በአዲስ አበባ ኮልፌ 18 ማዞሪያ አካባቢ በደረሰ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ 3 ሰዎች ሞቱ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በአዲስ አበባ ኮልፌ 18 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ጠዋት 3 ሰዓት ከ30 አካባቢ በደረሰ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ሶስት ሰዎች ሞቱ። በርካቶችንም አቁስሏል::
አደጋውን ያደረሰው ሲሚንቶ የጫነ ቱርቦ ከባድ ተሽከርካሪ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በስድስት ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ማድረሱም ተገልጿል። የተጠቀሰው ከባድ ተሽከርካሪ ከዊንጌት ወደ 18 ማዞሪያ አደባባይ እየተጓዘ ነበር።
እስካሁን በአደጋው ምክንያት ሶስት ሰዎች ሲሞቱ፥ ከ20 በላይ ሰዎችም ቀላል እና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።በተጨማሪም በአደጋው አደባባዩ ፊትለፊት የሚገኝ መድሃኒት ቤት፣ የሞባይል እና የቡና መሸጫ እንዲሁም የፑል ማጫወቻ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል።እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት በአደጋው ከተጎዱት መካከል 11 ሰዎች በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል፣ 11 ደግሞ በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ውስጥ የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። ኮልፌ 18 ማዞሪያ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በተደጋጋሚ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ከሚከሰትባቸው ስፍራዎች መካከል አንዱ ነው።