በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል – VOA


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ



በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ላይ ባለፈው እሁድ ተኩስ እንደነበር ታውቋል። በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ እንደከፈቱባቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጠቁመዋል። በተኩሱና ተያይዘው በደረሱ ጉዳቶች የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ በተለያዩ የተቃዋሚዎች ሚድያ እየተገለጸ ነው። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ስለሞቱትም ሆነ ስለቆሰሉት ሰዎች በነጻ ምንጭ ማረጋገጥ አልቻለም። ስለ ጉዳዩ ከኤርትራ ባለስልጣኖች ምላሽም ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም።