የቤንሻንጉል የቅማንት ይሁን የወልቃይት ሕዝብ ችግር የሚፈታው ሕወሓታዊ ፕሮፓጋንዳና ሕዝበ-ውሳኔ አይደለም::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የቤንሻንጉል የቅማንት ይሁን የወልቃይት ሕዝብ ችግር የሚፈታው ሕወሓታዊ ፕሮፓጋንዳና ሕዝበ-ውሳኔ አይደለም:: #Ethiopia #Amharaprotests #Welkait #Qimant #Benshangul
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) እያደር ጉድ ከሕወሓት ኩሬ ይተናል::ሕወሓቶች ስለቤሻንጉል ወልቃይትና ቅማንት ሕዝብ እያሞጠሞጡ ነው::የቤንሻንጉል ይሁን የወልቃይት ይሁን የቅማንት ሕዝብ ከትግራይ ክልል ጋር መሆን እፈልጋለሁ አለ እያሉ የሚነግሩን እኮ ሕወሓቶች ናቸው እንጂ ባለጉዳዮቹ ሕዝቦች/ተወላጆች አይደሉም:: ሕወሓት የምታቀርበው ሃሳብ የተቀደሰ ነው የሚሉ የኢዴፓ ሰዎች በወልቃይት እና ቅማንት ሕዝብ ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ ከመደገፍ እንደማይተናነስ ማወቅ አለባቸው:: ሕወሓቶች የወልቃይት ሕዝብ የቅማንት ሕዝብ የቤሻንጉል ሕዝብ የወሎ ሕዝብ ኧረ ስንቱ …እንበለው ..በሕገመንግስቱ መሰረት ከትግራይ ክልል መጠቃለል ከፈለጉ ሕዝበ ውሳኔ እንዲሰጡ የፌዴራል መንግስቱ ሊፈቅድ ይገባል የሚለውን አጀንዳ ሕወሓቶች ማራገብ ሲጀምሩ ኢዴፓዎች ደግሞ ማጨብጨብ ጀምረዋል:: የሚገርመው ደሞ የቤንሻንጉል ሕዝብ በትግራይ ክልል እንዲተዳደር ሕዝበ ውሳኔ ይስጥ የሚለው አዲሱ አስገራሚ የሕወሓት ሃሳብ ነው::ልንዋጋቸው ይገባል::
በመጀመሪያ ደረጃ ሕወሓት ይሁኑ ታማኝ ተቃዋሚው ኢዴፓ ማወቅ ያለባቸው ነገር ቢኖር ሁሉንም ዜጋ እኩል የምታይ ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚሰራበት ወቅት የግዛት አንድነት ለማስፋፋት የሚደረግ ሩጫ ተቀባይነት እንዳሌለው ነው::የሕወሓት ሰዎች ራሳቸው ወታደር ልከው የቅማንት ሕዝብ ወጥረው ይዘውት በአማራ ክልል ባለስልጣናት በተለይ በገዱ አንዳርጋቸው ማሳበብ ምን የሚሉት ባዶ የተበላበት እቁብ እንደሆነ አላወቁትም::ምንሊክ ሳልሳዊ የሕወሓት ካድሬዎች ስለ ቅማንት ህዝብ ወንዝ ተሻግረው ተከራካሪ የሆኑት ለምን አላማ ነው? የቅማንት ሕዝብ ከትግራይ ክልል ጋር መሆን እፈልጋለሁ አለ እያሉ የሚነግሩን እኮ ሕወሓቶች ናቸው እንጂ የቅማንት ተወላጆች አይደሉም::የአማራ ክልል ባለስልጣናት የዘር መጥፋት ወንጀል ያካሂዳሉ ብሎ የሚወነጅለው ራሱ ሕወሓት እንጂ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ዘሬን አጠፉብኝ ብሎ ክርክር የገጠመ የቅማንት ተወላጅ አላየንም::
ሕገመንግስቱን ፌዴራል መንግስቱ ሊተገብር ይገበዋል ይሉናል ሕወሓት እና አጨብጫቢው ኢዴፓ::ሕገመንግስቱ የሚተገበረው ሕዝብን ለመነጣጠል እና ለማጋጨት ነው? ስለ ሰብዓዊ መብት ሃሳብን በነጻነት ስለመግለጽ ስለ ነጻ ፕሬስ ወዘተ ሕገ መንግስቱ ይከበር ብለው ለምን አይከራከሩም? በቅማንት ብሄር ላይ በገዱ አስተዳደር የሚደርሰው ጭፍጨፋ ባፋጣኝ ቆሞ በገለልተኛ ወገን ሊጣራ ይገባል፡፡ የሚሉት ሕወሓቶች መጀመሪያ ራሳቸው በኦሮሞ እነ በኦጋዴን በጋምቤላ ሕዝብ ላይ ያደረጉት ጭፍጨፋ የት ደብቀውት ነው::የወያኔን ሴራ ለማሳካት የተፈጠረው ታማኝ ተቃዋሚው ኢዴፓም ለፓርቲዎች ድጎማ ይደረጋል ከተባለ በኋላ የቤንሻንጉል የቅማንት ይሁን የወልቃይት ሕዝብም ሪፈረንደም (ውሳኔ ሕዝብ) በማድረግ ቢፈልግ በትግራይ ክልል፣ ቢፈልግ በአማራ ክልል፣ ቢያሻው የራሱን ክልል መመስረት የሚያስችለው እድል ሊመቻችለት ይገባል፡፡ የሚል አዲስ ሃሳብ ይዞ መቷል::ይህ የትም አያደርስም ሕወሓት ይሁኑ ኢዴፓ የተፉትን ትፋት ሁሉ መልሰው ይልሷታል:: #ምንሊክሳልሳዊ #MinilikSalsawi
