መቐለ ከተማ እየተደረገ ያለው የባጃጅ ኣድማ 4ተኛ ቀኑ ይዘዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የባጃጅ ኣድማ 4ተኛ ቀኑ ይዟል
=============

መቐለ ከተማ እየተደረገ ያለው የባጃጅ ኣድማ 4ተኛ ቀኑ ይዘዋል። Bajaj Protests

መንግስት “ከ300 በላይ ባጃጆች ላጠፉት ጥፋት 500 ብር እየተቀጡ የይቅርታ ደብዳቤ ኣስተስገብተው ታፔላ እየወሰዱ ነው” በኤፍ ኤም ራዲዮዎች ቢናገም በተግባር ግን ኣድማው ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው።

ከ20 የማይበልጡ ባጃጆች ታፔላ ኣድርገው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሲሆን እንቅስቃሴው ኣገልግሎት ለመስጠት ሳይሆን በውስጣቸው ታጣቂ ፖሊስና ድህንነቶች በማሳፈር ተቃውሞ የሚገልፅ ወጣት ኣሳድደው እያሰሩ ይገኛሉ።
እስካሁን ድረስ በባጃጅ የትራንስፖርት ኣገልግሎት ያገኘ ህዝብ የለም።

በየክፍለ ከተማው ፖሊስ ጣብያዎች ከ50 በላይ ኣሽከርካሪዎችና በርካታ ኣድማው የደገፉ የመቐለ ከተማ ወጣቶች እየታሰሩ ነው።

በማቆምያ ቦታ የሚገኙ ባጃጆችም እንዳይንቀሳቀሱ በታጣቂዎች ታግተው ይገኛሉ። ከየቤቱ እየታሰሱ ወደ ፖሊስ ጣብያ እየተወሰዱ ነው።

መንግስት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ዓፈናና እስር በመምረጡ ህዝብ ተቃውሞው እየጨመረ ነው።

ይሄ በስራ ኣጥነት፣ በፍትህ እጦት፣ በድህነት፣ በድርቅ የተነሳ ችጋር፣ በሙስና ችግር የተጎሳቆለ ማህበረሰብ ንቀት፣ እብሪትና ጡጫ ለባሰ ችግርና ህዝባዊ ንቅናቄ የሚያነሳሳ መሆኑ ማወቅ ኣለበት።

*ኣትኪ ዘሎ ቖልዓ ኣይተብኪ በሉ ኣቦ ይርጋ።

በምስሉ የሚታዮ ባጃጆች በዓዲ ሹምድሑን ፖሊስ ጣብያ የታሰሩት ናቸው።

‪#‎BAJAj_PROTESt_Mekelle_TIGRAY_ETHIOPIA‬

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

Amdom Gebreslasie's photo.