ሴሜቲኩ ጉራጌ የአማራ ነገድ ነው። አማራ ነው። (መሳይ መኮንን የኢሳት ጋዜጠኛ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Mesay Mekonnen – ሴሜቲኩ ጉራጌ የአማራ ነገድ ነው። አማራ ነው። (መሳይ መኮንን የኢሳት ጋዜጠኛ)
ዛሬ article መጻፍ ስላማረኝ ይህን ጻፍኩኝ። ገንቢ አስተያየታችሁን እቀበላለሁ።
መሳይ መኮንን የተባለ የኢሳት ጋዜጠኛ ከጻፈው በኋላ ባልታወቀ ምክንያት እንዳጠፋው ጽሁፉን የላኩት ገልጸዋል::
የጉራጌ እጣፈንታ
፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲፲
ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ብሔሮች አሉ። አብዛሀኛዎቹ በዞናቸው የየራሳቸውን ቛንቛ ይጠቀማሉ፤ ሲዳማ ሲዳምኛ፣ ሀዲያ ሀዲያኛ፣ ወላይታ ወላይትኛ ወዘተ… ጉራጌ ዞን ግን አማርኛን ይጠቀማል። ለመሆኑ ጉራጌዎች ይህን ያደረጉት ለአማራ ብለው ነው? “አማራ ንግዱን ሁሉ ስለተወልን እንደማካካሻ አማርኛ እንጠቀም” ብለው ነው? አይደለም!! በፍጹም አይደለም!!
ጉራጌ የሚባለው አካባቢ የብዙ ጎሳዎች ጥርቅም ነው። እነዚህም
>>መስቃን
>>ክስታኔ(አይመለል)
>>ዶቢ
>>ሰባት ቤት
>>ቀቤና
>>ማርቆ
>>ወለኔ
>>ስልጢ(እራሱን ከጉራጌ ስብስብ የገነጠለ)
ከነዚህ ውስጥ ማርቆ እና ቀቤና ኩሺቲክ ናቸው። ሴሜቲኮቹም የየራሳቸው ቛንቛ፣ ባህል እና ታሪክ አላቸው። ለምሳሌ መስቃን እና ክስታኔ የሚግባቡት በአማርኛ ነው። አንዳንዶቹም በዩዲት ጉዲት ጊዜ ከአክሱም ወደ ሸዋ ዝዋይ የተሰደዱ ናቸው። ብዙ ጊዜ የጉራጌ ዘፈን፣ አለባበስና ጭፈራ ተብሎ የምናየው የሰባት ቤቱን ብቻና ብቻ ነው። ለዚህም ይመስላል ወለኔ እና ቀቤና እራሳቸውን ከስብስቡ የማግለል ጥያቄ (ልዩ ወረዳ ለመሆን) እያቀረቡ ያሉት።
ከኦሮሞ መስፋፋት በፊት አማራና ሀዲያ ድንበርተኞች እንደነበሩ Paul Henze እና ኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ጽፈዋል። ይህ ማለት አሁን ጉራጌ የሚባለው አካባቢ የአማራ ደቡብ ምዕራባዊ ግዛትና አንጡራ ርስት ነው ማለት ነው። ሴሜቲኩ ጉራጌ የአማራ ነገድ ነው። አማራ ነው።
ሀያሉ ንጉሥ አፄ አምደጽዮን በ14ኛው ክ/ዘመን የአሁኑን ጉራጌ-አማራዎችን ከደዋሮ ሱልጣኔቶች አድኗቸዋል። አፄ ሱስኒዮስ ደግሞ በ17ኛዉ ክ/ዘመን ከጎንደር በራስ ስብሐት የሚመራ ተወርዋሪ ጦር በመላክ ከኦሮሞ ተስፋፊዎች የአሁኑን ጉራጌ-አማራዎች አትርፈዋል። “ጉራጌ” የሚለውን ስም መጀመሪያ የተጠቀሙት አፄ ሱሰኒዮስ ናቸው፤ በግራ አቅጣጫ ያለው ሀገሬ ለማለት ( ሰላምጌ፣ አምባላጌ፣ እቴጌ፣ አላጌ እንዲል)። አፄ ምኒልክ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ አገር ሲያቀኑ “አባታችን ወደኛም ኑልን፣ ድረሱልን” የሚል ደብዳቤ ከጉራጌ-አማራዎች እንደደረሳቸው ጳውሎስ ኞኞ “የአፄ ምኒልክ ደብዳቤዎች” በሚለው መጽሐፉ አስነብቧል።
ስለዚህ አሁን ጉራጌ የሚባለው አካባቢ የሚኖሩ የተለያዩ ጎሳዎች ከሦስት መቶ ዓመታት በፊት ጥርት ያሉ አማራ መሆናቸውን አውቀው ‘አማራ ነን’ ማለት ቢጀምሩ እውነት አላቸው። የአማራነት ሥነልቦና እና መጎናፀፊያ ቢላበሱ ያምርባቸዋል፣ ለወደፊቱም ዋስትና ይሆናቸዋል፣ የአማራ ነገሥታቶቻቸው መስዋዕትነትም በከንቱ አልቀረም ማለት ነው።