ረሃብ ጊዜ አይሰጥም::ለቻይና እና ቱርክ ሸቀጦች ቅድሚያ እንዲራገፉ በማድረግ በረሃብ አለንጋ ዜጎቹን በመግረፍ የሚገድል አገዛዝ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ረሃብ ጊዜ አይሰጥም::ለቻይና እና ቱርክ ሸቀጦች ቅድሚያ እንዲራገፉ በማድረግ በረሃብ አለንጋ ዜጎቹን በመግረፍ የሚገድል አገዛዝ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiopiafamine‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በምግብ እሕል ራሳችንን ችለናል እየተባለ ከውጭ አገራት 450 ሺህ ሜትሪክ ቶን የእርዳታ ስንዴ በውጪ ሃይሎች ድጋፍ መግዛት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? የሚያወራውን እና የሚተገብረውን የማያመዛዝን የማይናበብ አገዛዝ በጅቡቲ ወደብ የተከማቸው የእርዳታ እህል ገና መራገፍ እንዳልጀመረ የእርዳታ እህሉን የጫኑ አስር ያህል መርከቦች ጭነታቸውን ለማራገፍ ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙ ከጅቡቲ ወደብ አስተዳደር እና የእርዳታ ድርጅቶች እየተናገሩ ባሉበት ወቅት የወያኔ አገዛዝ ለማዳበሪያና ለስንዴ ቅድሚያ ተሰጥቶ የማራገፍ ስራው እየተከናወነ እደሆነ ሲዋሽ ተይዟል::ረሃብ ጊዜ አይሰጥም::የቻይና መንግስት የሚልካቸው እቃዎች ፈጥነው በመራገፍ እየተጫኑ ወደ አገር ቤት ሲገቡ ለሕዝቦቹ ደንታ የሌለው አገዛዝ በግዢ የመጣው እህል በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች እንዳይደል በሃስት መግለጫ ጋሬጣ ሆኗል::

Minilik Salsawi's photo.

ለግል ንብረቶቻቸውና ለቻይና ለቱርክ እንዲሁም ለሕንድ ሸቀጦች ቅድሚያ እንዲራገፍ ያስደረገው የኢትዮጵያ መንግስት ነው የሚሉት የጅቡቲ የወደብ አስተዳዳሪዎች የወደብ መጨናነቅ የፈጠረው የወያኔ አገዛዝ እንደሆነ ተናግረዋል::ለዘገባው ቅርብ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት ከሆነ በጅቡቲ ወደብ ያለውን የእርዳታ እህል ለማራገፍ አንድ ወር ሊፈጅ ይችላል ሲሉ የኢሕኣዴግ መንግስት ግን ከዚህ በፊት ሃገር ቤት በገቡ የእርዳታ እህል የተቀረጹ ሃሰተኛ ፊልም በማቀናበር የእርዳታ እህሎቹ ተራግፈው አገር ቤት እንደገቡ በማስመሰል ሁኔታውን ለማረጋጋት ይሞክራል ሲሉ መረጃ ሰጥተዋል::

ከቀናት በፊት ኢሳት ባወጣው የዜና ዘገባው ድርቁ በተለየ መልኩ በከፋባቸው እንደ ሶማሌና አፋር ባሉ ክልሎች ሁኔታውን ተዘዋውረው የተመለከቱ የረድኤት ሰራተኞች ለኢሳት እንደተናገሩት ፤ በተጠቀሱት ክልሎች ባሉ የማገገሚያ ጣቢያዎች ከመክሳታቸው ብዛት ቆዳቸው አጥንታቸው ጋር የተጣበቀና ጭንቅላቶቻቸው ብቻ የቀሩ ህጻናት በሞት ቋፍ ላይ ሆነው እያጣጣሩ ይታያሉ። በህይወቴ በረሀብ ሳቢያ የዚህ አይነት ዘግናኝ ነገር ሲከሰት ዓይቼ አላውቅም የሚሉት አቶ መስፍን የተባሉ የረድኤት ሰራተኛ፤ የህጻናቱን ሁኔታ ሲመለከቱ አምርረው ማልቀሳቸውን አልሸሸጉም። ሲል ዘግቧል:: http://www.mereja.com/amharic/489054 ይህ ዘገባ የሚያሳየው ረሃቡ ከተጠበቀው ገደብ አልፎ እጅግ አስደንጋጭ አደጋ እያደረሰ መሆኑን ነው::