ከ18 የኦሮሚያ ዞኖች 14ቱ ዞኖች በ2009 ዓ.ም. ዩኒቨርሲቲ የሚገባ ተማሪ የለም ማለት ነው።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ለኦሮሞ ህዝብ ከዚህ የሚበልጥ አጀንዳ የለም!!
ከ18 የኦሮሚያ ዞኖች 14ቱ ዞኖች በ2009 ዓ.ም. ዩኒቨርሲቲ የሚገባ ተማሪ የለም ማለት ነው።
ኦሮሚያ ውስጥ 18 ዞኖቹ አሉ። እስካሁን ባለው መረጃ ከ18ቱ ዞኖች የመማር ማስተማር ሂደት ያልተቋረጠው በ4 ዞኖች ብቻ ነው። ትምህርት ሙሉ በሙሉ ያልተቋረጠባቸው ዞኖች፦ ፊንፊኔ፣ ምሥራቅ ሸዋ፣ አርሲና ጂማ ዞኖች ናቸው።
ትምህርት የተቋረጠባቸው በ14ቱ ዞኖች ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አይሰጥም ማለት ነው። ከ14ቱ የኦሮሚያ ዞኖች በ2009 ዓ.ም. ዩኒቨርሲቲ የሚገባ ተማሪ የለም ማለት ነው። ለኦሮሞ ህዝብና ለኦሮሚያ ከዚህ የሚበልጥ አጀንዳ የለም፣ ሊኖርም አይችልም።
የኦሮሚያ ጉዳይ ያለ ፖለቲካዊ መፍትሄ በተራ መልካም አስተዳደር ሊፈታ አይችልም ሲባል የሚሰማ ሰው የለም። 300 የኦህዴድ ካድሬዎችን ማባረር ለኦሮሞ ህዝብና ኦሮሚያ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። ውድ ጊዜ ያለ አግባብ እየተቃጠለ ነው።
ህጋዊና ፖለቲካ መፍትሄዎቹ፦
1) በታጣቂዎችና አጋዚዎች ለተገደሉት በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ካሳ መክፈል፣
2) ገዳዮችንና የግድያው አዛዦች በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ለፍርድ ማቅረብ፣
3) ያለምንም ቅድሚያ ሁኔታ በተቃውሞው የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፣
4) ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ባሉበት በኦሮሚያ ህዝባዊ ምርጫ ማካሄድና በህዝብ የተመረጠ ፓርቲ ብቻ ክልሉን እንዲያስተዳድር ማድረግ ህጋዊና ፖለቲካዊ መፍትሄዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
** እናቱ የሞተችበትና እናቱ ገበያ የሄደችበት ልጅ እኩል የሚያለቅሱበት ምክንያት ሊኖር አይችልም። የኦሮሚያ ጉዳይ ከየትኛውም ክልል የተለየና የከፋ ነው።