የጂንካ ምክትል አስተዳዳሪ ለሀሰት ውንጀላ እየተሯሯጠ ነው፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የጂንካ ባለስልጣን ለሀሰት ውንጀላ እየተሯሯጠ ነው፡ አቶ አወቀ አይኬ በጂንካ ከተማ እነ ዓለማየየሁ መኮንንን በሽብርተኝነት ፈርጆ የሚንቀሳቀሰው በዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አወቀ አይኬ የሚመራው ቡድን እስካሁን የሄደበት መንገድ ህገወጥና በምንም ማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ የፈጠራው ውንጀላ የሀሰት ምስክሮችን ለማዘጋጀት እየተሯሯጠ መሆኑ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጥቆማ አድርሰዋል፡፡
ለዚሁ ውንጀላ ይረዳቸው ዘንድ እነዓለማዬሁ ከመያዛቸው በፊት ሃሙስ ዕለት ምሽት በከተማው ውስጥ ቦንብ መፈንዳቱን እንደመነሻ በስፋት እስሰወራ መሆኑን ምንቾቹ አስታውሰው፣ በገንዘብና ጥቅማ ጥቅሞች የሀሰት ምስክሮች እየተመለመሉ ያሉት በከተማው አውቶብስ መናሃሪያ አካባቢ ከሚሰሩ የቀን ሰራተኞች እንደሆነና ምልምል የሃስት ምስክሮች በተሰጣቸው ጥቅም ከተስማሙ አዋሳ እንደሚወሰዱና በፈለጉት ቦታ እንደሚዝናኑ፣ ከፍተኛ የገንዘብ/መነሻ ካፒታል፣ የስራ ቦታና የገበያ ትስስር ድጋፍ እንዲሚደረግላቸው ቃል እንደተገባላቸው ለዚህ የታጩና የተገባላቸውን ቃል ያልተቀበሉ ወገኖች ገልጸዋል ፡፡
ምንጮቹ በዚህ መሰረት የሃሰት ምስክሮች ከተገኙ ለቀጣዩ የሚያዝያ 4/ 2008 ቀጠሮ ለማቅረብ እንደታሰበ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል የዞኑ ፖሊስ ከነዚህ ምልምል የሀሰት ምስክሮች( ከተገኙ) ቃል ለመቀበል ፍቃደኛ እንዳልሆነ፣ እንዲሁም በእነ ዓለማዬሁ እስር ጉዳይ በዞኑ ፖሊስና በእነ አቶ አወቀ ቡድን መካከል ልዩነት እንደተፈጠረና ልዩነቱን በማጥበብ ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የዞኑ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ኦህዲኅ/ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በእነ ዓለማዬሁ ላይ የተፈጸመውን ህገወጥ ድርጊት የሚቃወምና በዞኑ ያሉት ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊና ማኅበረ-ኢኮኖሚ ችግሮች በአሳታፊ መንገድ እንዲመረመሩ፣ በአካባቢው የግጭት አፈታት ዘዴ እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሄ እንዲቀመጥላቸው የሚጠይቅ ደብዳቤ ለማስገባት መወሰኑን የገለጸ ሲሆን ፤ይህ ባይሆን የተቃውሞ ሰልፍ ለመጥራት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ መረጃ የኦህዲኅ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ደግሞ እነ ዓለማሁ ከተያዙበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ መዋቅር በተጨማሪ ከተለያዩ የዞኑ ነዋሪዎች ጋር እየተገናኘ መረጃዎችን ሲያሰባስብ፣ የተገኙ መረጃዎችን ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጋር እየተገናኘ የድርጊቱን ህገወጥነት እያስረዳ ጉዳዩን በቅርብ እንዲከታተሉ እያሳሰበ ሲሆን ፣ በተጨማሪም ለሌሎች የተቃውሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ስለሁኔታው በማስረዳት አጥጋቢ የአጋርነት ድጋፍ እያገኘ መሆኑን ከድርጅቱ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል ፡፡