በሱልልታ እና በጅማ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ቀጥሏል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በሱልልታ እና በጅማ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ቀጥሏል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Sululta‬ ‪#‎Jimma‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎AddisAbaba‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የኣዲስ ኣበባ መግቢያ በሆነው የሱልልታ ከተማ እና በጅማ ዩንቨርስቲ ውስጥ ከፍተኛ የተማሪዎች የተቃውሞ ድምጾች መሰማታቸው ታወቀ፥የወያኔው ኣገዛዝ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እስር እና ኣፈና ቀጥሎ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በይቅርታ ሽፋን የሚሰሩ መንግስታዊ ሽብሮች በርትተዋል።ተቃውሞው ኣሁንም የወያኔ ኣስተዳደሮች ሊመልሱት ያልቻሉ ሲሆን በሃይል ተጠቅመው ወጣቶቹን መደብደብ ማሰር ተያይዘዋል።

በዚህም መሰረት ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የኣግዓዚ የሕወሓት ሰራዊት ኣባሎች የጅማ ዩንቨርስቲ ገብተው ተማሪዎችን በመደብደብ ከባድ ጉዳት ኣድርሰዋል፥በፎቶው ላይ የሚታየው ሕክምና አየተሰጠው የሚገኘው የጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነው፥ እንዲሁም በሱልልታ በርካታ ወታቶች የተደበደቡ ሲሆን ሰባት ተማሪዎች በወታደሮች ተይዘዋል ኣምስት ወንዶች አና ሁለት ሴቶች ሲሆኑ ወታደሮቹ ተማሪዎችን ሲያንገላቱ አና ሲያዋክቡ ተስተውሏል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.