አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ተከሰው በዲሲ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
(አዲስ መረጃ ተካቷል ) መጋቢት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. (April 6, 2016)
ይህንን ጉዳይ እየተከታተልን አዳዲስ መረጃዎችን እናቀርባለን ባልነው መሰረት አሁን ለሕዝብ ማሳየት የሚቻለውን መረጃ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ጨምረናል። ሙሉውን የፍርድ ቤት የመጀምሪያውን ትዕዛዝ የሚቀጥለውን ሰንሰለት በመጫን ያንብቡ። (አቡነ ፋኑኤል ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የታዘዙበት የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ)
በአቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ፊታውራሪነት የሚመራው ”ዘመቻ አባ መላኩ” የተሰኘው አቀፍ ዘመቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ከበደ ያለ ፈተና ገጠመው። አቡነ ፋኑኤል የናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያ ው ሲኖዶስ እንዲገባ መደረጉን ተከትሎ በተነሳው ዉዝግብ ምክንያት የዘመቻው ፊታውራሪ የሆኑት አቡነ ፋኑኤል ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው። አቡነ ፋኑኤል ፍርድ ቤት ላለመቅረብ ብዙ ሲከላከሉ ቆይተው ጉዳዩ ስለከበደና መሄጃ ስላጡ በመጨረሻ በሚያዚያ ወር ፍርድ ቤት ሊቀርቡ መስማማታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ጉዳዩ አቡነ ፋኑኤል አስተዳድረዋለሁ የሚሉትንና በአሜሪካን ግዛቶች አገረ ስብከት ዉስጥ ብዙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በስራቸው ለማድረግ የሚደረገው ዘመቻ ተከትሎ የተከስተ ሁኔታ ነው። እንደሚታወቀው አቡነ ፋኑኤል ብዙ አዳዲስ ቤተክርስቲያን በመክፈት፣ ድርብ ታቦት በማደል፣ ሹመት በመስጠት ‘የግዛት ማስፋፋት’ ርምጃቸውን የወያኔ ታዛዥ ልሆኙት ለአቡነ ማትያስ አድናቆትን ሳያተርፉ እንዳልቀሩ ብዙዎች ይናገራሉ። ከአሁን በፊት እንደዘግብነው የአባ መላኩ የተሰጣቸው ትልቁ ግብ ስለሰባዊነትና ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚቆረቆሩትን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ማዳከም እንደሆነ ታውቋል። ይህ በተለይም በዲያስፖራ ያለውን ተቃውሞ እንዳይጠነክር ለማፈን የታለመ ዘመቻ መሆኑ በተለያዩ መረጃዎችና በሚደረጉት ተግባራት ለማወቅ ተችሏል። ለዘመቻው አፈጻጸም የተነደፈው ስትራቴጂው ሦስት አማራጮችን ጎን ለጎን አድርጎ መንቀሳቀስን ያካተተ ነው። እነዚህም፤
- ከተቻለ እያንዳዱን ቤተክርስቲያን በአባ መላኩ ቁጥጥር ስር ማዋል፣
- ካልተቻለ ደግሞ ሥርዓተ አልበኝነትን በማስፈን መበጥበጥ። በተለይ የጸረ-ወያኔን ጎራ በትርምስ ማወክና ስለወገኑና ስለ እምነቱ የሚቆረቆረው ሁሉ በተረጋጋ መንፈስ መኖር እንዳይችል ማድረግ ነው። ይሄ በአገር ቤት የሚደረገው አይነተኛ መገለጫው ነው። በአንድ ከተማ ውስጥ ሌላ ቤተክርስቲያን በተመሳሳይ ስም በየማዕዘኑ መክፈትና፣
የሚገርመው አቡነ ፋኑኤል የማይገባቸውን የፓትርያርክ ልብስ በመልበስ ከሌሎች ጳጳሳት በላይ መሆናቸውን ለማሳየት ቢሞክሩም ምንም አይነት ተቃውሞ ሲደርስባቸው አላየንም። ይህም ወያኔ ስራውን ስለሚሰሩለት ሊናገራቸው አልፈለገም። አቡነ ማትያስም ወያኔ ያዘዛቸውን ማስፈፀም እንጂ በውነት ለቆሙበት እምነት የሚያገለግሉ አለመሆናቸውን ደጋግመን ያየነው ስለሆነ እዚህ ላይ ማንሳት አያሻም። ምናልባት ባለፉት 4 ወራት በተለያየ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመሬታችን ተዘረፈብን ጥያቄ ዋልድባ ገዳምን ያስታውሱ። ወያኔ ዘርፎ ለስኳር ፋፍሪካ ምርት ማቅረቢያ ለማድረግ የዋልድባን ገዳም በግማሽ ወስዶታል።
የEthiopianreview ባደረገው ክትትል አቡነ ፋኑኤል የሚመለከት ከአገር ቤት ድረስ የሚዘልቁ መረጃዎችን አሰባስቧል። በቅርቡ መረጃዎቹን በዘገባችን እናቀርባለን።
ምናልባት አሁን ፍርድ ቤት የሚቀርበው ዝርዝር ሁኔታ አቡነ ፋኑኤል ‘ፓትሪያርክ’ የመሆን ምኞታቸውን ለማሳካት እጅግ የሚያስቸግር እንደሆነ መገመት ይችላል። አሁን ያላቸው አማራጭ ማንኛውንም ኃይላቸውን ከዚህ ክስ ሊያመልጡ የሚችሉበትን ሁኔታ መሻት ይሆናል። ነገር ግን የገጠማቸው ክስ በቀላል መንገድ መውጫ የሚያገኙበት እንደማይኖር የክስ ሁኔታውን ከሚያውቁት መረዳት ተችሏል። ከነዚህ አመልካች ነገሮች አንዱ የተከሰሱበት መነሻ የሆነው የናሽቪል ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም የአኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው ምእመኑ ያውቃል። እንደውም እባካችሁ ይቅርታ እንዲደራረጉ እያሉ የወያኔን ታክቲክ ለመጠቀም ቢሞክሩም ጉዳይ ጊዜ ስላለፈበት የፍርድ ሂደቱን መጠበቅ ብቻ ነው ያለው አማራጭ።