ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ እዳ ይፈለጋል የተባለው የኦሮሚኛ ዘፋኝ አርቲስት ቀመር የሱፍ በጋዜጣ ተጠራ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ እዳ ይፈለጋል የተባለው የኦሮሚኛ ዘፋኝ አርቲስት ቀመር የሱፍ በጋዜጣ ተጠራ::

በኦሮሚኛ ዘፈኑ የሚታወቀው አርቲስት ቀመር የሱፍ ላይ የወያኔ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ እዳ ይፈለግበታል ብሎ ክስ እንደመሰረተበትና በአድራሻው ሊገኝ ስላልቻለ በጋዜጣ እንዲጠራለት በጠየቀው መሰረት የወያኔው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጋት ጋዜጦች ጥሪ እንዲደረግ ትእዛዝ በሰጠው መሰረት ጥሪ ተደርጎለታል::

ስለጉዳዩ የተጠየቀው አርቲስት ቀመር የሱፍ ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ እንጂ እኔ ባለፉት አራት አመታት ቋሚ አድራሻ ያለኝ ሲሆን አድራሻዬም ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 6 ቀበሌ 12/13 የቤት ቁጥር 419/2 ነው በማለት ውንጀላውን ተቃውሞታል::በመንግስት ጋዜጦች አድራሻው ንፋስ ስልክ ክፍለከተማ በሚል ጥሪ የተደረገለት ቀመር የሱፍ ከብርሃን ኢንሹራንስ ካምፓኒ ጋር በጋራ ክስ ቀርቦበታል::ስለ ጉዳዩ የተጠየቀችው ባለቤቱ አትሌት እጅጋየሁ ዲባባ እሷም ሆነች ባለቤቷ ስለዚህ ክስ የሚያውቁት ጉዳይ እንደሌለ እና ገና መስማቷ እንደሆነ ተናግራለች::
ባልና ሚስቱ ይህን ይበሉ እንጂ ክሱ የተመሰረተው በመስከረም 2008 እንደሆነ የፍርድ ቤቱ መዝገብ ያሳያል::

አርቲስት ቀመር የሱፍ ከወያኔ ጋር የፖለቲካና የኢኮኖሚ እከክልኝ ልከክልህ ቁርኝት በመፍጠር የወያኔ አገዛዝ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጭቆና እና ግፍ ወደ ጎን በመተው እንዲሁም የኦሮሞ እስረኞችን አያያዝ በተመለከተ በተቃራኒው የማስተባባያ ቃል በመስጠቱ ለኦሮሞ ሕዝብ ንቀት አለው በሚል በዲያስፖራ አክቲቭስቶች ይወቀሳል:: #MinilikSalsawi

ዝርዝር መረጃ :- http://addisfortune.net/articles/tax-authority-takes-singer-to-court-over-two-million-birr/