የጀሀዳዊ ሀረካት ዶክመንተሪ አዘጋጅ የተሰራው አዲስ ቤዛ የተሰኘ ፊልም ላይ በማህበራዊ ሚዲያ የቦይኮት ዘመቻ ተካሄደበት::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አብደላህ ኢብን አብደላህ's photo.

የኢትዮጵያን ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ እና ህዝበ ሙስሊሙ በፊርማው ጥያቄዬን በሰላማዊ መንገድ ያቀርቡልኛል ያላቸን ኮሚቴዎችንን አሸባሪ በማለት የሚዎነጅለው ጀሀዳዊ ሀረካት የተሰኘውን ዶክመንተሪ ፊልምን ያዘጋጀው የወያኔ ለጋሲ አስቀጣይ የሆነው ብርሀኔ ንጉሴ የተባለው ግለሰብ አዲስ የሰራው ቤዛ የተሰኘ ፊልም በማህበራዊ ሚዲያ ፊልሙን እንዳታዩ የሚል ዘመቻ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡
አዲስ የተሰራው ፊልም ወንድም ወንድሙ ግድሎ እና አስገድሎ ወደ ስልጣን የመጣበትን የወያኔን የቀድሞ የጫካ አውሬነታቸውን ሂወት የሚያሳይ አንደትልቅ ጀብድ በማር ቀብተው ህዝቡን ለማደናገር የተሰራ ፊልም ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደበት ያለው ዋነኛ ምክንያት በኦሮሚያ ፣ በአማራ ፣ በኮንሶ ፣ በጋምቤላ ፣ እና በሱርማ ህዝቡ በህወሀት ቅልብ ወታደሮች እየተገደሉ ባለበት ወቅት እና በሰላማዊ መንገድ ሙስሊሙ ያቀረባቸውን ጥያቄዎች ከመመለስ ወደ ጎን ብሎ መፍትሄ አፈላላጊ ኮመቴዎችን በሀሰት ወንጅሎ ለእስር በዳረገበት ወቅት እንዲህ አይነት ፊልም አዘጋጅቶ ማውጣት ለህዝብ ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው ተብሏል።


ይህ ፊልም በህወሀት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ሲሆን በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የተነሳባቸውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ ስልጣን የያዝነው ብዙ ታግድለን ነው የመጣነው የሚል አጉል ጀብደኝነትን ያሳያል ሲሉ አክትቪስቶች ይናገራሉ፡፡

 BBN