ መሆኑ ፀሀይ የሞቀው አገር ያወቀው፤መረጃ የሚቆጠርለት፣ምስክር የሚቀርብለት፣ታሪክ የተጻፈለት ብዙ የተባለለት የፋሺሽስት ሴራ ነው። ለመሆኑ ክርስቶስን የሰቀሉት ሮማውያን ስለክርስትና ዕምነት ተቆርቋሪዎች ያደርጋቸው ማነው?በእኛ ትውልድ ዳግም የ’ከደሙ ንፁህነኝ፣እጃቸውን ለመታጠብ በተለይም ኢትዮጵያን ለመያዝ ዘመናት እየቆጠሩ የሚመላለሱት ለምን ይሆን???
በሽታዎች ሁሉ የሚመጡት ከጀርሞች፣የሚወገዱትም ደግሞ በጀርሞች ሲሆን፤ግዴታችንም ሆኖ፣እኛም የሰው ልጆች የምንኖረው ደግሞ ከጀርሞች ጋር ነው።ጀርሞች ሁለት አይነቶች በመሆናቸው የጠቃሚነታቸውን ያህል የጎጂዎቹ ጀርሞች ልዩነት በሕላዌ ባሕርያቸው ተረጋግጧል።በሌላ በኩል ያኔ ነቢዩ ዕንባቆም የታየው የኢትዮጵያ ሸክም ትንቢት ሆኖ ይነገር እንጂ በዘመናችንም በግልጽ እየተፈጸመ ይገኛል።
እናም የዘመናችን ፈላስፎች ምሥጋና ይግባቸውና ዲባቶ (ዶክተር) ሉዊስ ፓስተር እና ዲባቶ(ዶክተር) ሮበርት ኮች የተባሉ የምርምር ሰዎች እስከ ፲፰ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የሳይንስ ሊቃውንት ሳያዩዋቸው በምልክታቸው ብቻ ያጨቃጬቋቸው የነበሩትን የበሽታዎች ግኝት፤ በአጉሊ መነፅር መገኘት ምክንያት በአይናቸው ሐቁን እንዲያዩ እና ምርምሮቹን ከመላ-ምት አውጥተው በገሃድ በሽታዎቹ ራሳቸው እንዲመሰክሩ አድርገዋቸዋል።በዚህ ሐቅ መሠረት እኛን የሰው ልጆችን ሁሉ በውጤቱ ረድተውናል፤ምንም እንኳን የምርምራቸው ግኝት የርኩስ-መናፍስትን በሽታዎች ለማየት የማያስችሉ ቢሆኑም።
ይሁንና ኢትዮጵያውያን ግን ከእግዚአብሔር ከራሱ የተሰጣቸው ፀጋ እና በረከት አለና(ለዚሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መረጃዎቿ ሰፍረዋል።ትንቢተ አሞጽ ምዕ ፱ ቁ ፯ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር፡፡ እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?)እሷን የሚሿት ሁሉ ያገኟታል። ምክንያቱም በአይን የሚታየውም ሆነ የማይታየው ረቂቅ በሽታ በምርምር በአጉሊ መነፅር እንደሚገኝ ተረጋግጧልና ነው።ይሁንና የርኩስ መንፈስ በሽታ ግን የተለየ በመሆኑና ከኢትዮጵያውያን መካከልም በእርኩሰ-መናፍስት ጭምር የተያዙ በመኖራቸው ለዚህ መፍትሔ ደግሞ የአጉሊ መነፅር ሳይሆን ከጥንትም ጀምሮ በታደላት መለኮታዊ ኃይል እና በረከቶቿ እየተፈወሱ ይገኛሉ።ይህን ሥጦታ ተመራማሪዎችም ያልደረሱበት በመሆኑ ለዚህ ችግር ደግሞ በመፍትሄነት ኢትዮጵያውያን(ኤፌሶን ምዕ ፮ ቁ ፲፪ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ) ከመጽሐፍ ቅዱስ በስተቀር ሌላ አማራጭ አይሹም።
በሌላ በኩል ግን የትግራይ ጉጅሌን ደዌነት በአይናችን ፍጹም እንዳናይ በነገር ሲሙለጨለጩና በደረቅ ቃላት ሲለፋደዱ ይታያል። እንደጀርሞቹ ባሕርይ ተከፋፍሎ:- ማለትም ቫይረስ እና ባክቴሪያ በሽታ ከሚባሉት የሚመደቡ አሉ፤በአንፃሩም ደግሞ ፈንጊ፣ፕሮቲስቲ እና ፕሪኦንስ ተብለው በጀርም ውስጥ በተጨማሪነት የሚጠቃለሉ አሉ፤እንደዚያ መልኩን እየለዋወጠ፣ ባህርዩን እያመሳሰለ፣እየተጠቀለለ፣ እየተዘረጋ እየተዳቀለ፣ እየተጥመለመለ፣እየተገለባበጠ አስማት እስኪመስል ሕዝቡን ግራ የሚያጋባ ፍጡር ነው።ከመነሻዬ እንደገለፅኩት ስለጀርም ዝርያዎቹ ለማውሳት ሳይሆን፣ (እኔ ከምገልፀው ይልቅ በበለጠ ዲባቶዎቹ እና ምሁራን በደምብ አድርገው ያብራሩታል።)የተነሳሁበት ዋናውና አቢይ ጭብጥ ግን የኢትዮጵያ ነፃነት በደዌ በሽታ መታመሙን ሲነገረን በዜግነታችን ምን እያደረግን እንደሆነ ለማመላከት ነው።በመሆኑም ታሪክ የኢትዮጵያ ነፃነት በሽታ እንደነበረና ዛሬ ግን ደዌ ወይም ነቅርሳ የሆነባትን ሐቅ ደግሞ ከታሪክ እንመልከት።
በመሠረቱ ነቀርሳ ወይም ደዌ በአካላችን ላይ ወይም በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠርና ቢያንስ የመቶ ዓይነት ጀርሞች በደማችን ውስጥ መገኘት ነው እናም በቀጥታ የሚገድሉን ቆርጠን ለማውጣት በማንችልበት አካል ውስጥ ከተፈጠሩ ብቻ ነው።ስለዚህ አሁን ካለንበት ትውልድ ጀምሮ ስንመለከት የኢትዮጵያ ነፃነት-ደዌ በሽታ መሆኑን መጀመሪያ በይፋ ያረጋገጡት ዲባቶ ብርሃኑ ነጋ እና የትግል ጓዱ አርበኛው አንዳርጋቸው ፅጌ ናቸው።
በትዕግስት ጠብቀው የጉጅሌዎችን ባሕርይ በሕሊና ማጉያ መነፅራቸው በጣም ተጠግተው በመርመር ያለምንም ሐፍረት{“ንጉሱ ራቁታቸውን ናቸው”እንደአለች ሕፃን} በአደባባይ በድፍረት”የኢትዮጵያ የነፃነት በሽታ፣በጉጅሌው ሴራ የደዌ በሽታ ሆኖባታል” በማለት ከረዳቱ አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር በድፍረት በይፋ ያጋለጠው ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ነው።ብዙ ዶክተሮች የኢትዮጵያ ነፃነት በበሽታ እንደታመመ ይመኑ እንጂ፣ደዌ(ካንሰር)መሆኑን አፍ አውጥተው የመሰከሩ የሉም። የሚያስድስተው ደግሞ በደዌ መታመሟን ብቻ ሳይሆን በአመፅ ቆርጦ ከማውጣት በስተቀር መፍትሄ የለውም ብለው በሙሉ-ልብነት ከነቁርጥ-እርምጃው አስቀምጠውልናል።ሲገልፁም የበሽታዋ ምክንያት ደዌም በመሆኑ ለጤናዋ በመስጋት ሁሉም እንደተቻለው መድኃኒት እንዲያፈላልግና የፈለገም ጠበል ያስረጫት አሊያም ቅጠላ-ቅጠል ወይም ሥራ-ስር እንዲፈልጉላት ብለዋል።በዕውነቱ የያዛት ደዌ ስለሆነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ደግሞ ኦፕሬሽን አደርግላታለሁና ደዌዋን ቆርጬ አወጣዋለሁ ብሎ የአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌን በአጋርነት ይዞ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ትግሉን አቀጣጥሎታል።
አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌማ፣ዕድሜውን ሙሉ ከአያቶቹ የነፃነት አርበኝነቱን በንቃተ-ህሊና የተረከበ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣አለቃ ሳይፈልግ ምቾት ሳያታለው፣ጉጅሌዎችን ከውስጣቸው ያውቅ ስለነበረ እንደጦር ነበር ይፈሩት የነበረው፤ዛሬ ግን እሱ በአረቦቹ ተሽጦ ጉጅሌዎቹ እጅ መብረቅ ሆኖ ወደቀላቸው።”እስኪ ትበላት!!!አያ ጅቦ”እንደተባለው ሆኖባቸውና ፈረንጁ የጉጂሌዎች ጌቶቻቸውን ትዕዛዝ ይጠብቃሉ።
እኚያ ሰባዊነት የማይለያቸው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስም ቢሆኑ አፈሩን ገለባ ያድርግላቸውና:-በእጃቸው እሳት ሆነው ስለወድቁላቸው ነው በየዋህነት ነብሳቸውን ይማርልንና ያወቁትን በማሳወቃቸው “አውቆብናል” ብለው የገደሏቸው።እሳቸው ያኔውኑ ኢትዮጵያ ወደቀዶ ጥገናው በአስቸኳይ እንድትገባ ምርመራ ይደረግላት ዘንድ ተማጽነዋል።በደዌ መያዟን አረጋግጠው አልገለፁም(ዶክተር ብርሃኑ ነጋና አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ በአሲምባ የትግል በረሃ ውስጥ ጉጅሌን ያውቃሉና)እንጂ የኢትዮጵያ ነፃነት በሽታዋ ደዌ ሊሆን እንደሚችል አፅንዖት ሰጥተዋል።በዚህም የሐቅ ንግግራቸው(ምክንያት ሰይጣንን ድንገት እንዳየ ሰው)በእጅ አዙር ግድያ እስር ቤት ውስጥ በበሽታቸው ታፍነው እንዲገደሉ በመደረግ ወንጀል ነው የተፈፀመባቸው።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም ቢሆኑ የታሪክ መዝገባቸውን ከወገኖቻቸው ጋር አጭቀው ከወጣት ምሁራን ጋር በመሆን አቅማቸው የፈቀደውን ያህል ባደባባይ እየተንከራተቱ ከውስጥ ሆድ-አምላኩ ምሁራንን እና ምድረ-ፈረንጅን ከጥቅም እጋሮቻቸው ጋር የጥቅም-መግቢያ በማሳጣት በኢትዮጵያዊነት ሥም ታግለዋቸዋል፤ተሟግተዋቸዋል።ሌሎች ምሁራንና ፕሮፌሰሮችም ነበሩ በሽምግልና ሥም እየተልመጠመጡ፤ይህን ዓይነት የነፃነት በሽታ አቅልለው በሽታዋ የደዌ ሳይሆን የጉንፋን ዓይነት ነው በማለት በፕሮፓጋንዳና በባዶ-ተስፋ ይከስማል ይሉን የነበሩ የፋሺሽቱ ጉጅሌ ሹማምንታት የነበሩ።
ድንክዬውም የገና አባትን የመሰለው እና እንደየገና አባት ማጭበርበርን የተካነው *ቱኒው* (ትርጉሙን”በጦርነት ላይ ጓደኛውን አጋልጦ ትን ብሎ የሚሸሽ፣ፈሪ፣ቶስቶአሳ….”ከሳቴ ብርሃን**:- ይመልከቱ።) ወቸገል-ዜናዊ የትግል አጋሮቹን ገድሎ እና አስገድሎ ሥልጣን የጨበጠው በሌለው ዕውቀት :በተንኮሉ ብቻ ሲሆን፤ከሕዝብ ባዘረፈው የትጥቅ ብረት እየተኩራራ በትዕቢቱ አብጦ የፖለቲካ ዶክተር ነኝ ብሎ ነበር።
እነ ታጋይ ገብረ መድህን አረዓያ የኢትዮጵያ ሐቀኛ አባቶች ሲያጋልጡት ግን፤*ቱኒው* ዜናዊ ያኔ እንደገባ ኢትዮጵያን በባንዳዎች መቀስ እየቀደደ፤በቻይና፣ በኮሪያና በሩሲያ አምባገነንነትን አብዮታዊ መርፌ እየወጋ፤በስደተኝነት ሕይወቱ በእንግሊዝ አገር ያየውን የዘርኝነት ልሳን”እንኳን ከወርቅ ዘር ተፈጠርኩ፤” እያለ አፉን በትዕቢቱ ከፍቶ ራሱን አዋርዷል።ልዋጭ-ልዋጭ ሲልበት የነበረውንም የሸበጥ ጫማውን ገና ሳያወልቅ ቁንጮ እንዳማረው ላይመለስ ከእነኮዳ-ቀዳዳ የፈሪ-ሥሙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ እንደኮነነው እና ትውልድ እንደረገመው ሊወሳ ባደባባይ ተቀጭቷል። በግድያው የተሰማሩት የባንዳ ልጆች ግን እነሆ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያን እያደሟት ያጣችውን ነፃነት ወደደዌ በሽታ እያባባሱባት ወደ መላ አካሏ ለማሰራጨት ደፋ ቀና ይላሉ። ለዚሁም በመለስ ጣዕረ-መንፈሱ ተለክፈው የኢትዮጵያን ነፃነት በደዌ በሽታ መ-ያ-ዝ የሚክዱ፤ከደሞዛቸው በተጨማሪ ለለዘብተኝነታቸው ምንዳ እየተከፈላቸው በምቾት የሚኖሩ ምሁራን ሞልተዋል።
ካህናት እንኳ ሳይቀሩ፣ኢትዮጵያ አልታመመችም፤ ጠበልም ሆነ ፆም ፀሎት አያስፈልጋትም፤ መድኃኒትም አያሻትም እያሉ በየገዳማቱ ያሉትን ባሕታውያንን ሳይቀር ደፍረው የኃጢያት ደሞዛቸውን ተቀብለዋል።ይህንን ሐቅ የካዱት ካህናት ከአባ ጳውሎስ ጀምሮ መለስን አስከትለው ከመቀጨት ጋራ እግዚአብሔር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ መናገሩን ንቀው የሃጢያት ደሞዛቸውን ስለጠየቁ ተከፍሏቸዋል።ለዚህ የመለኮት ውድመታቸው የተከፈላቸውን ደሞዝ በማጉያ መነፅር ማግኘት ወይም ማየት አይቻልም፤በዕምነት ብቻ የሚፈጸም ነው።ሐቁንም ለማየት በአባታችን መምህር ግርማ ወንድሙ “በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ሥም”በአደባባይ አጋንንትን እና እርኩሰ-መናፍስትን ሲያወጡ ማየት ብቻ ይጠቅማል።
በሌላ በኩል ደግሞ እነዚሁ ምሁራን ነን የሚሉን ሆድ-አደሮች የንዋይ ተገዥዎች በመሆናቸው ምግብ ተትረፍርፏል ሕዝቧም ጠግቦ ነው የሚያድረው ሲሉን፣ወጣቱ ከየሆቴል ቤቶቹ ጓሮ ትርፍራፊ ለመቃረም በወረፋ ሲጠብቅ፣በየቆሻሻ መጣያዎቹ መኪናዎች ጎማ ሥር ያለፍላጎቱ ሲወድቅ፣ በየአውራ መንገዶቹ ከየውሻዎቻቸው ጋር እንደሬሳ በየጥጋጥጉ ተጋድመው፤ያለመጠለያ በቁርና በጠራራ ጸሀይ ሲሰጣ፤አገሪቷም ሰላም ነች በሚሉበት አፋቸው፣የማጎሪያ ቤቶች እስር ቤት ተብለው በየቀኑ በድብቅ ሰዎች ተገድለው ደመ-ከልብ ሆነው ሲቀሩ እያዩ፤ ኢኮኖሚውም ተመንድጓል ብለው አፍ ሞልተው ይመሰክራሉ።እሺ! አደባባይ ይውጣና ለሕዝብ ይታይ ሲባሉ ግን እኛ በመንግሥትነታችን ሳንፈቅድ አይደረግም እያሉ ቢያንስ በዚህች ዕድሜ እንኳ ሃያ አራት አመታትን አስቆጠርን።
አንባቢዎቼ ሆይ:- ስለአገሩ የማይቆረቆር ዜጋ የለም።ኢትዮጵያ አገራችን የነፃነት በሽታ እንደያዛት የታወቀው የፋሺሽቱ አብራሪ (ፓይለት) ቲቶ ሚኒቲ በትዕዛዝ 26 ዲሴምበር 1935 (እ ኤ አ) ባዘነበው የጋዝ መርዝ በርሜልም አይደለም። አሊያም ቀ.ኃ.ሥ. በጦርነቱ ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት በወሰነው መሠረት የጠፋ ንብረት ማካካሻ ከጣሊያን ስለተከፈለን የ$250,000,000 የጣሊያን ክፍያ ካሳ የት እንዳስገቡት አለመታወቅ እና በ 525,000 ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ቤቶች መውደም ሥም ምክንያት ባልተከፈላቸው ኢትዮጵያውያኖች ገንዘብ ጉድለትም አይደለም።አልፎ ተርፎም በመጀመሪያው የጣሊያን ጦር ወረራ ማለትም ከ1895 እስከ 1896 (እኤአ) በዳግማዊ ምኒልክ አሸናፊነት በተጠናቀቀው የጦርነት ድል ጊዜ ሰበብም አይደለም።እንደውም የመጀመሪያው የጣሊያኖች ወረራ ሽንፈትማ ልዩ ስያሜ ተሰጥቶት፣ የአድዋው ድል በሚል ጣሊያኖች በገቡበት ቀዳዳ በኩል የተቀበሩበት ስያሜ አግኝቶ የጥቁር-ሕዝቦች ድል እንደሆነ በታሪክ ተመዝግቦ አልፏል።የኢትዮጵያ የነፃነት በሽታ የጀመራት ግን በሁለተኛው እና በመጨረሻው የጣሊያን የበቀል ወረራ ዋዜማ ጀምሮ ነው።
ሁለተኛው እና የመጨረሻው ኢትዮጵያ ከፋሺሽት ጣሊያን ጋር ያደረገችው ጦርነት ከ1935 እስከ1936 ለአንድ ዓመት ይቆይ እንጂ ከ”ኖቬምበር” 1934 ጀምሮ እስከ 1943 ድረስ የነፃነት ውጊያው ውስጥ ውስጡን በባንዳዎች ላይ ተፋፍሞ ባደባባይ ወጥቶ እንደተፋፋመ ለቅኝ ግዛት ማስፋፋት የጣሊያን ጦር ሲጣደፍ ተበትኖ ነበር።ኋላም እስከ 10 ፌብሯሪ 1947 የተረፉት የሞት ሽረት ደፈጣ ውጊያ እያደረጉ ኢትዮጵያ በረሓ ውስጥ ይቆዩ እንጂ አረንጓዴ፣ቢጫ እና ቀይ ሰንደቅ-ዓላማዋን ያላስወረደ ወረራ ነበር።እናም በአርበኞች የደፈጣ ውጊያ አፃፋ ምክንያት የጣሊያን ሰራዊት ጥሩምባውን አስነፍቶ ሕዝብ እንዳያስተዳድር እና የሐገር መሪ እንዳይሆን ከ 45,000 በላይ የሚበልጡ አርበኞች ውድ ሕይወታቸውን በስቅላት ገብረው ሰላም በማሳጣታቸው ጣሊያን በመንግሥትነት መቀመጥ ሳይችል ቀርቷል።በዚህም ምክንያት አገሪቷን ኢትዮጵያን ያዛት እንጂ ቅኝ አላደረጋትም ተብሎ በደም ተጻፈ።ስለሆነም በምንሊክ የተጠበቀው ነፃነቷ እንደፀና ባንዳዎችም ሆኑ የናዚ እና የፋሺሽት ርዝራዦች ወደዱም ጠሉም፤በተባበሩት መንግሥታት በደም ብዕር የታሪክ መዝገብ ላይ መኖሩን አረጋግጠዋል።
በዚህም ጠንካራ የታሪክ ትግል የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አስተዋፅዖ በግንባር ቀደምትነት ሲወሳ ይኖራል፤ይሁን እንጂ በነዚያ የስደታቸው ዓመታት የተዋጉት አርበኞች አስታዋሽ አጥተዋል።በጦርነቱ ወቅት ተጠቃሚዎቹ የባንዳ ልጆች ነበሩና ትምህርት የቀሰሙት የባንዳ ልጆች ብቻ በመሆናቸው አርበኞች ከነቤተሰቦቻቸው በባንዳዎች የቢሮክራሲው ወጥመድ ተወታተቡ።እነ በላይ ዘለቀን የመሳሰሉ በሺህ በሚቆጠሩ የድል አጥቢያ አርበኞች እየተተኩ :-ጀግናዎቹን ደግሞ እያሸሹ እንኳን ካሳ ሊከፈላቸው ይባስ ሰበብ እየተፈለገላቸው ባደባባይ ተሰቅለዋል።የተረፉትም የለማኝ ሕይወት ኖረው፣ታሪካቸው እንደ ጀግናው አብዲሳ አጋ እንኳ ሳይነገርላቸው በሜዳ ተበትነው ቀርተዋል።ያኔም”…የገደለሽ በላ።”እንደተባለ ዛሬም ድረስ የገድሏት ይበሏታል፤አሁንም የሚገድሏት ቀጥለውበት ሊበሏት ልጆቻቸውን በየፈረንጅ አገሮች የተሻለ ትምህርት እያስተማሯቸው ያሳድጓቸዋል።በየምርጫ ሰበብ የምናየው መራር-ትግል ይህንኑ የዘመናዊ ባንዳዎችን አፈጣጠርና የቀስበቀስ መደላደል ለማፈራረስ ነው፤የኢትዮጵያ ነፃነት የደዌ በሽታ መሆኑን አጥብቀን ስለምናውቅ።
ይህም የትውልድ ጥያቄ በመሆኑ አሮጌዎቹ የኢትዮጵያ ነፃነት ደዌ በሽታዎች ተቆርጠው እየተንጠባጠቡ ሲሞቱ፣የሚበላው እንዳጣ የደዌ በሽታ ራሳቸውን ሲያበሰብሱት የምናየው በዚሁ ምክንያት ነው።የኢትዮጵያ ነፃነት ደዌ በሽታ የሆነው የትግሬው ጉጅሌ ቡድን ግን አይታወቅበትም መስሎታል።የእነዶክተር ብርሃኑ ነጋን ዕድሜና ጤና ሰጥቶ ሲይቆይልን እነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ደግሞ ነፍሳቸውን በመንግሥተ ሰማያት የኢትዮጵያ አምላክ ያሳርፍላቸውና የነፃነት ደዌ በሽታዋን ቆርጦ ለመጣል በሁለ-ገብ የኢትዮጵያ አርበኞቹ፦በእነተከበሩት አቶ ገብረ-መድህን አረዓያ፣ዖባንግ ሜቶ፣አል ማርያም ጦማሪው፣ታማኝ በየነ፣ሻምበል በላይነህ አዝማሪው፣ዘላለም የለንደኑ፣በሌሎቹም ሁሉ ትግሉን ቢቀጥሉም በማጉሊያ መነፅሮቹ በሃቀኞቹ ጋዜጠኞቻችን፦ በእነ አበበ ገላው፣በእነ ርዕዮት ዓለሙ፣በነአበበ በለው፣በነደሳለኝ አማካኝነት በሚገባ አይተንዋል።ከእንግዲህ ሕሊና ያለው ዕውነቱን ለመፈለግ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እንዳለው እያንዳነዱ ኢትዮጵያዊ ለሁለ-ገብ ትግሉ ህሊናውን ያዘጋጅ።
እናም መጀመሪያ ነፃነታችንን በግድ እንዲያስረክብ የጉጅሌውን ቡድን በቃ ብለን ለመናገር ስንችል:-በማስገደድ አምርሮ መታገል ሲሆን፣እምቢታው በእሺታ ካልተለወጠ ነው፣ለማሽቀንጠር በብልሃት እና በልበ-ሙሉነት አምርረን የምንነሳው።መጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም ሥጋ መሆኑንም ማመን ሊኖርብን ነውና ከሁሉም በፊት ነፃነታችንን መንጭቀን ካልወሰድን ዋጋ የለንም። ከዚያም በኋላ እኛ እንደ እነርሱ የደዌ በሽታቸውን እንዳናዛምትና ሕዝብ እንዲዳኘን በግልፅነት መድኅኒት በጥበብ ችሎታ እንመራ።የኢትዮጵያ የደዌ በሽታዋ የግልፅነት አለመኖር ብቻ ነውና፤ያለበለዚያ ግን ግልፅነትን የሚፈራ ተሸፋፍኖ መኖርን ይፈልጋልና ሊትዮጵያ ነፃነት የደዌ በሽታ አዲስ ጀርም፣አዲስ ቫይረስ ወይም አዲስ ዓይነት ባክቴሪያ ተሸካሚዎች ሆነን እንቀርባታለን። ስለዚህ በግልጽነት ዲምክራሲን አምጥተን በሕግ የበላይነት እየተዳደርን አዲስቱን ኢትዮጵያን እንገንባ።