በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ እየሆነ ያለው በሰራተኞች አንደበት ሲገለጽ – ኢዮብ ዓለም —
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
‹‹ በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ እየሆነ ያለው በሰራተኞች አንደበት ሲገለጽ››// በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የህዳሴና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን (ከ 2002 እስከ 2007) በአገራችን ሊከናወኑ በዕቅድ ከተያዙ ሜጋ -ፕሮጀክቶች -እንደ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጄክቶች /የህዳሴው ግድብ የለበትም፣በድንገት የተጀመረ ነው/፣ የባቡር ትራንስፖርት መስመር ግንባታ / አልተጀመረም ማለት የሚቻል/ና ዕድሳት፣ የአዳዲስ ስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ግንባታና ማስፋፊያ ፕሮጄክቶች /አስር/ …ይገኙበታል፡፡በዚህ ጥናታዊ ዘገባ የምንመለከተው በመጀመሪያው ዙር የህዳሴና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ይጠናቀቃሉ የተባሉትን ግን በተግባር አንዳቸውም በሚፈለገው አቅምና ደረጃ ወደ ምርት ያልገቡትን አስር አዳዲስ ስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ግንባታና ማስፋፊያ ፕሮጄክቶች ን ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ሦስቱ / በደቡብ ኦሞ ዞን ይተገበራሉ የተባሉት / አለመጀመራቸውን በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡ከመነሻው ፕሮጄክቱ 30 ከመቶውን አልጀመረም ማለት ነው ፡፡ ለዚህ ጥናት የመረጃ ምንጭ የሆኑት የኢቲቪ/ኢቢሲ ሪፖርቶች፣ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ሰራተኞችና በተጠቀሱት ፕሮጄክቶች ላይ እየሰሩ ያሉ የአመራር አካላት፣ ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች ናቸው፡፡ ጥናታዊ ዘገባው በሁለት ክፍሎች የተዘጋጀ ሲሆን ይህም ከወራት በፊት የተዘጋጀው ክፍል አንድና በክፍል ሁለት የተገለጸው ሰሞነኛ መረጃ የቀረበበት ነው፡፡ መልካም ንባብ፡፡ ክፍል አንድ– ከዚህ በፊት፡- ሃሰትና ክህደት የማይታክተው ዘረኛው የህወኃት አገዛዝ በስኳር ኮርፖሬሽን- ያስከተለው መዘዝ፤ መቼም በተመራጫችን ሚዲያ /ኢሳት/ መታፈን ጾማችን ቀርቶ የኢቢሲ/ኢቲቪ/የአየር ጊዜኣችን በመጨመሩ የማንሰማው ጉድ የለም፣ ይህ ሃፍረትና ይሉኝታ የማያውቅ መንግስት በራሱ ዓይን እያየን በራሱ ሚዛን እየመዘነን አያስታውሱም በሚል እሳቤ እስከሚሰለቸን ውሸቱን እያቀረሸብን የ50ኛ ኣመት ልደቱን ይነግረናል፣ ወይ አለማፈር፣ ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባለልወጣሽ፡፡ በዚያ ሰሞን ኢቢሲ/ኢቲቪ በመስኮቱ ዘወትር በሚመግበን የተትረፈረፈ ምርት ከምንሰቃይበት ቁንጣን በተቃራኒ መርዶ አርድቶናል፡፡ በስኳር ዋጋ ላይ በአንድ ጊዜ ሦስት ብር ጨምረናል በማለት፡፡ አዲስ አበባ ላይ ብር 18.40 እንዲሸጥ መንግስት ፈቅዶልናል ብሏል ኮርፖሬሽኑ፡፡ በዚህ ላይ ከዚህ በፊት በመጀመሪያው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተነገረንን አስታውሰን ወደያዝነው መረጃ እንገባለን፡፡ እንዲህ ተብለን ነበር ‹‹ … አስር አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር ፕሮጀክቶችን ወደ ምርት አስገብተን እያደገ የመጣውን የሽኳር ፍላጎት በማሟላት ከውጪ ለማስገባት የምናወጣውን የውጪ ምንዛሪ ከማትረፍ አልፈን ወደ ውጪ በመላክ የውጪ ምንዛሪ ገቢያችን እናሳድጋለን …›› ፡፡ በዕቅድ ዘመኑ ማብቂያ ደግሞ ‹‹ እነዚህን ፕሮጄክቶች ለማጠናቀቅ ተጨማሪ የአምስት ቢሊዮን ብር ብድር ከመንግስት እንዲፈቀድለት መጠየቁን …›› ነግረውናል፡፡ ከዚሁ በተያያዘ በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ ቅጥ ያጣውን ሙስናና 800 ሚሊዮን ብር አየር -በአየር ደብዛው እንደጠፋና ለዚህም ተጠያቂው አቶ አባይ ፀሃዬ መሆናቸውን ፣የተኳቸው አቶ ሺፈራው ጃርሶም ‹‹…. ተብትቦና አሳስሮት ገድሎት በሄደው ቤት እንደምን ለአስከሬን ህይወት ዘርተን ልንሰራ እንችላለን…›› እያሉ ሲያማርሩ እንደነበር ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ሰምተናል፡፡ አሁን በአምባሳደርነት ‹እስከተገላገሉበት› ድረስ አንድም ቀን በሥራቸው ደስተኛ ሆነው እንዳልታዩና የከፍተኛ የሥራ አመራሩን ሰብስበው አነጋግረው እንደማያውቁ እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በቴዘ ስለማንኛውም የኮርፖሬሽኑ አቅጣጫ በቦርዱ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይገለጽ እንጂ ‹ቦርዱ› የሚባለው አካልም ሆነ ስለሚያደርገው ስብሰባ እንኳን ባለሙያዎች፣ዝቅተኛና መካከለኛ አመራር ቀርቶ የከፍተኛ አመራር አባላትም እንደማያውቁ የውስጥ ኦዲት ምንጮች አሳውቀዋል፡፡ ዛሬ በአፈና ውስጥ ባይሆን በዕለት ተዕለት በሚጠቀመው ምርት /ስኳር/ላይ የተደረገው ጭማሪ ህዝቡን ለተቃውሞ የሚያስነሳ ነው፡፡ በየቱም ጊዜ እንዲህ ያለው ጭማሪ መንግስት በሚያቀርበው የእለት ተዕለት መጠቀሚያ ምርት ላይ ተደርጎ አያውቅም፡፡ ሦስት ብር በኪሎ ለደሃው/ለህዝብ ከፍተኛ ነው፡፡ ውስጥ አዋቂ ምንጮቹ ‹‹ በጭማሪው ቢያበቃ ጥሩ ነበር፣ ከዚያ አልፎ ለጭማሪው የተሰጠው ምክንያትና ከአዳዲሶቹ ሦስት ፋብሪካዎች በዚህ ዓመት ምርት ይጀምራሉ በማለት ዛሬም የተስፋ ዳቦ ማቅረቡ በመልካም አስተዳደር መድረክ ስለ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሚያወሩበት ጊዜ መሆኑን ካለው እውነታ ጋር ስናየው እንደዜጋ በጣም ያማል ›› ሲሉ ምንጮቹ ምክንያታቸውን እንደሚከተለው ያቀርባሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የስኳር ዋጋ የተጨመረው ኮርፖሬሽኑ በሙስና የገባበትን የገንዘብ እጥረትና ከጠየቀውን የቢሊዮኖች ብር ተጨማሪ ብድር ከፊሉን ለመሸፈን ካልሆነ በቀር የስኳር ማምረቻ ዋጋ በኪሎ በየቱም ፋብሪካ ከ 7/ሰባት /ብር አይበልጥም፣ እንደኮርፖሬሽኑ የማምረቻ አማካይ ዋጋ ስሌት ከዚህ በታች ነው ይላሉ ፡፡ ስለዚህ ማንም ጠያቂ በሌለበት ቢያንስ እኛን የምናውቀውን ባያከብሩ እንኳ እንደሰው ሊያፍሩን በተገባ ፣ የህዝብ አካል መሆናችን በተረዱ ነበር፤ ሲሉ በቁጭት ይናገራሉ፡፡ ይህን ኃሳባቸውን በመረጃ ሲያጠናክሩም ፡- አቶ ሺፈራው ያነሱት የነበረውን የተተበተበ መዋቅርና በቅርቡ በኮርፖሬሽኑ የመልካም አስተዳደር ስብሰባ ላይ የተነሱትንና በከፍተኛ አመራሩ መካኪል በግልጽ ያለውን ልዩነትና የአሰራር ዝርክርክነት ያቀርባሉ፡፡ ስለመዋቅሩ ካነሳን ‹‹ማንም ወደ ኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት የሄደ ሰው ፣ መቀሌ ያለና የሥራ ቋንቋውም ትግርኛ ቢመስለው አይፈረድበትም፡፡ ዘጠና ከመቶው ሊባል የሚችለው የድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ፣ ከጥቂት የከፍተኛና መካከለኛ አመራር ቦታዎች በቀር ሁሉም የተያዙት አቶ አባይ በተከሏቸውና ከትግራይ ወረዳ ጭምር በመጡ ከያዙት መደብ ጋር ተገቢ ሙያና በቂ ልምድ በሌላቸው የህወኃት አባላት ነው›› ይላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኮርፖሬሽኑ ስራ መሪ አማካሪ ሆነው የተመደቡት በሙያው ልምድ የሌላቸውና ሊያማክሩ አይደለም ሊመከሩ የሚገባቸው አቶ ኃ/ማሪያም እንደ ልጃቸው ያሳደጓትና የዳሯት የእህታቸው ልጅ ባለቤት በመሆናቸው ብቻ ከአዋሳ መጥተው የተመደቡ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ በቅርቡ በተደረገው የመልካም አስተዳደርና የአመራር ግምገማ ላይ የተስተዋለው በእርግጥም አመራሩ ተወያይቶ እንደማይሰራ የውስጥ መረጃ ልውውጥ ሥርዓት የሌለውና ሁሉም የሕወኃት አባል ማለት በሚቻል ደረጃ በየመዋቅሩና በተመደበበት ‹‹የየድርሻውን›› እየተቀራመተ ያለበት መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ ምንጮቹ በዚህ የሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ የታየው ሙስናው የደረሰበትን ደረጃ፣ የተመዘበረውን ሃብት/ገንዘብና ቁሳቁስ/ ፣ የተረገጠውን የመንግስት የግዢ ስርዓና ደንብና የአንዳንዶችና ከህግ በላይ መሆን፣ በአጠቃላይም ኮርፖሬሽኑ የገባበትን አዘቅት በግልጽ ያመላከተና የወገን የለሽ ባለሙያዎችን የሥራ ተነሳሽነት ያዳከመ፣ ተስፋ ያስቆረጠ በመሆኑ ሥራ ለመልቀቅ እየሞከሩ እንደሚገኙባቸውም ይገልጻሉ፡፡ ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮችም– 1ኛ/ የግብይትና አቅርቦት ክፍሉ በማያውቀው መንገድ የተንዳሆ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ እስከ ውጪ በመሄድ ተደራድረው የውጪ ግዢ በመፈጸም ክፍያ እንዲደረግ እንደሚታዘዝ፣ በዚህም ለፋብሪካው የማያገለግል ዕቃ ተገዝቶ ፋብሪካ ከደረሰ በኋላ ጥቅም ላይ ሊውል አለመቻሉ በባለሙያ ተረጋግጦ ወደሌላ ፋብሪካ/በለስ/ እንዲጓጓዝ በትዕዛዛቸው 170 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የገለጹት ምንጮች ይህ በስብሰባ ላይ በመነሳቱ የተበሳጩት የፋብሪካው ስራአስኪያጅ ‹‹ ኮሎኔልና ዛሬ ላይ ለመድረስ ደም የከፈልኩ መሆኔን አታውቁምን ?›› በማለት ማስፈራራታቸውን ገልጸዋል፡፡በዚህና ተያያዥ በፋብሪካው ተከላ ላይ የተከሰተ የቴክኒክ ችግር የተንዳሆ ፋብሪካ በዚህ ዓመት ወደ ምርት ቢገባም በአጭር ጊዜ ምርቱን አቋርጧል፡፡ በተጨማሪም ባለሙያዎች ይህ የአመራርና የቴክኒክ ችግር ባለበት ሁኔታ መቼውንም ወደ ምርት እንደሚገባ ለመገመት አይቻልም ብለዋል፡፡ 2ኛ/ ኮርፖሬሽኑ ያሉትንም ማስፋፋት እንደ አማራጭ ታይቶ እየተሰራ ባለበትና በፋብሪካ ማሳዎች ዙሪያ የሰፈሩትን ገበሬዎች እያፈናቀለ ባለበት በወንጂ ፋብሪካ እርሻዎች መሃል ካለ መሬት ከውጪ የመጣ ኢንቨስተር በሚል ለአንድ የሕወኃት አባል 1000/አንድ ሺህ/ ሄክታር የእርሻ ቦታ መሰጠቱን ቅጥ ያጣ ሃፍረተ-ቢስ ተግባር ነው በማለት ገልጸዋል፡፡ 3ኛ/በዚህ ዓመት ምርት ይጀምራሉ ከተባሉት እንዲያውም በመጪው የካቲት ወር ወደ ምርት ይገባል ተብሎ የተነገረለት የኩራዝ አንድ ፋብሪካ ጉዳይ በሚመለከት እንኳን ወደ ስራ ሊገባ በባለሙያዎች ግምት መሰረት እስካሁን የተሸፈነው ከፋብሪካ ግንባታና ተከላ ሥራው ከግማሽ አይበልጥም ይላሉ የፋብሪካው ሰራተኞች፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመትም እንዲሁ ተብሎ የተተከለው የሸንኮራ አገዳ ጊዜው አልፎበት ለተከላ የዋለ ሲሆን ዘንድሮም ለሁለተኛ ጊዜ ዳግም ጊዜው አልፎበት ለተከላ ለመጠቀምም የተዘጋጀ ማሳ ባለመኖሩ ማኔጅመንቱ ምን ማድረግ እንዳለበት እየተጨነቀበት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ አሁን ባለው እውነት ኩራዝ ሁለት እንዳይቀድመን ይላሉ፡፡ በዚህ ላይ የአካባቢው ህዝብ ጥያቄና የፀጥታው ሁኔታ ተጨምሮበት ከዓመታት በኋላ ወደ ምርት ከገባን ትልቅ ውጤት ነው ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ በኮርፖሬሽኑ ውስጥ የሚታየው የመልካም አስተዳደር እጦትና የአሰራር ሥርዓቱ በህወኃት አባላት መደፍጠጡ፣በተጠቃሚዎቹ ይሉኝታ ቢስነት ታግዞ ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ ዓመታትም ለተመሳሳይ የብድር ጥያቄ እንጂ ለምርት የሚታሰብ አለመሆኑን ፣ የውስጥ ኦዲት አገልግሎት ክፍሉ ከዚህ የከፋ የግዢና ፋይናንስ አጠቃቀም ጥፋት መኖሩን ለማኔጅመንቱ በተደጋጋሚ መግለጽን በስብሰባው ላይ በይፋ ተናግሯል፡፡ ከህወኃት ውጪ ያሉ ባለሙያዎችም እኛን እንኳ እንደዜጋ ያገባቸዋል ቀርቶ እንደሰው ይታዘቡናል ያለማለታቸው፣ አድሎኣዊነቱ ዓይን ያወጣና የፈለጉትን በገሃድ መፈጸማቸው በእጅጉ ያስገርማል ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ የመረጃ ምንጮቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ስንት ጊዜ ይዋሻል፣ እስከ መቼስ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ይቀጥላል፣ እናስ መቼ ይሆን እንደዜጋ የምንታየው፣ ብለው ከጠየቁ በኋላ ከዚህ ዘረኝነት ለልማት የቱን ያህል መሰናክል እንደሆነ ለመረዳት የሚፈልግ የኛን ኮርፖሬሽን ጠጋ ብሎ ይመልከት በማለት የሚያደምጠን ካገኘን ብዙ የምንለው አለን ሲሉ ሃሳባቸውን ደምድመዋል፡፡
Part One. ‹‹ በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ እየሆነ ያለው በሰራተኞች አንደበት ሲገለጽ››// በተጠናቀቀው የመጀመሪያው የህዳሴና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን (ከ 2002 እስከ 2007) በአገራችን ሊከናወኑ በዕቅድ ከተያዙ ሜጋ -ፕሮጀክቶች -እንደ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጄክቶች /የህዳሴው ግድብ የለበትም፣በድንገት የተጀመረ ነው/፣ የባቡር ትራንስፖርት መስመር ግንባታ / አልተጀመረም ማለት የሚቻል/ና ዕድሳት፣ የአዳዲስ ስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ግንባታና ማስፋፊያ ፕሮጄክቶች /አስር/ …ይገኙበታል፡፡በዚህ ጥናታዊ ዘገባ የምንመለከተው በመጀመሪያው ዙር የህዳሴና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ይጠናቀቃሉ የተባሉትን ግን በተግባር አንዳቸውም በሚፈለገው አቅምና ደረጃ ወደ ምርት ያልገቡትን አስር አዳዲስ ስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ግንባታና ማስፋፊያ ፕሮጄክቶች ን ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ሦስቱ / በደቡብ ኦሞ ዞን ይተገበራሉ የተባሉት / አለመጀመራቸውን በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡ከመነሻው ፕሮጄክቱ 30 ከመቶውን አልጀመረም ማለት ነው ፡፡ ለዚህ ጥናት የመረጃ ምንጭ የሆኑት የኢቲቪ/ኢቢሲ ሪፖርቶች፣ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ሰራተኞችና በተጠቀሱት ፕሮጄክቶች ላይ እየሰሩ ያሉ የአመራር አካላት፣ ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች ናቸው፡፡ ጥናታዊ ዘገባው በሁለት ክፍሎች የተዘጋጀ ሲሆን ይህም ከወራት በፊት የተዘጋጀው ክፍል አንድና በክፍል ሁለት የተገለጸው ሰሞነኛ መረጃ የቀረበበት ነው፡፡ መልካም ንባብ፡፡ ክፍል አንድ– ከዚህ በፊት፡- ሃሰትና ክህደት የማይታክተው ዘረኛው የህወኃት አገዛዝ በስኳር ኮርፖሬሽን- ያስከተለው መዘዝ፤ መቼም በተመራጫችን ሚዲያ /ኢሳት/ መታፈን ጾማችን ቀርቶ የኢቢሲ/ኢቲቪ/የአየር ጊዜኣችን በመጨመሩ የማንሰማው ጉድ የለም፣ ይህ ሃፍረትና ይሉኝታ የማያውቅ መንግስት በራሱ ዓይን እያየን በራሱ ሚዛን እየመዘነን አያስታውሱም በሚል እሳቤ እስከሚሰለቸን ውሸቱን እያቀረሸብን የ50ኛ ኣመት ልደቱን ይነግረናል፣ ወይ አለማፈር፣ ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባለልወጣሽ፡፡ በዚያ ሰሞን ኢቢሲ/ኢቲቪ በመስኮቱ ዘወትር በሚመግበን የተትረፈረፈ ምርት ከምንሰቃይበት ቁንጣን በተቃራኒ መርዶ አርድቶናል፡፡ በስኳር ዋጋ ላይ በአንድ ጊዜ ሦስት ብር ጨምረናል በማለት፡፡ አዲስ አበባ ላይ ብር 18.40 እንዲሸጥ መንግስት ፈቅዶልናል ብሏል ኮርፖሬሽኑ፡፡ በዚህ ላይ ከዚህ በፊት በመጀመሪያው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተነገረንን አስታውሰን ወደያዝነው መረጃ እንገባለን፡፡ እንዲህ ተብለን ነበር ‹‹ … አስር አዳዲስና የማስፋፊያ የስኳር ፕሮጀክቶችን ወደ ምርት አስገብተን እያደገ የመጣውን የሽኳር ፍላጎት በማሟላት ከውጪ ለማስገባት የምናወጣውን የውጪ ምንዛሪ ከማትረፍ አልፈን ወደ ውጪ በመላክ የውጪ ምንዛሪ ገቢያችን እናሳድጋለን …›› ፡፡ በዕቅድ ዘመኑ ማብቂያ ደግሞ ‹‹ እነዚህን ፕሮጄክቶች ለማጠናቀቅ ተጨማሪ የአምስት ቢሊዮን ብር ብድር ከመንግስት እንዲፈቀድለት መጠየቁን …›› ነግረውናል፡፡ ከዚሁ በተያያዘ በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ ቅጥ ያጣውን ሙስናና 800 ሚሊዮን ብር አየር -በአየር ደብዛው እንደጠፋና ለዚህም ተጠያቂው አቶ አባይ ፀሃዬ መሆናቸውን ፣የተኳቸው አቶ ሺፈራው ጃርሶም ‹‹…. ተብትቦና አሳስሮት ገድሎት በሄደው ቤት እንደምን ለአስከሬን ህይወት ዘርተን ልንሰራ እንችላለን…›› እያሉ ሲያማርሩ እንደነበር ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ሰምተናል፡፡ አሁን በአምባሳደርነት ‹እስከተገላገሉበት› ድረስ አንድም ቀን በሥራቸው ደስተኛ ሆነው እንዳልታዩና የከፍተኛ የሥራ አመራሩን ሰብስበው አነጋግረው እንደማያውቁ እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በቴዘ ስለማንኛውም የኮርፖሬሽኑ አቅጣጫ በቦርዱ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይገለጽ እንጂ ‹ቦርዱ› የሚባለው አካልም ሆነ ስለሚያደርገው ስብሰባ እንኳን ባለሙያዎች፣ዝቅተኛና መካከለኛ አመራር ቀርቶ የከፍተኛ አመራር አባላትም እንደማያውቁ የውስጥ ኦዲት ምንጮች አሳውቀዋል፡፡ ዛሬ በአፈና ውስጥ ባይሆን በዕለት ተዕለት በሚጠቀመው ምርት /ስኳር/ላይ የተደረገው ጭማሪ ህዝቡን ለተቃውሞ የሚያስነሳ ነው፡፡ በየቱም ጊዜ እንዲህ ያለው ጭማሪ መንግስት በሚያቀርበው የእለት ተዕለት መጠቀሚያ ምርት ላይ ተደርጎ አያውቅም፡፡ ሦስት ብር በኪሎ ለደሃው/ለህዝብ ከፍተኛ ነው፡፡ ውስጥ አዋቂ ምንጮቹ ‹‹ በጭማሪው ቢያበቃ ጥሩ ነበር፣ ከዚያ አልፎ ለጭማሪው የተሰጠው ምክንያትና ከአዳዲሶቹ ሦስት ፋብሪካዎች በዚህ ዓመት ምርት ይጀምራሉ በማለት ዛሬም የተስፋ ዳቦ ማቅረቡ በመልካም አስተዳደር መድረክ ስለ ግልጽነትና ተጠያቂነት በሚያወሩበት ጊዜ መሆኑን ካለው እውነታ ጋር ስናየው እንደዜጋ በጣም ያማል ›› ሲሉ ምንጮቹ ምክንያታቸውን እንደሚከተለው ያቀርባሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የስኳር ዋጋ የተጨመረው ኮርፖሬሽኑ በሙስና የገባበትን የገንዘብ እጥረትና ከጠየቀውን የቢሊዮኖች ብር ተጨማሪ ብድር ከፊሉን ለመሸፈን ካልሆነ በቀር የስኳር ማምረቻ ዋጋ በኪሎ በየቱም ፋብሪካ ከ 7/ሰባት /ብር አይበልጥም፣ እንደኮርፖሬሽኑ የማምረቻ አማካይ ዋጋ ስሌት ከዚህ በታች ነው ይላሉ ፡፡ ስለዚህ ማንም ጠያቂ በሌለበት ቢያንስ እኛን የምናውቀውን ባያከብሩ እንኳ እንደሰው ሊያፍሩን በተገባ ፣ የህዝብ አካል መሆናችን በተረዱ ነበር፤ ሲሉ በቁጭት ይናገራሉ፡፡ ይህን ኃሳባቸውን በመረጃ ሲያጠናክሩም ፡- አቶ ሺፈራው ያነሱት የነበረውን የተተበተበ መዋቅርና በቅርቡ በኮርፖሬሽኑ የመልካም አስተዳደር ስብሰባ ላይ የተነሱትንና በከፍተኛ አመራሩ መካኪል በግልጽ ያለውን ልዩነትና የአሰራር ዝርክርክነት ያቀርባሉ፡፡ ስለመዋቅሩ ካነሳን ‹‹ማንም ወደ ኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት የሄደ ሰው ፣ መቀሌ ያለና የሥራ ቋንቋውም ትግርኛ ቢመስለው አይፈረድበትም፡፡ ዘጠና ከመቶው ሊባል የሚችለው የድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ፣ ከጥቂት የከፍተኛና መካከለኛ አመራር ቦታዎች በቀር ሁሉም የተያዙት አቶ አባይ በተከሏቸውና ከትግራይ ወረዳ ጭምር በመጡ ከያዙት መደብ ጋር ተገቢ ሙያና በቂ ልምድ በሌላቸው የህወኃት አባላት ነው›› ይላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኮርፖሬሽኑ ስራ መሪ አማካሪ ሆነው የተመደቡት በሙያው ልምድ የሌላቸውና ሊያማክሩ አይደለም ሊመከሩ የሚገባቸው አቶ ኃ/ማሪያም እንደ ልጃቸው ያሳደጓትና የዳሯት የእህታቸው ልጅ ባለቤት በመሆናቸው ብቻ ከአዋሳ መጥተው የተመደቡ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ በቅርቡ በተደረገው የመልካም አስተዳደርና የአመራር ግምገማ ላይ የተስተዋለው በእርግጥም አመራሩ ተወያይቶ እንደማይሰራ የውስጥ መረጃ ልውውጥ ሥርዓት የሌለውና ሁሉም የሕወኃት አባል ማለት በሚቻል ደረጃ በየመዋቅሩና በተመደበበት ‹‹የየድርሻውን›› እየተቀራመተ ያለበት መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡ ምንጮቹ በዚህ የሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ የታየው ሙስናው የደረሰበትን ደረጃ፣ የተመዘበረውን ሃብት/ገንዘብና ቁሳቁስ/ ፣ የተረገጠውን የመንግስት የግዢ ስርዓና ደንብና የአንዳንዶችና ከህግ በላይ መሆን፣ በአጠቃላይም ኮርፖሬሽኑ የገባበትን አዘቅት በግልጽ ያመላከተና የወገን የለሽ ባለሙያዎችን የሥራ ተነሳሽነት ያዳከመ፣ ተስፋ ያስቆረጠ በመሆኑ ሥራ ለመልቀቅ እየሞከሩ እንደሚገኙባቸውም ይገልጻሉ፡፡ ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮችም– 1ኛ/ የግብይትና አቅርቦት ክፍሉ በማያውቀው መንገድ የተንዳሆ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ እስከ ውጪ በመሄድ ተደራድረው የውጪ ግዢ በመፈጸም ክፍያ እንዲደረግ እንደሚታዘዝ፣ በዚህም ለፋብሪካው የማያገለግል ዕቃ ተገዝቶ ፋብሪካ ከደረሰ በኋላ ጥቅም ላይ ሊውል አለመቻሉ በባለሙያ ተረጋግጦ ወደሌላ ፋብሪካ/በለስ/ እንዲጓጓዝ በትዕዛዛቸው 170 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የገለጹት ምንጮች ይህ በስብሰባ ላይ በመነሳቱ የተበሳጩት የፋብሪካው ስራአስኪያጅ ‹‹ ኮሎኔልና ዛሬ ላይ ለመድረስ ደም የከፈልኩ መሆኔን አታውቁምን ?›› በማለት ማስፈራራታቸውን ገልጸዋል፡፡በዚህና ተያያዥ በፋብሪካው ተከላ ላይ የተከሰተ የቴክኒክ ችግር የተንዳሆ ፋብሪካ በዚህ ዓመት ወደ ምርት ቢገባም በአጭር ጊዜ ምርቱን አቋርጧል፡፡ በተጨማሪም ባለሙያዎች ይህ የአመራርና የቴክኒክ ችግር ባለበት ሁኔታ መቼውንም ወደ ምርት እንደሚገባ ለመገመት አይቻልም ብለዋል፡፡ 2ኛ/ ኮርፖሬሽኑ ያሉትንም ማስፋፋት እንደ አማራጭ ታይቶ እየተሰራ ባለበትና በፋብሪካ ማሳዎች ዙሪያ የሰፈሩትን ገበሬዎች እያፈናቀለ ባለበት በወንጂ ፋብሪካ እርሻዎች መሃል ካለ መሬት ከውጪ የመጣ ኢንቨስተር በሚል ለአንድ የሕወኃት አባል 1000/አንድ ሺህ/ ሄክታር የእርሻ ቦታ መሰጠቱን ቅጥ ያጣ ሃፍረተ-ቢስ ተግባር ነው በማለት ገልጸዋል፡፡ 3ኛ/በዚህ ዓመት ምርት ይጀምራሉ ከተባሉት እንዲያውም በመጪው የካቲት ወር ወደ ምርት ይገባል ተብሎ የተነገረለት የኩራዝ አንድ ፋብሪካ ጉዳይ በሚመለከት እንኳን ወደ ስራ ሊገባ በባለሙያዎች ግምት መሰረት እስካሁን የተሸፈነው ከፋብሪካ ግንባታና ተከላ ሥራው ከግማሽ አይበልጥም ይላሉ የፋብሪካው ሰራተኞች፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመትም እንዲሁ ተብሎ የተተከለው የሸንኮራ አገዳ ጊዜው አልፎበት ለተከላ የዋለ ሲሆን ዘንድሮም ለሁለተኛ ጊዜ ዳግም ጊዜው አልፎበት ለተከላ ለመጠቀምም የተዘጋጀ ማሳ ባለመኖሩ ማኔጅመንቱ ምን ማድረግ እንዳለበት እየተጨነቀበት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ አሁን ባለው እውነት ኩራዝ ሁለት እንዳይቀድመን ይላሉ፡፡ በዚህ ላይ የአካባቢው ህዝብ ጥያቄና የፀጥታው ሁኔታ ተጨምሮበት ከዓመታት በኋላ ወደ ምርት ከገባን ትልቅ ውጤት ነው ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ በኮርፖሬሽኑ ውስጥ የሚታየው የመልካም አስተዳደር እጦትና የአሰራር ሥርዓቱ በህወኃት አባላት መደፍጠጡ፣በተጠቃሚዎቹ ይሉኝታ ቢስነት ታግዞ ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ ዓመታትም ለተመሳሳይ የብድር ጥያቄ እንጂ ለምርት የሚታሰብ አለመሆኑን ፣ የውስጥ ኦዲት አገልግሎት ክፍሉ ከዚህ የከፋ የግዢና ፋይናንስ አጠቃቀም ጥፋት መኖሩን ለማኔጅመንቱ በተደጋጋሚ መግለጽን በስብሰባው ላይ በይፋ ተናግሯል፡፡ ከህወኃት ውጪ ያሉ ባለሙያዎችም እኛን እንኳ እንደዜጋ ያገባቸዋል ቀርቶ እንደሰው ይታዘቡናል ያለማለታቸው፣ አድሎኣዊነቱ ዓይን ያወጣና የፈለጉትን በገሃድ መፈጸማቸው በእጅጉ ያስገርማል ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ የመረጃ ምንጮቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ስንት ጊዜ ይዋሻል፣ እስከ መቼስ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ይቀጥላል፣ እናስ መቼ ይሆን እንደዜጋ የምንታየው፣ ብለው ከጠየቁ በኋላ ከዚህ ዘረኝነት ለልማት የቱን ያህል መሰናክል እንደሆነ ለመረዳት የሚፈልግ የኛን ኮርፖሬሽን ጠጋ ብሎ ይመልከት በማለት የሚያደምጠን ካገኘን ብዙ የምንለው አለን ሲሉ ሃሳባቸውን ደምድመዋል፡፡
Part Two: ክፍል ሁለት– አሁን በቅርቡ፡- በስኳር ልማት ኮርፖሬሽን የሚፈጸመው ሠራተኛውን ‹‹ በአገሪቱ መንግስት አለ ወይ›› …እያስባለ ነው// ከላይ በክፍል አንድ የቀረበው ዘገባ እንደተጠበቀ ሆኖ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ከዚያ ስብሰባ በኋላ ስላለው የሚከተለውን አካፍለውናል፡፡ በ 14/07/08 ከጠ/ሚ/ር ቢሮ —መጣ የተባለ የሜጋ ፕሮጄክቶች የጥናት ቡድን–ከውስንና የተመረጡ (መስፈርቱ ባይታወቅም) ሠራተኞችና አመራሮች ጋር ስለ ኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ውይይት ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ ውይይት ላይ ሠራተኛው በምሬት ብሶቱንና ኮርፖሬሽኑ የገባበትን አዘቅት ‹‹አሁን የምታናግሩን ልታባርሩን ከሆነ አባሩን እንጂ እንናገራለን፣ ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ አያውቁም ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ (የኮርፖሬሽኑን የሥራ መሪ/ዋና ዳይሬክተር አማካሪ ከክፍል አንድ ልብ ይሏል)›› በማለት ኃሳብና አስተያየት አቅርበዋል፡፡ የተነሱትን ጉዳዮች እንደሚከተለው አጠቃለን አቅርበናል፡፡ በ2007 በጀት ዓመት የተመዘገበው የበጀት አጠቃቀም ከ100 % በላይ ሲሆን የፊዚካል አፈጻጸም ደግሞ 18 ከመቶ/18 %/ ነው፡ ገንዘቡ በክብሪት ካልተቃጠለ በቀር ምን እየተፈጸመ እንደሆነ ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡ በፋብሪካዎች ያሉት የህንድ ባለሙያዎች የእውቀት፣ ልምድና ቴክኖሎጂ ሽግግር የተባለውን ዓላማ ማስፈጸም ይቅርና በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ያለውን የማምረት ሂደት እያደናቀፉ ነው፡፡ ለዚህም ያበቁት በግልጽ የሚታዩ የመዋቅር፣ አመራርና አሰራር ችግሮች ናቸው፡፡ ማለትም፡- 1. መዋቅር፤ ሰዎችን በሹመት ስም ለመጥቀም የተዘጋጀ በድርጅት ማነጅመንት አወቃቀር ሣይንስ ላይ ያልተመረኮዘ የተንዛዛና የተንዘላዘለ መዋቅር ነው፡፡ (ሁለት ሰው የቡድን መሪ)፣ 2. አመራር፤ የዋና መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች ሹመትና ቅጥር ከሙያ ዝግጅትና ልምድ ይልቅ ከፖለቲካ ድርጅት አባልነትና ከህወኃት ባለስልጣን ካለ ዝምድናና ግንኙነት ጋር የተያያዘ ነው፤ ስለፕሮጄክት ጽንሰ ኃሳብ፣ አመራርና አተገባበር ዕውቀትና ልምድ የለም፡፡ 3. አሰራር፡- ከቅጥር ጀምሮ ከጥቂቶች በቀር እያንዳንዱ አመራርና ሠራተኛ ከጀርባው ጠባቂ አለው፤ ስለቅጥር፣ ዕድገት…. የሚመካበትና ቢያጠፋ የሚመክትለት አለው፡፡ ከፋብሪካዎች የሚደርሰው ሪፖርት ሃሰትነት ከዚህ ጋር የተዛመደ ነው፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ከዋና መስሪያ ቤት እስከ ፕሮጀክቶች ላለው ከፍተኛ የሰራተኛ ፍልሰት ምክንያት ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ችግሮች ጋር በተያያዘ በአሁኑ ጊዜ በሜጋ-ፕሮጀክቱ ከታያዙ ፋብሪካዎች ወደ ተግባር የገቡት ውስጥ የሚታየው ተጨባጭ ሁኔታ የሚከተለው ነው፡፡ 1. የተንዳሆ ፋብሪካ ምርት አቁሟል—— በክፍል አንድ ከተገለጹት ችግሮች ጋር በተያያዘ ፋብሪካው ወደኋላ ተመልሶ ወደ ፕሮጀክት ይግባ/አይግባ እየተባለ ነው፡፡ ይህም ‹እንደገና› ወደ ምርት ስለሚገባበት የፕሮጄክት ጥናትና የመልሶ ማቋቋም ትግበራ በጀት ተይዞለት ከማምረቻ ፋብሪካ ወጥቶ ወደ ዝርዝር ጥናት ይመለስ ማለት ነው፡፡ 2. የበለስ ፋብሪካ ፕሮጀክት ችግር ውስጥ ነው—– ከተንዳሆ የመጣው ያልታዘዘ የፋብሪካ ዕቃ ባስከተለው የቴክኒክ ችግር ፋብሪካው ሊንቀሳቀስና ወደ ምርት ሊገባ አልቻለም፡፡ ለፋብሪካው ግብኣት እንዲሆን የተተከለው ሸንኮራ አገዳ ዕድሜው ስለደረሰ ይቆረጥ/አይቆረጥ፣ ከተቆረጠስ በኋላ እንደምን ለሌላ አገልግሎት/ጥቅም /የእንስሳት መኖ፣…/ሊውል ይችላል በሚለው ላይ የእርሻ ክፍል ባለሙዎች እየተወያዩ ና ከኮርፖሬሽኑ ጋር እየተመካከሩ ነው፡፡ 3. የኩራዝ አንድ ፋብሪካ ፕሮጄክት ፡- ለፋብሪካ ግብኣትነት የተተከለው ሸንኮራ ዕድሜው አልፎበት የፕሮጄክት አመራሩ ለማቃጠል ከኮርፖሬሽኑ ውሳኔ ጠይቆ ማንም እጁን ለማስገባት ባልፈለገበት እውነት ውስጥ በየካቲት ወር ፋብሪካው ‹‹የሙከራ ምርት መጀመሩን›› በቴለቪዥን መስኮት አሳይቶናል፡፡ ‹‹ አይ አለማፈር›› …… 4. የኩራዝ ሁለት—- ምንም የእርሻ /ሸንኮራ ማምረት እንቅስቃሴ/መሬት ምንጣሮ እንኳ/ ባልተጀመረበት በጫካ ውስጥ የፋብሪካ ግንባታው በቻይናዎች በፍጥነት እየተካሄደ ነው፣ ባለሙያዎች የፋብሪካው ግንባታ እየተጓዘ ባለው ፍጥነት ከቀጠለ ከኩራዝ አንድ ቀድሞ ሊጠናቀቅ ይችላል የሚል ግምት እንዳላቸው አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡ ከኩራዝ አንድ ተቃራኒ ችግር ማለትም ፋብሪካው ተጠናቆ የሸንኮራ ምርት ግብኣት ችግር ይገጥመዋል የሚል፡፡ 5. የአርጆ ዴደሳ ፋብሪካ ፕሮጀክት— ይህ ፋብሪካ በፓኪስታኖች ተሰርቶ ወደ ኮርፖሬሽኑ እንዲካተት የተደረገ ነው፡፡ የፋብሪካው ግንባታ አልቆ የተተከለው ሸንኮራ አገዳ ደርሶ ለግብኣትነት ሊቆረጥ ከተቃጠለ በኋላ የፓክስታን ባለሃብቶች ከመንግስት ጋር ያላለቀ ጉዳ ስላለ እንደያቆረጥ አግደው ሸንኮራው ለብልሽት እየተዳረገ ያለበትና ከጥቅም ውጪ ሆኖ ለኪሳራ ሊዳርግ የመችልበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በስብሰባው መጨረሻ ላይ ሰራተኞቹ ‹‹በኮርፖሬሽኑ በተያዙት የሜጋ ፕሮጄክቱ አስሩ ፋብሪካዎች ውስት በሚታየው የመዋቅር፣ አመራርና አሰራር ችግሮች ድምር ውጤት ከፋብሪካዎቹ በመጪዎቹ ዓመታት የሚጠበቅ የስኳር ምርት የለም፡፡ በቀጣይ ዓመታት ዕቅዳችሁም ከፋብሪካዎቹ ለህዝብ ፍላጎት የሚደርስ ስኳር አለ ብላችሁ አታስቡ — እንደተለመደው አያስገባን እናከፋፍላለን›› በማለት ኃሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ በምርት ላይ ባሉ ፋብሪካዎች/ በተለይ በወንጂ/ ያሉ ከቴክኒክ አገልግሎት በተጨማሪ ለዕውቀት ክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ያግዛሉ ተብለው በከፍተኛ ክፍያ የመጡ የህንድ ባለሙያዎች አብረዋቸው የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎችን በማግለል፣ እነርሱ ሲጠግኑም ሆነ አዲስ መሳሪያ ሲገጥሙ አጠገባቸው እንዳይገኙ በማድረግ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግሩ አስተዋጽኦ ማድረግ ቀርቶ የተለያዩ ጥቃቂን ምክንያቶች/ ቁርስ በሰዓት አልደረሰንም ፣ሰርቪስ አልመጣልንም/አልቀረበልንም…./ በሚል ፋብሪካዎች በሰዓቱ ወደ ምርት ተግባር እንዳይገቡ እንቅፋት እየሆኑ እንደሚገኙ ሰሚ ባያገኙም ሰራተኞች በቁጭት ስሞታቸውን በየጊዜውና በየመድረኩ ያቀርባሉ፡፡ ኢዮብ ዓለም —