የኢትዮ ቴሌኮም የቫይበር የዋትስኧፕ እና መሰል አገልግሎቶችን በክፍያ እና በአገዛዙ ኔትወርክ ቁጥጥር ሊያደርግ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮ ቴሌኮም የቫይበር የዋትስኧፕ እና መሰል አገልግሎቶችን በክፍያ እና በአገዛዙ ኔትወርክ ቁጥጥር ሊያደርግ ነው:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthioTelecom‬ ‪#‎VoIP‬ ‪#‎Internet‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) አለማቀፍ የድምጽ ግንኙነት(የኢንተርኔት ስልክ)አገልግሎቶችን እንዲሰጡ በፈጠሯቸው የሶፍትዌር ካምፓኒዎች ለአለም ሕዝብ በነጻ ክፍት የሆኑት የቫይበር ዋትስኧፕ እና ተመሳሳይ የኢንተርኔት አገልግሎቶች በኢትዮጵያ በክፍያ ሊሆኑ መሆኑን የድርጅቱ ስራአስኪያጅ የወያኔው ሹም የሆነው አንዱኣለም አድማሴ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል::

እኛ እነዚህን የኢንተርኔት አገልግሎቶች ማገድ አንፈልግም ሆኖም ግን በኛ ስር አድርገን ቁጥጥር እያደረግን ክፍያ እንዲፈጸምበት መስራት ነው ሲል የወያኔው ሹም ገልጿል::ወያኔ የተለያዩ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ በኢትዮቴሌኮም ትቦነት በማስተላለፍ አስፈላጊውን የስለላ እና የአፈና ስራዎችን ለመስራት እንዲያመቸው ሲሆን ክፍያውም በተወደደ ኑሮ ሕዝቡን ለማንገፍገፍ እና እንዳይጠቀም ለማድረግ የታቀደ እኩይ ሴራ መሆኑ ታውቋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.