ከየቦታው እየተወሰዱ መድረሻቸው ያልተገኙ እስረኞች ጦላይ ወታደራዊ ካምፕ እየተንገላቱ መሆኑ ተሰማ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
#Ethiopia #MinilikSalsawi : – በአሁኑ ወቅት ከየቦታው እየተወሰዱ መድረሻቸው ያልተገኙ እስረኞች ጦላይ ወታደራዊ ካምፕ እየተንገላቱ መሆኑን የገለፀው ውስጥ አዋቂ ምንጫችን ከ2800 በላይ ሰዎች እንደምገኙ ስገልፅ ከወደ ሀረር የመጡ የ7 ልጆች እናት እንደምገኙበትም አስታውቀዋል።
ይህንን የህዝብ አፈና በበላይነት የሚያስፈፅሙት የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ በአቶ በዙ ዋቅቤካ እየተመራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የካምፑ ስራ አስተባባሪዎች
1) ቀነዓ ያደታ
2) ተሾመ ዱጋሳ
3) ፀሀይ ነጋሽ የኦሮሚያ ማረሚያ ኮምሽነር
4) የኦሮሚያ ፖሊስ ኮምሽንና የኦሮሚያ ማረሚያ ኮምሽን ከፍተኛና የመስመር መኮንኖችም በአስተባባሪነትና በፈፃምነት በከፍተኛ ደረጃ ተሳትፈዋል።
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ እና ስቭል ሰርቪስም በተሰጣቸው ድርሻ እየተሳተፉ መሆኑን ምንጫችን የገለፀ ሲሆን ታፍሶ የተሰበሰበው ህዝብ በከፍተኛ የምግብ፤ የመጠጥ፤ የጤና እና የማረፊያ ችግር ውስጥ መሆኑንም ስያብራራ ቤቶቹ የአራዊት ማረፍያ ሆኖ የቆየ፤ ምግቡ ደግሞ ረሀብን ለማስታገስ የማይችል እና ሁሉም ነገር ከምነገረው በላይ የከፋ መሆኑን ይናገራል።
ታሳሪዎቹ ከኦሮሚያ በተጨማሪ ከጋምቤላ፣ ከደቡብ ክልል እና ከበንሻንጉልም የመጡ ይገኙበታል። በዝህ ተግባር አፈፃፀም ላይ የትግራይ ተወላጆች በርቀት ከመቆጣጠርና ከማዘዝ ባለፌ እጃቸው በቀጥታ የማይታይ ሲሆን ሪፖርት የሚቀበሉና የሚያስተላልፉት እነርሱ መሆናቸውን ግን መደበቅ አይፈልጉም። ይህንን የአፈና የማንገላታትና የማሰቃየትን ተግባር የምንፈፅመው ለምንድነው የምል ስመት ያላቸው ፈፃሚዎች ባለመግባባት ከቀጠሉ ከፍተኛ ግጭት ልፈጠር ይችላል የምል ግምትና ፍራቻ መናሩንም ምንጫችን አልደበቁም። በጥቅት ቀናት ቆይታ ብቻ ብዙ እስረኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረም ምንጫችን ጠቁመዋል።