የፌደራል ፖሊሶች ባደረሱት ከፍተኛ ድብደባ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ህይወት አለፈ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአምቦ ዩኒቨርስቲ ግቢ የፌደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ባደረሱት ከፍተኛ ድብደባ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ህይወት አለፈ፤በዚህ ዓመት የተነሳውን የኦሮሞ ወጣቶች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተከትሎ በህዳር ወር መጨረሻ ላይ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ግቢ የፌደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ባደረሱት ከፍተኛ ድብደባከተጎዱት ተማሪዎች ሁለት የጎድን አጥንቶቹ ተሰብሮ የነበረው የሁለተኛ ኣመት የሳይኮሎጂ ተማሪ ወጣት ተክሌ ቶማ በትውልድ አካባቢው ዳውሮ ህይወቱ ማለፉን የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አሳወቁ፡፡

ተማሪው በደረሰበትከፍተና ድብደባ ህክምና ሲደረግለት ቆይቶ ብዙም ለውጥ ሊያሳይ ባለመቻሉ ወደ ቤተሰብ ወዳለበት
ዳውሮ ዞን ሄዶ ባለበት ነው ህይወቱ ያለፈው፡፡ ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲው መኪና መድቦላቸው ወደ ሟች ቤተሰብ ሄደው ለማጽናናትያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ እንደተደረገባቸውና በዚህም ተማሪዎች ሃዘናቸውን ከቤተሰቡ ጋር ለመካፈል እን ያለመቻለቸው ሃዘናቸውን ድርብ እንዳደረገው አክለው
ገልጸዋል፡፡

ይህ ተምሮ ለወግ ማዕረግ ይበቃልናል ብሎ ልጁን ወደ ዩኒቨርስቲ የላከ ቤተሰብ ይህ የምያደርሰውን የልብ ስብራት ምንም ጤናማ አዕምሮ ያለው የሚረዳው ነው፤ ለሟች ቤተሰብና ለጓደኖቹ መጽናናትን እንመኛለን፡፡