በደቡብ ኦሞ ወደ አመጽ እየተገፋ ያለው- ህዝባዊ እምቢተኝነት
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
እነ ዓለማዬሁ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ 60 ሰዓት አለፈ// ቤተሰብ በሄርፒስ ኮርፒስ መብት ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ነው ፡፡ በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጂንካ ፖሊስ ጣቢያ ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ የኦህዲኅ ም/ሰብሳቢ አቶ ዓለማዬሁን ጨምሮ የታሰሩት ሦስት ሰዎች በተጠረጠሩበት ጉዳይ ቃላቸውን ሳሰጡና ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ሦስተና ሌሊት በእስር ቤት ሊያሳልፉ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ገልጸውልናል፡፡
ቤተሰቦችና የትግል ጓዶቻቸው ስለዛሬ ውሎኣቸው እንደገለጹልን ዛሬ ጠዋት በከተማው ያሉ ኮማነደሮች በሙሉ ፖሊስ ጣቢ ሄደው እንደነበርና እነ አቶ ዓለማዬሁ ‹‹ ስለምን ለተጠረጠርንበት ድርጊት አንዳች መረጃ ባላገኛችሁበት በልሙጥ ወረቀትና የመዝሙር ካሴት እንታሰራለን፣ ይህ ህጋዊ ነውን ? ›› ብለው ለጠየቁት ኮማንደሮቹ እርስ በርስ ከመተያየት ውጪ ምንም መልስ አልሰጡም፡፡አያይዘውም ከሰዓት በኋላ ወደ ዞኑ ፖሊስ መምሪያ ተወስደው በተጠረጠሩበት ጉዳይ ሳይሆን በተያዙ ዕቃዎች ላይ ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደርገው ወደ እስር ቤት እንደተመለሱ ገልጸውልናል፡፡ ይህ አካሄድ ህጋዊ አይደለም፣ በተጠረጠሩበት የማይታወቅ ጉዳይ ቃላቸውን ሳይሰጡና በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለሦስተኛ ቀን በእስር ቤት ማደራቸው ህገመንግስታዊ መበንታቸውንና ህግን መዳፈር ስለሆነ ነገ ሰብዐዊ መብታቸውን ለማስከበር የሄርፒስ ኮርፕስ አቤቱታ እናቀርባለን ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ ባለበት እነ አቶ ዓለማዬሁ ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ቅዳሜ ከገበያ መልስና እሁድ ከቤተክርስቲያን መልስ የከተማው አዛውንቶችና ነዋሪዎች በከፍተኛ ቁጥር ፖሊስ ጣቢያ በመገኘት እንደጠየቋቸውና እንዳበረታቷቸው ፣ይህም እነ አቶ ዓለማዬሁ እያደረጉ ያሉት ሰላማዊ ትግልና እያሰሙ ያሉት ጩሄት የህዝቡን ጥያቄና ፍላጎት ያማከለና ህዝቡ ከጎናቸው መሆኑን ያሳያል ሲሉ በህዝቡ ድጋፍ ታሳሪዎችም ሆኑ የትግል አጋሮቻቸውና ቤተሰብ የተደሰተና የተበረታታ መሆኑን ጨምረው ገልጸውልናል፡፡ በተያያዘ ዜናም የኦህዲኅ ወጣቶች ክንፍ አባላት ‹ መሪያችን ታስሮብን ዝም ብለን አንቀመጥም › በማለት ምን ሰላማዊ ጫና መፍተር እንዳለባቸው ዛሬ እንደመከሩ ድርጅቱ አባላት አሳውቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ከጂንካ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ የተገኘ መረጃ – ለስራ ጉዳይ ከክልል/ሃዋሳ/ ጂንካ የሚገኙ አንድ ከፍተኛ የደህንነት ሠራተኛ ስለሁኔታው ለመከታተል ፖሊስ ጣቢያ ሄደው በሰሙትና በፍተሻ ተገኙ የተባሉትን ወረቀቶችና ንብረቶች ተመልክተውአንዱን ሞባይል በመወርወር የጣቢውን ፖሊስ አዛዥ በዚህ ዓይነት ያለማስረጃ ማሰር ለምን አስፈለገ በማለት ተቆጥተው መውጣታቸው ተመልክቷል፡፡ በመጨረሻም ይህን ጉዳይ በሚመለከት መረጃውን ላሰራጫችሁ፣ አጋርነታችሁን ለገለጻችሁ፣ ህመማችን ለተጋራችሁና ታሳሪዎችን ለጎበኛችሁ እንዲሁም ለጊዜው አገር-ቤት ቢዘጋም ‹ኢሳት› ስለጉዳዩ የቅርብ ክትትል በማድረግ ስላቀረበልን ቃለመጠይቅ ሁሉ ምስጋናችንን እያቀረብን፣ ከእንዲህ ዓይነቱ ህገወጥና የማንአለብኝነት አገዛዝ ለመገላገል እያንዳንዳችንና ሁላችን የበኩላችን እንወጣ ጥሪያችን ነው፡፡
በደቡብ ኦሞ ወደ አመጽ እየተገፋ ያለው- ህዝባዊ እምቢተኝነት // በደቡብ ኦሞ ዞን የሚታየው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ምስቅልቅል ሁኔታ በፍትህ መዛባት እየታገዘ በህዝቡ የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ እያሳረፈ ያለው ተጽዕኖ ከሸክም በላይ እየሆነ መጥቷል ፡፡ የዞንና ወረዳ ከተሞች አስተዳደር፣ ፍትህ ቢሮና የፖሊስ ኃይል ፣ የማንአለብኝ ተግባር በዞኑ በሰፈሩ የመከላከያና ልዩ ኃይል አባላት እየታገዘ በህዝቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚደርሰው በደልና ግፍ ህዝቡን ‹በቃኝ› እያስባለ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በሃመር ወረዳ በወጣቶችና የዞኑ ፖሊስ በኋላም ከመከላከያና ልዩ ኃይል ጋር ግጭት መፈጠሩንና ለብዙ ዜጎች ህይወት መጥፋትና አካል መጉደል ምክንያት መሆኑን ፣ አንድ አመራር መገደላቸውን፣ በአቶ አወቀ አይኬ ላይ ተኩስ መከፈቱን የሚያስታውሱ ነዋሪዎች አሁን ደግሞ በማሌ ወረዳ ዋና ከተማ በ ‹ሌሞ ጌንቶ› ከተማ በም/ሳጂን ደግነት ኤሆ ላይ የተፈጸመው ግድያ የዚሁ ማሳያ መሆኑን ይገልጻሉ ፡፡ በማሌ ወረዳ ዋና ከተማ ሌሞጌንቶ በመጋቢት 14/ 08 ዓ.ም ምክትል ሳጂን ደግነት ኤሆ የቆመ ሞተር ቢስክሌት ለምን ነካህ ብሎ 50 ብር ትቀጣለህ ያለው ነዋሪ ፣ ነገር ለማብረድ በሚል ሠላሳ ብር ልስጥህ ሲለው የለም አልቀበልም ብሎ በጥፊ ሲማታ የተመቺ ዘመዶች መጀመሪያ ገንዝብ መጠየቅህ አግባብ አልነበረም፣ አሁን ደግሞ ይባስ ብለህ ለምን ትመታዋለህ ብለው ሲጠይቁት ጥይት ይተኩሳል ፡፡ በዚህ ድርጊት የተበሳጩት በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ተባብረው ባደረሱበት ጉዳት የምክትል ሳጂን ደግነት ኤሆ ህይወት አልፏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁለት ወንድማማቾች አቶ ፈስታዬ ወንዳጥርሻ እና አቶ ወታደር ወንዳጥርሻ ተይዘው የተወሰዱበት አይታወቅም ሲሉ ቤተሰቦቻቸው በጭንቀት ገልጸዋል ፡፡ በበነጋው ሶስት መኪና የመከላከያ ኃይል ወደ ወረዳው መሄዱን የገለጹት ምንጮች አካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኑንና የአካባቢው ነዋሪና መከላከያ ኃይሉ በፍጥጫ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ከጅንካ በተገኘው መረጃ የደረሱበት አልታወቀም የተባሉት ሁለቱ ወንድማማቾች ከመጋቢት 17/ 08 ጀምሮ በጂንካ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ እነዚህ ታሳሪ ወንድማማቾች እንደሚገልጹት ከሆነ በወረዳቸው ያሉት አስተዳዳሪዎች፣ ዳኞችና ፖሊሶች በህዝቡ ላይ የሚፈጽሙት በደል ህዝቡን እያማረረው ‹‹ ከዚህስ ሞት ይሻላል›› የሚያስብል ደረጃ እንዳደረሰውና የም/ሣጂን ሞትም ከዚህ ብሶትና ምሬት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ፣የመንግስት ባለሥልጣናትና የህዝብ ግንኙነት በዚህ ከቀጠለ ህዝብ ወደማይፈልግበት ተገፍቶ ሁኔታው ወደከፋ ደረጃ ሊሸጋገር እንደሚችል ከህዝቡ የሚሰማው ብሶት ያመለክታል ብለዋል፡፡ ይህንን በሚመለከት ወደ ወረዳው ደውለን ያገኘነው መረጃም የታሳሪዎቹን አባባል የሚያረጋግጥ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሃመር ወጣቶችና በመንግስት መካከል የተፈጠረው ግጭት የክልሉ ፕሬዝዳንት በቦታው ተገኝተው ዕርቅ ወረደ ቢባልም እስካሁን እልባት እንዳላገኘና ወደ ማጎ ፓርክ በረሃ የወረዱት ወጣቶች እስካሁንም ወደ መኖሪያቸው እንዳልተመለሱና ከፓርኩ ስካውቶች ጋር በየጊዜው እንደሚጋጩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በዚህ መልኩ እስከመቼ ይቀጥላል የሚሉት የሃመር ወረዳ ነዋሪዎች ያለው ውጥረት ለደህንነታቸው አስጊ እንደሆነና ባለፈው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ የተከሰተው ሁኔታ እንዳይደገም ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ፡፡ በተመሳሳይ ኩራዝ አንድና ሁለት የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች እየተካሄዱ ያለበት ሳላማጎ ወረዳ ከፕሮጄክቱ መጀመሪያ እስከአሁን የዘለቀው የነባር ነዋሪ ህዝቦች /ሙርሲ፣ ቦዲ እና ሱርማ/ ጥያቄ እስካሁን ምላሽ ባለማግኘቱ ቅሬታውና ተቃውሞው እንደቀጠለ በመሆኑ ወረዳውን የስጋት ቀጠና አድርጎታል፡፡ በአጠቃላይ በደቡብ ኦሞ ዞን ከዓመታት በፊት በዞኑ ዋና ከተማ-ጂንካ በሁለት ካምፖች የሰፈረው የመከላከያና ልዩ ኃይል በከተማው ወጣቶች ላይ የሚያሳየው የማንአለብኝነት ስሜትና ተግባር ከዞኑ አስተዳደር የተጠያቂነት አለመኖር ጋር ተደምሮ በዞኑ ውስጥ ያለው ነዋሪ ላይ እየፈጠረ ያለው የብሶት ስሜት የህዝቡን ትዕግስት እየተፈታተነ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የህዝቡን እምቢተኝነት ወደ ኃይል እርምጃና አመጽ እያሳደገው መሆኑና የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ይህንን በአፈሙዝና በማስፈራራት ሊቀለብሱና ሊያፍኑ የሚያደርጉት ሁሉ ከዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ይልቅ ቅራኔውን የሚያጠናክር ይሆናል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በዞኑ የተጋረጠውን የደህንነት፣ መረጋጋትና በልማት ላይ ሊያስከትል በሚችለው አሉታዊ ተጽዕኖ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡ ሰሚ ያላኘውንና በተደጋጋሚ የምንለው ‹‹ልብ ያለው ልብ ይበል›› መልዕክታችን ነው፡፡ ለአገርና ህዝብ የሚጠቅመውን ደግ ደጉን ያሰማን፡፡ በቸር ያገናኘን፡፡ 19/07/08 UNITE.
Another News. በደቡብ ኦሞ ወደ አመጽ እየተገፋ ያለው- ህዝባዊ እምቢተኝነት // በደቡብ ኦሞ ዞን የሚታየው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ምስቅልቅል ሁኔታ በፍትህ መዛባት እየታገዘ በህዝቡ የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ እያሳረፈ ያለው ተጽዕኖ ከሸክም በላይ እየሆነ መጥቷል ፡፡ የዞንና ወረዳ ከተሞች አስተዳደር፣ ፍትህ ቢሮና የፖሊስ ኃይል ፣ የማንአለብኝ ተግባር በዞኑ በሰፈሩ የመከላከያና ልዩ ኃይል አባላት እየታገዘ በህዝቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚደርሰው በደልና ግፍ ህዝቡን ‹በቃኝ› እያስባለ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በሃመር ወረዳ በወጣቶችና የዞኑ ፖሊስ በኋላም ከመከላከያና ልዩ ኃይል ጋር ግጭት መፈጠሩንና ለብዙ ዜጎች ህይወት መጥፋትና አካል መጉደል ምክንያት መሆኑን ፣ አንድ አመራር መገደላቸውን፣ በአቶ አወቀ አይኬ ላይ ተኩስ መከፈቱን የሚያስታውሱ ነዋሪዎች አሁን ደግሞ በማሌ ወረዳ ዋና ከተማ በ ‹ሌሞ ጌንቶ› ከተማ በም/ሳጂን ደግነት ኤሆ ላይ የተፈጸመው ግድያ የዚሁ ማሳያ መሆኑን ይገልጻሉ ፡፡ በማሌ ወረዳ ዋና ከተማ ሌሞጌንቶ በመጋቢት 14/ 08 ዓ.ም ምክትል ሳጂን ደግነት ኤሆ የቆመ ሞተር ቢስክሌት ለምን ነካህ ብሎ 50 ብር ትቀጣለህ ያለው ነዋሪ ፣ ነገር ለማብረድ በሚል ሠላሳ ብር ልስጥህ ሲለው የለም አልቀበልም ብሎ በጥፊ ሲማታ የተመቺ ዘመዶች መጀመሪያ ገንዝብ መጠየቅህ አግባብ አልነበረም፣ አሁን ደግሞ ይባስ ብለህ ለምን ትመታዋለህ ብለው ሲጠይቁት ጥይት ይተኩሳል ፡፡ በዚህ ድርጊት የተበሳጩት በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ተባብረው ባደረሱበት ጉዳት የምክትል ሳጂን ደግነት ኤሆ ህይወት አልፏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁለት ወንድማማቾች አቶ ፈስታዬ ወንዳጥርሻ እና አቶ ወታደር ወንዳጥርሻ ተይዘው የተወሰዱበት አይታወቅም ሲሉ ቤተሰቦቻቸው በጭንቀት ገልጸዋል ፡፡ በበነጋው ሶስት መኪና የመከላከያ ኃይል ወደ ወረዳው መሄዱን የገለጹት ምንጮች አካባቢው በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኑንና የአካባቢው ነዋሪና መከላከያ ኃይሉ በፍጥጫ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ከጅንካ በተገኘው መረጃ የደረሱበት አልታወቀም የተባሉት ሁለቱ ወንድማማቾች ከመጋቢት 17/ 08 ጀምሮ በጂንካ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ እነዚህ ታሳሪ ወንድማማቾች እንደሚገልጹት ከሆነ በወረዳቸው ያሉት አስተዳዳሪዎች፣ ዳኞችና ፖሊሶች በህዝቡ ላይ የሚፈጽሙት በደል ህዝቡን እያማረረው ‹‹ ከዚህስ ሞት ይሻላል›› የሚያስብል ደረጃ እንዳደረሰውና የም/ሣጂን ሞትም ከዚህ ብሶትና ምሬት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ፣የመንግስት ባለሥልጣናትና የህዝብ ግንኙነት በዚህ ከቀጠለ ህዝብ ወደማይፈልግበት ተገፍቶ ሁኔታው ወደከፋ ደረጃ ሊሸጋገር እንደሚችል ከህዝቡ የሚሰማው ብሶት ያመለክታል ብለዋል፡፡ ይህንን በሚመለከት ወደ ወረዳው ደውለን ያገኘነው መረጃም የታሳሪዎቹን አባባል የሚያረጋግጥ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሃመር ወጣቶችና በመንግስት መካከል የተፈጠረው ግጭት የክልሉ ፕሬዝዳንት በቦታው ተገኝተው ዕርቅ ወረደ ቢባልም እስካሁን እልባት እንዳላገኘና ወደ ማጎ ፓርክ በረሃ የወረዱት ወጣቶች እስካሁንም ወደ መኖሪያቸው እንዳልተመለሱና ከፓርኩ ስካውቶች ጋር በየጊዜው እንደሚጋጩ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በዚህ መልኩ እስከመቼ ይቀጥላል የሚሉት የሃመር ወረዳ ነዋሪዎች ያለው ውጥረት ለደህንነታቸው አስጊ እንደሆነና ባለፈው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ የተከሰተው ሁኔታ እንዳይደገም ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ፡፡ በተመሳሳይ ኩራዝ አንድና ሁለት የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች እየተካሄዱ ያለበት ሳላማጎ ወረዳ ከፕሮጄክቱ መጀመሪያ እስከአሁን የዘለቀው የነባር ነዋሪ ህዝቦች /ሙርሲ፣ ቦዲ እና ሱርማ/ ጥያቄ እስካሁን ምላሽ ባለማግኘቱ ቅሬታውና ተቃውሞው እንደቀጠለ በመሆኑ ወረዳውን የስጋት ቀጠና አድርጎታል፡፡ በአጠቃላይ በደቡብ ኦሞ ዞን ከዓመታት በፊት በዞኑ ዋና ከተማ-ጂንካ በሁለት ካምፖች የሰፈረው የመከላከያና ልዩ ኃይል በከተማው ወጣቶች ላይ የሚያሳየው የማንአለብኝነት ስሜትና ተግባር ከዞኑ አስተዳደር የተጠያቂነት አለመኖር ጋር ተደምሮ በዞኑ ውስጥ ያለው ነዋሪ ላይ እየፈጠረ ያለው የብሶት ስሜት የህዝቡን ትዕግስት እየተፈታተነ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የህዝቡን እምቢተኝነት ወደ ኃይል እርምጃና አመጽ እያሳደገው መሆኑና የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች ይህንን በአፈሙዝና በማስፈራራት ሊቀለብሱና ሊያፍኑ የሚያደርጉት ሁሉ ከዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ይልቅ ቅራኔውን የሚያጠናክር ይሆናል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በዞኑ የተጋረጠውን የደህንነት፣ መረጋጋትና በልማት ላይ ሊያስከትል በሚችለው አሉታዊ ተጽዕኖ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡ ሰሚ ያላኘውንና በተደጋጋሚ የምንለው ‹‹ልብ ያለው ልብ ይበል›› መልዕክታችን ነው፡፡ ለአገርና ህዝብ የሚጠቅመውን ደግ ደጉን ያሰማን፡፡ በቸር ያገናኘን፡፡ 19/07/08 UNITE.