አቡነ ማትያስ “ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” መሆናቸው ተረጋገጠ!
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
አቡነ ማትያስ “ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” መሆናቸው ተረጋገጠ።

የ ESAT አቶ ኤፍረም አሸቴ ቅለመጠይቅን ለማዳመጥ የሚቀጥለውን ይጫኑ።
ለ 30 ዓመታት ከኖሩበት ከውጭው ዓለም አቡነ ጳውሎስ በድንገት ሲሞቱ ወያኔ ጠርቶ የሾማቸው አቡነ ማትያስ ኢ.ኦ.ተ.ቤተክርስቲያን እውቋትም። አቡነ ማትያስ ብቃቱም እንደሌላቸው አሁን በይፋ መረጋገጡን ህዝበ ክርስቲያኑም ሆነ በተሾሙበት ወቅት የደገፏቸውና ምናልባትም ከአቡነ ጳውሎስም ይሻላሉ በሚል ቀቢፀ ተስፋ አሁን እውነቱን እየተረዱት መሆኑን ከአለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ የበለጠ ግልፅ ሆኗል።
ብዙ የተታለሉና የማይሆን ተስፋ አድርገው የነበሩ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ ከአባ ማትያስ የተሻለ ነገር የጠበቁበት ዋና ምክንያት አንዱ አቡነ ማትያስ አቡነ ጳውሎስን ‘ከፋፋይ ናቸው” እያሉ ይወቅሱ ስለነበር ነው። ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ አቡነ ማትያስን ለረጅም ጊዜ የሚያውቋችውና በሰፊው የፃፉ አባት ኢንደሚሉት፤ አቡነ ማትያስ ኢንደሰው ገር ናችው፣ ነገር ግን ጭንቅላታቸው ባዶ ስለሆኑ ከአቡነ ጳውሎስ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ይፈጥራሉ በማለት በተደጋጋሚ ፅፈዋል፣ ተናግረዋል። ታዲያ አቡነ ማትያስ ለምን ነበር አቡነ ጳውሎስን ‘ከፋፋይ ናቸው’ እያሉ ይወቅሱ የነበረው ለሚለው ጉዳዩን ስናጣራ ያገኘነው ምክንያት የሚከተለው ነው።
መለስ ዜናው ጫካ በነበረበት ጊዜ ለአቡነ ጳውሎስና አቡነ ማትያስ “ፓትርያርክነት እሰጥዎታለሁ” ብሎ በየግላቸው ቃል ገብቶላቸው ነበር። ነገር ግን መለስ ዜናዊ አቡነ ጳውሎስን መርጦ ሾመ። በዚህ የተናደዱት አቡነ ማትያስ ለብዙ ዓመታት ሲጋጩ እንደኖሩ ጉዳዩን በደንብ ከሚያቁ ሰዎች ለመረዳት ችለናል። እንደ ማስረጃ የሚሆነው አቡነ ማትያስ አሜሪካን ሊቀ ጳጳስ ተብለው በቆዩበት ወቅት ቁጥራቸው ከ10 የማያንሱ ኢትዮጵያ ባለው ሲኖዶስ የምመሮ በአሜሪካን የሚገኙ ቤተክርስቲያኖች በአቡነ ማትያስ ሳይሆን ቀጥታ በአቡነ ጳውሎስ ይመሩ ነበር። ይህንን ማንም ማረጋገጥ ይችላል።
በመጨረሻም አቡነ ጳውሎስ ሲሞቱ መለስ በገባላቸው ቃል መሰረት ሹመቱን እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
ቀሲስ አስተርአየ ደጋግመው እንደሚሉት የአቡነ ማትያስን ባህርዬ የሚያሳየው አቡነ ማትያስ ገና ከኢየሩሳሌም ሳይነሱ: “ፓትርያርክ ለመሆን ተጠርቼ ወደ ኢትዮጵያ ልሄድ ነው” ብለው የነግሯቸው የገዳሙ መነኮሳት በወቅቱ ተናግረዋል። ነገር ግን በወቅቱ ወያኔ መሾሙን የማስቆም አቅም እንደሌላቸው የተገነዘቡ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ አቡነ ማትያስን ለማግባባት ይቻል ዘንድ መልካም ነገር ስፅፉና በተለይም አቡነ ጳውሎስ ነጭ የለበሱ ነበር ግን ቀጥሎ የሚመጡት ፓትርያርክ (አቡነ ማትያስ መሆናቸው ነው) ጥቁር ነው የሚለብሱት እያሉ የፃፉም ነበሩ።
አሁን ዉሉ አድሮ ግልፅ የሆነው እስከአሁን የተደረገውን ለማስታወስና አንባቢ ግንዛቤ እንዲያደርግ በማለትጥቂት ነጥቦችን አንስተን ተያያዥነት ያላቸው ጽሑፎችን አንባቢመለከት እንጋብዛለን።
- አቡነ ማትያስ ብቁ አለመሆናቸው ብቻ ሳይሆን መጀመሪያ ጵጵስና በሰጧቸው በአቡነ ተከለሃይማኖት የተወገዙበትን ምክንያትና ዉግዘቱ ተነስቶም ከሆነ ለምን ለሕዝበ ክርስቲያኑ ሳያሳወቁ ተነስቶልኛል ብለው ተናገሩ።
- ስለ መወገዛቸውም ራሳቸው አቡነ ማትያስ የተናገሩትን ይመልከቱ። “መወገዙማ ደርግን አወገዝኹ እኔ፡፡ ደርግን ሳወግዝ የነበሩ ሰዎች እንዴት መንግሥትን ያወግዛል ብለው ፓትርያሪኩን አሳሳቱና አውግዘውኝ ነበር፡፡ በኋላ ስመጣ በስሕተት ነው ተብሎ አነሡት፡፡ የተወገዝኹት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ ነው፡፡ የተነሣው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስም ለቀው አቡነ ያዕቆብ ዐቃቤ መንበር በነበሩ ጊዜ ነው፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከመሾማቸው ጥቂት ጊዜ በፊት ነው ይኼ” (ምንጭ ሐራ ዘተዋሕዶ ሐራ ዘተዋሕዶ)
- አቡነ ማትያስ የወያኔ መጠቀሚያና ከአቡነ ጳውሎስም እጅግ የባሱ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዳከም እጅግ ለወያኔ ለጥፋት ዓላማ የተመቹ መሆናቸውን ማየት ይቻላል። ዶ/ር አረጋዊ በርሔ መፃፋቸው እንደወጣ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የፃፏቸው ጦማሮቸውን አንባቢ ያስተውል።
ጦማሮቹን ቀጥለው ይመልከቱ።
አቡነ ማቲያስ ከመሾማቸው በፊት የካቲት ፳፻፭ ዓ.ም. የተፅፈ: “ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ”
ቀጥሎም ሰኔ ፳፻፭ ዓ.ም. የተፅፈ: አባ ማትያስ “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም”
በጥፋት ጎዳና እንዳይቀጥሉም ሚያዚያ ፳፻፮ ዓ.ም. የተፅፈ: “ኢንሔሊ ተቃርኖተ ጽድቅ” “ከእውነት ጋራ የሚጋጭ ነገር እየሰራን ለሞኖር አንድፈር”