የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ውስጥ 2 ወጣቶች ለማምለጥ ሲሞክሩ ሞተዋል፣ 11 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ – VOA
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አስመራ ውስጥ ሁለት በብሄራዊ አገልግሎት ላይ የነበሩ ወጣቶች ባለፈው እሁድ ከተጫኑባቸው መኪኖች ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ በደረሰባቸው ጉዳት ሞተዋል ሲሉ የኤርትራ ማስታወቅያ ሚኒስቴር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገልጸዋል። ሌሎች ከመኪኖቹ ዘለው ለማምለጥ የሞከሩ 11 ወጣቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል ብለዋል። ፖሊሶች ጥቂት ጥይቶች ወደ ሰማይ በመተኩስ እንዲረጋጉ አድርገዋል ሲሉም አቶ የማነ አክለዋል።
የተለያዩ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ሬድዮዎችና ድረ-ገጾች ግን የሞቱት ወጣቶች ብዛት ከአራት እስከ 11 ነው ይላሉ።
የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከኤርትራ ባለስልጣኖች ምላሽ ለማግኘ ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካለትም።